Get Mystery Box with random crypto!

Fast mereja

የቴሌግራም ቻናል አርማ fetanmereja24 — Fast mereja F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fetanmereja24 — Fast mereja
የሰርጥ አድራሻ: @fetanmereja24
ምድቦች: ኢኮኖሚክስ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 42.97K
የሰርጥ መግለጫ

ፈጣን እና ወቅታዊ መረጃ በፍጥነት ያደርሶታል።

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-06 13:04:47
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታ ጠየቀ።

በክልል ትግራይ በተካሄደው ጦርነት ወቅት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊትና ታሪካዊት ቤተ ክርስቲያን እንደመሆኗ መጠን ፦

- ጦርነቱ እንዲቆም በወቅቱ መግለጫ ባለመሰጠቷ፣

- በጦርነቱ መካከል ወደ ትግራይ ክልል መግባትና መውጣት በሚቻልበት ወቅትም በክልሉ የሚገኙ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትን፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና መላው #ሕዝበ_ትግራይን በአካል በቦታው ተገኝታ ባለመጠየቋና ባለማጽናናቷ፣

- ጦርነቱ ቁሞ በአገር አቀፍ ደረጃ እርቀ ሰላም ከወረደበት ጊዜ ጀምሮ ለደረሰው ጉዳት በቅዱስ ሲኖዶስ የተወሰነውን ሰብአዊ ድጋፍ በውሳኔው መሠረት በወቅቱ ማድረስ ባለመቻሏ፣ በዚሁም የተነሣ በቤተ ክርስቲያኗና በመላው ሕዝበ ትግራይ መካከል ለተፈጠረው ቅሬታና አለመግባባት ቅዱስ ሲኖዶስ በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።
3.1K views10:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-05 14:17:16
የፌዴሬሽን ምክር ቤት የምርጫ ቦርድን ሪፖርት ማዳመጥ ጀመረ

የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት 6ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 2ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን በማካሄድ ላይ ይገኛል፡፡

ምክር ቤቱ በዛሬ ዉሎው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ቀድሞ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ያካሄዱትን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ ያቀረበውን ሪፖርት እያዳመጠ ይገኛል፡፡

ሪፖርቱን ያቀረቡት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምክትል ሰብሳቢ ውብሸት አየለ ሲሆኑ፤ የኢፌዴሪ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በ6ኛው የፓርላማ ዘመን በ1ኛ ዓመት የሥራ ጊዜ፣ ነሐሴ 12 ቀን 2014  ባካሄደው 2ኛ አስቸኳይ ስብሰባ በደቡብ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ውስጥ ይኖሩ የነበሩ የስድስት ዞኖችና የአምስት ልዩ ወረዳዎች ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔ አስፈጽሞ ሪፖርት እንዲያደርግ መታዘዙን አስታውሰዋል፡፡

በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ ሕዝብ ውሳኔውን በማስፈጸም ያዘጋጀው ሪፖርት እንደሆነም ምክትል ሰብሳቢው ገልጸዋል፡።

በቀጣይ በቀረበው ሪፖርት ላይ ውይይት እንደሚደረግ አዲስ ማለዳ ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ያገኘችው መረጃ ያመለክታል።
ተዋሕዶ  ቤተክርስቲያን እንደሆነ ቢነገርም፤ ግብጻውያኑም የይገባኛል ጥያቄ በማንሳት ለዘመናት ዉጥረትን የሚያስተናግድ ቦታ ነዉ፡፡
አምባሳደር አለልኝ ቀደም ባለዉ ጊዜ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስትያን አባቶች በገዳሙ ዉስጥ እንዲጠለሉ አንድ የግብጽ መነኩሴ በማስጠጋታቸዉ ግብጾቹ የእኛነዉ የሚል እሳቤ እንዳደረባቸዉና ከዚያ በኋላ የይገባኛል ጥያቄ ማንሳት መጀመራቸውን ተናግረዋል፡፡
4.8K views11:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-07-02 10:54:40
በሲዳማ ክልል በጤጢቻ ወረዳ ልዩ ቦታ ሀንጋኤ ከሚባል ቀበሌ አንድ ላም ሁለት አንገት፤ አራት ዓይን፤ ሁለት ፊትና አራት ጆር ያለዉ ጥጃ ወልዳለች በማለት ግርማ ካሳ ለፋስት መረጃ መረጃውን አድርሷል።
3.8K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-29 11:38:10 " ዝግጅቱ ተጠናቋል " - ትምህርት ሚኒስቴር

ትምህርት ሚኒስቴር ፤ የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂዎች የመውጫ ፈተና ዝግጅት #መጠናቀቁን አስታወቀ።

ፈተናው ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 8 ቀን 2015 ዓ.ም ድረስ ይሰጣል።

በሚኒስቴሩ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አገልግሎት ዴስክ ኃላፊ እዮብ አየነው (ዶ/ር) ለኢዜአ በሰጡት ቃል ፤  " የመጀመሪያ ዲግሪ ተመራቂ ተማሪዎችን እውቀትና ብቃት ለመለካት የሚሰጠው የመውጫ ፈተና ዝግጅት ተጠናቋል " ብለዋል።

የትምህርትና ስልጠና ባለስልጣን የትክክለኛ ተፈታኞችን ቁጥር እንዲያጣራ በማድረግ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 95 ሺህ 755 እንዲሁም ከመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች 74 ሺህ 776 ተማሪዎች ለፈተና  ይቀመጣሉ ሲሉ ገልጸዋል።

ፈተናውን ያላለፉ ተማሪዎቸ ዲግሪ እንደማይሰጣቸው እና የትምህርት ሚኒስቴር በሚያዘጋጀው የፈተና ጊዜ መሰረት ድጋሚ እንደሚፈተኑ አመልክተዋል።

ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ከተማሯቸው የትምህርት ዓይነቶች መካከል መሰረታዊ የሚባሉ ከ12 እስከ 17 የትምህርት ዓይነቶች ፈተና እንደሚወጣ ገልጸዋል፡፡

ለዚህም የፈተና ንድፍና የብቃት መመዘኛ መስፈርቶች መዘጋጀታቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከግንቦት 15 ጀምሮ ለ211 የትምህርት ፕሮግራሞች የፈተና ጥያቄዎች በማውጣት ለፈተናው ሙሉ ለሙሉ ዝግጁ እንዲሆን መደረጉን ተናግረዋል።

ፈተናው በኦንላየን የሚሰጥ በመሆኑም አስፈላጊ የቴሌኮም እና ሌሎች መሰረተ ልማቶችን ዝግጁ ለማድረግ እየተሰራ ስለመሆኑ ጠቁመዋል።

በሀገሪቱ ካሉ 325 የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት 161 እና ከመንግስት ደግሞ 44 ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እንደሚያስፈትኑ ጠቅሰዋል።

ዶ/ር እዮብ ፤ " ገበያው የሚፈልገውን ብቁ የሰው ኃይል ለማፍራት የመውጫ ፈተናው ከ2015 ጀምሮ በሁሉም የትምህርት መስኮችና መርሐ ግብሮች መስጠት እንዲቻል ስራዎች ከአንድ ዓመት በላይ ሲሰሩ ቆይቷል " ሲሉ አስታውሰዋል።

#ኢዜአ
6.8K views08:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:57:52
በነገው ዕለት ጠዋት 2:30 ላይ የኢድ ሰላት እንደሚሰገድ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አስታወቀ። ህዝበ ሙስሊሙም ይህንን አውቆ ሰዓቱን ጠብቆ በቦታው እንዲገኝ ተብሏል።

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ለህዝበ ሙስሊሙ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ።

የ1444ኛው የኢድ አል አድሃ አረፋ በዓል አስመልክቶ የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ለሚዲያ አካላት መግለጫ ሰጥቷል።

ህዝበ ሙስሊሙ በእድሳት ላይ በሚገኘው እስታዲየም የኢድ አል አደሃ አረፋ በዓል ሰላት እንዲሰግድ ከሚመለከተው አካል ጋር ማመቻቸት መቻሉ ምክር ቤቱ አስታውቋል።

ህዝበ ሙስሊሙ ሰላሙን አስጠብቆ በአንድነት፣ የተቸገሩ ወገኖች በመርዳት በዓሉን እንዲያከብር ጥሪ ቀርቧል።

JEILU TV
8.9K views09:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:41:02 በአፍሪካ ቀንድ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ ቀውስ ውስጥ ይገኛሉ - የተመድ ድርጅቶች

የአየር ንብረት ለውጥ እና ግጭትን ጨምሮ በተደራራቢ አደጋዎች ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአፍሪካ ቀንድ ነዋሪዎች በአስቸኳይ የረሃብ አደጋ እና የጤና ቀውስ ውስጥ እንደሚገኙ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ገለጹ።

በምስራቅ አፍሪካ ቀጠና የሚገኙ ሰባት ሀገራት ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ የምግብ ዋስትና እጦት ውስጥ መሆናቸውን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል። ስልሳ ሚሊዮን የሚሆን ህዝብም ንቁ እና ጤናማ ሆነው ለመቆየት የሚያስፈልገውን በቂ ምግብ እንደማያገኙም ባወጣው ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

የተቋሙ ከፍተኛ የአደጋ ጊዜ ኃላፊ ዶምኒክ ፌሬቲ፣ የረሃብ ቀውሱ የተመጣጠነ ምግብ እጦት እንዲጨምር ማድረጉን ገልፀው፣ በአፍሪካ ቀንድ ከአምስት ሚሊዮን የሚበልጡ ከአምስት ዓመት በታች ያሉ ሕፃናት ለከፋ የምግብ እጥረት መጋለጣቸውን አስታውቀዋል። ከነዚህ፣ የከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ካለባቸው ህፃናት መካከልም 1.7 ሚሊዮን የሚሆኑት ልዩ የምግብ ድጋፍ ካላገኙ ለሞት ሊዳረጉ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

"ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ ምስራቅ አፍሪካ ኮቪድ 19፣ የኢቦላ ወረርሽኝ እና ሌሎች እንደ ኮሌራ እና ኩፍኝ የመሳሰሉ ተላላፊ በሽታዎችን እንዲሁም ደንጊ የተሰኘውና በትንኝ አማካኝነት የሚተላለፈው በሽታ አስተናግዷል። የበረሀ አንበጣ ወረርሽኝም በአካባቢው የሚገኘውን ሰብሎች እና መተዳደሪያ አውድሟል" ያሉት ፌሬቲ፣ "ከሁሉ የከፋው ደግሞ በቀጠናው ያለው ሰፊ ግጭት እና አለመረጋጋት በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ቤታቸውን ጥለው እንዲሰደዱ እና እንደ ኢትዮጵያ፣ ሶማሊያ እና አለመታደል ሆኖ ሱዳንም አዳዲስ ስደተኞች እና ተፈናቃዮች እንዲፈጠሩ ማድረጉ ነው" ሲሉ እነዚህ አስደንጋጭ አኃዞች በአንድ ድንገተኛ አደጋ ብቻ የተከሰቱ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።

በአፍሪካ ቀንድ መጣል የጀመረው ዝናብ፣ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ረጅም ጊዜን ላስቆጠረው የድርቅ አደጋ እፎይታን ቢያስገኝም፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ተቋማት ግን ዝናብ ብቻውን ቀውሱን ለማስቆም በቂ እንዳልሆነ እያስጠነቀቁ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት፣ የአፍሪካ ቀንድ የሚኖሩ ሰዎች ከፍተኛ የጤና አደጋዎችን እየተጋፈጡ መሆኑን ያመለክታል። በጤና ተቋሙ የአስቸኳይ አደጋ ዋና ኃላፊ የሆኑት ሊዝቤት አልብሬችት እንደሚያስረዱት፣ አምስት አመታትን በዘለቀው ድርቅ ሳቢያ በርካታ የጤና ችግሮች ተከስተዋል።

"በቅርቡ በአፍሪካ ቀንድ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ፣ ባለፈው አመት እና በዚህ አመት እንደ ኮሌራ እና ኩፍኝ የመሳሰሉ ወረርሽኞችን እያየን ነው። ቁጥር በጣም ከፍተኛ የሆነ የወባ በሽታም አለ። ስለዚህ በጎርፍ ተፅእኖ ምክንያት እነዚህ በሽታዎች እየተባባሱ ሲሄዱ እያየን ነው" ሲሉም፣ በከፍተኛ ዝናብ እና ከባድ የጎርፍ አደጋዎች በተጎዱ አካባቢዎች የጤና ችግር እየተባባሰ እንደሚሄድ አስጠንቅቀዋል።

በምዕራቡ የአፍሪካ ቀንድ ክፍል ከድርቁ ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሁኔታ በቀጠለበት ወቅት፣ በምስራቁ አካባቢ ተጨማሪ ዝናብ የሚጠበቅ መሆኑ፣ የዓለም ጤና ድርጅት አዳዲስ ፈተናዎችን እንዲጋፈጥ እያደረገው መሆኑን አልብሬችት ጨምረው ገልፀዋል። ሁለቱም ከባድ የአየር ሁኔታ ክስተቶች የንጹህ ውሃ አቅርቦትን እንደሚቀንሱም አስረድተዋል። አልብሬችት አክለውም፣ ይህ ሁኔታ የወባ እና ሌሎች ውሃ ውለድ በሽታዎች እንዲስፋፉ እንደሚያደርግና በሰዎች የአመጋገብ እና የጤና ሁኔታ ላይ አሉታዊ ተፅእኖ እንደሚያሳድርም አክለው ገልጸዋል።

Via VoA

https://t.me/fetanmereja24
https://t.me/fetanmereja24
8.4K views09:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:29:21 Channel name was changed to «Fast mereja»
09:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-27 12:28:21 Channel photo updated
09:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 13:53:44
ሰላም! ውድ የሳፋሪኮም ቤተሰቦች ይሄ የSafaricom Ethiopia ግሩፕ ነው!!

ለመሸለም ተራ ሳይጠብቁ በፍጥነት መሸለም ይፈልጋሉ ➪እንግዲያውስ እዚህ ግሩፕ ላይ Add ያድርጉ ያደረጉትን ያህል ይሸለሙ!!

1ኛ 25 ሰው Add ሲያደርጉ 25ብር
2ኛ 50 ሰው Add ሲያደርጉ 50ብር
3ኛ 100ሰው Add ሲያደርጉ 100ብር
4ኛ 200ሰው Add ሲያደርጉ 200ብር
5ኛ 300ሰው Add ሲያደርጉ 300ብር
6ኛ 400ሰው Add ሲያደርጉ 400 ብር
ሰዎችን Add በማረግ ብቻ ይሸለሙ

ሽልማትዎን ለመቀበል ይፈልጋሉ
ማሳሰቢያ: 100 ሰው 𝗔𝗱𝗱 ካደረጉ ተጨማሪ የ100 ብር ቦነስ ያገኛሉ!!

እዚህ https://t.me/safaarri
https://t.me/safaarri
ግሩፕ ላይ 𝗔𝗱𝗱 ሲያደርጉ ብቻ ነው የስጦታው ተሸላሚ የሚሆኑት::
1.2K views10:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-12 12:33:03
መርጌታ  ዳዊት  የባህል መድሐኒት ቀማሚ ህይወት ጥበብ ናት።
0916936955ብለው ይደውሉ
መምጣት ለማይችሉ ደንበኞች የለምንም መሰናክል መላክ እንችላለን
የምንሰጣቸዉ የጥበብ አገልግሎት ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደርግ
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል
ለጥያቄዎ
0916936955
0916936955
1.8K views09:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ