Get Mystery Box with random crypto!

በአዳማ ከተማ 30 ዓመት የኖሩና መነሻቸው ከኤርትራ የሆነ ሰዎች ቤታቸው እንደፈረሰባቸው ተገለጸ! | Fast mereja

በአዳማ ከተማ 30 ዓመት የኖሩና መነሻቸው ከኤርትራ የሆነ ሰዎች ቤታቸው እንደፈረሰባቸው ተገለጸ!

በአዳማ ከተማ በ1985 ከኤርትራ ወደ ከተማው በመግባት የመኖሪያ ፍቃድ በመጠየቅ ቦታ ተመርቶላቸው ቤት ሰርተው ሲኖሩ የነበሩ ሰዎች ‹‹ሕገ ወጥ ናችሁ›› በሚል ምክንያት ቤታቸው እንደፈረሰባቸው ተገለጸ፡፡

ይህን ያለው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ በኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ አስተዳደር እና አዳማ ከተማ ስለፈጸመው የቤት የማፍረስና የአስገድዶ ማፈናቀል እንቅስቃሴዎች ባወጣው መግለጫ ነው፡፡

ኢሰመጉ በመግለጫው፤ በግንቦት 10/2014 ጀምሮ የከተማ አስተዳደሩ ‹‹ሕገ ወጥ ናችሁ›› በሚል ምክንያት የ14 አባወራ እና እማወራ ቤቶች መፍረሳቸውን አቤቱታ ቀርቦልኛል ብሏል፡፡ የቀረበለትን አቤቱታ ተከትሎ፤ የቤቶቹን መፍረስ በሥፍራው በመሄድ ማረጋገጡንም አስታውቋል፡፡

የፈረሱት ቤቶች ጠቅላላ ዋጋው ከ8 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ሲሆን፤ ኢሰመጉ በጉዳዩ ላይ ማስረጃ እንዲሰጠው የአዳማ ከተማ አስተዳደርን በደብዳቤ ቢጠይቅም መልስ ማግኘት አለመቻሉን ጠቁሟል፡፡(አዲስ ማለዳ)