Get Mystery Box with random crypto!

#የጥቁር #አዝሙድ #የጤና #ጥቅሞች #በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን | Fast mereja

#የጥቁር #አዝሙድ #የጤና #ጥቅሞች



#በቅንነት #ሼር #ያድርጉልን

ዉድ pተከታታዮች ለዛሬ ስለ ጥቁር አዝሙድ ጥቅሞች ልንነግራችሁ ወደድን ተከታተሉን
ጥቁር አዝሙድ ከመቶ በላይ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ይይዛል ከነዚህ መካከል ፕሮቲን ፣ካርቦሃይድሬት፣የስብ አሲዶች ፣ካልሲየም ፣ፖታሲየም ፣ብረት ፣ዚንክ፣ማግኒዥየም ፣ቫይታሚን ኤ፣ቢ፣ሲ በዋናነት ይይዛል፡፡
#ጥቅሞች

ለመተንፈሻ አካላት ኢንፌክሽን
በዘይቱ ደረትንና ጀርባን ማሸት፤ በቀን ሦስት የሾርባ ማንኪያ መጠጣት እንዲሁም ሁለት ማንኪያ በፈላ ውኃ ውስጥ ጨምሮ
በእንፋሎቱን ቤትን ማጠን

ለራስ ምታት
በጥቁር አዝሙድ ዘይት ግንባርንና በጆሮ አካባቢ ያለውን አካል ማሸት ፤ለሦስት ተከታታይ ቀናት አንድ ሻይ ማንኪያ የጥቁር
አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መጠጣት

ለጀርባ ሕመም
የተወሰነ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በጥቂቱ በማሞቅ የታመመውን አካል አጥንትን ዘልቆ እስኪሰማ ድረስ በዘይቱ በደንብ መታሸት
በቀን ሦስት ጊዜ አንድ የሾርባ ማንኪያ ዘይት መጠጣት

ለልብ ሕመም
የጥቁር አዝሙድ ዘይት ከትኩስ መጠጥ ጋር በተከታታይ መውሰድ ስብን ለማሟሟትና የደም ሥሮችን ለማስፋት
ይረዳል

ለደም ብዛት
ትኩስ መጠጥ ባሰኘው መጠን ጥቂት የጥቁር አዝሙድ ዘይት ጠብታዎችን ጨምሮ መጠጣት፡፡ በተጨማሪም ገላውን ጥቁር
አዝሙድ በመቀባት ቢያንስ በየሳምንቱ አንድ ጊዜ የፀሐይ ሙቀት ማግኘት

ለጨጓራና ለአሲድ
አንድ ኩባያ ወተት የአንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በቀን ሦስት ጊዜ መውሰድ

ለኩላሊት ኢንፌክሽን
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ በየቀኑ በባዶ ሆድ ለአንድ ሳምንት ጥሬውን መቃም፤ ጥቁር አዝሙድን በሚገባ መፍጨትና ከማር ጋር ቀይጦ በሚገባ ማዋሀድ ከዚያም ሁለት ማንኪያ ከቅይጡ ቀንሶ በአንድ ብርጭቆ የሞቀ ውኃ ውስጥ ጨምሮ በባዶ ሆድ መጠጣት

ለሐሞት ከረጢት
አንድ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዱቄት፣ ሩብ ማንኪያ የተፈጨ እሬት፣ አንድ ኩባያ ማር ጋር መለወስና ጧትና ማታ መብላት

ለጉሮሮ ሕመም
የጥቁር አዝሙድ አፍልቶ መጉመጥመጥና  አንድ ማንኪያ አዘጋጅቶ ለብ ባለ ውኃ ውስጥ ጨምሮ መጠጣትና በዘይቱም የጉሮሮን ውጫዊ አካል መቀባት በውስጥ ደግሞ መንጋጋን መቀባት

ለቆዳ ውበት
አንድ ማንኪያ ጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ማንኪያ የወይራ ዘይት ጋር አዋሕዶ ፊትን መቀባት አንድ ሰዓት ቆይቶ በውኃና በሳሙና
መታጠብ

የማስታወስ ችሎታንና ፈጣን የግንዛቤ አቅምን ለመጨመር
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት፣ 100 ሚሊ ሊትር የፈላ ናና ተክል ጋር ተቀላቅሎ ለአሥር ተከታታይ
ቀናት መውሰድ

ለጭንቀት
አንድ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት በባዶ ሆድ መውሰድ ሰዉነትን ያረጋጋል አንድ ትልቅ የሾርባ ማንኪያ የጥቁር አዝሙድ ዘይት አንድ ሲኒ ቡና ውስጥ ጨምሮ መጠጣት የአእምሮ ጭንቀትን አስወግዶ መረጋጋትን ያስገኛል