Get Mystery Box with random crypto!

Fana Tv/Fbc ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ fanatvontg — Fana Tv/Fbc ™ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fanatvontg — Fana Tv/Fbc ™
የሰርጥ አድራሻ: @fanatvontg
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.04K
የሰርጥ መግለጫ

Join & share this channel
For true & fast news🙏🙏

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-02 00:23:41
ለምን ?


share fana 90
118 viewsBUKII , edited  21:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-02 00:03:32
በአዲስ አበባ ከተማ በ2 ህፃናት ላይ የተፈፀመው እጅግ ልብ የሚነካና አሳዛኝ ግድያ!!

ዛሬ በማህበራዊ ገፆች ሲሰራጭ የተሰማውና በሁለት ህፃናት ላይ ተፈፀመ ስለተባለው የግድያ ወንጀል ኢትዮ ኤፍ ኤም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ም/ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን አናግሯል።

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ (ኮምዶሚኒየም) በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል፤ የተፈፀመው ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ነው፡፡

በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ ተጠርጣሪ አማካኝነት ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሦስት አመት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ተጠርጣሪዋ በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ የህፃናቱ ህይወት በተጠርጣሪዋእንዴት እንዳለፈና ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና ህብረሰተቡም እንዲረጋጋም ም/ ኮማንደር ማርቆስ አደራ ማለታቸውን ዘገባው ያሳያል።

Share fana 90
128 viewsBUKII , edited  21:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 21:04:25 በአዲስ አበባ ነገ ለተሸከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ሆኑ

በአዲስ አበባ በነገው ዕለት ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አደረገ፡፡

ነገ ነሃሴ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከተለያዩ አቅጣጫዎች ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋናው መስሪያ ቤት እና አምባሳደር አካባቢ የሚወስዱ መንገዶች በሥራ ምክንያት ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

• ከሴንጆሴፍ መብራት ወደ ሃራምቤ ሆቴል

• ከኢሚግሬሽን ወደ ፍልውሃ

• ከፍል ውሃ ወደ ኢትዮጵያ ሆቴል

• ከጤና ሚኒስቴር ወደ ፍልውሃ

• ከለገሃር ወደ ፍልውሃ የሚወስዱት መንገዶች ሥራው እስከጠናቀቅ ድረስ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ፖሊስ አስታውቋል፡፡ ይህን በመገንዘብ አሽከርካሪዎች የትራፊክ ፖሊስ አባላት በሚያመላክቷቸው አቅጣጫ መሰረት ሌሎች አማራጭ መንገዶችን በመጠቀም አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አሳስቧል፡፡



Share fana 90
474 viewsBUKII , 18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 13:46:24
#Betking
የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር የስፖርቱ ሚድያዎች በተገኙበት የ2015 ዓ.ም ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መርሃ ግብር እጣ የማውጣት ፕሮግራምን ዛሬ ማክሰኞ ሐምሌ 26/2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 በፅ/ቤቱ አዳራሽ(ወንጌላዊት አካባቢ በሚገኘው ሜይስዊ ህንፃ 5ኛ ፎቅ) አከናውኗል።

የ15 ሳምንቱን መርሃ ግብር በምስሉ ላይ ተያይዟል።
1.0K viewsBUKII , edited  10:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-02 13:35:52 አሜሪካ የአል ቃኢዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪን መግደሏን አስታወቀች!!

አሜሪካ የአል ቃኢዳውን መሪ አይማን አል-ዛዋሂሪን በአፍጋኒስታን ዋና ከተማ ካቡል ውስጥ በፈጸመችው የድሮን ጥቃት መግደሏን ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስታወቁ።

የአሜሪካ የደኅንነት መሥሪያ ቤት ሲአይኤ ባለፈው ዕሁድ ካቡል ውስጥ ባካሄደው የፀረ-ሽብር ዘመቻ ላይ ነው ዛዋሂሪን መግደል የቻለው ተብሏል። ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ግድያውን ተከትሎ በሰጡት መግለጫ አይማን አል-ዛዋሂሪ በአሜሪካ ዜጎች ላይ ግድያ እና ጥቃትን የቀረጸ ሰው ነው ያሉ ሲሆን “አሁን ፍትህ ተሰጥቷል ፤ ይህ የአሸባሪ ቡድን መሪ ከዚህ በኋላ በሕይወት የለም” ብለዋል፡፡

የአሜሪካ ባለሥልጣናት እንዳሉት ዛዋሂሪ በአንድ በጥብቅ በሚጠበቅ ቤት በረንዳ ላይ ተቀምጦ ባለበት ወቅት ነው የአሜሪካ ሰው አልባ አውሮፕላን ሁለት ሚሳኤሎችን ተኩሶ የገደለው። እንዲሁም በቤቱ ውስጥ የነበሩ ሌሎች የቤተሰብ አባላት ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባቸው እና በጥቃቱ ዛዋሂሪ ብቻ ተነጥሎ መገደሉን መናገራቸውን ቢቢሲ አስነብቧል።

ዛዋሃሪ ከቀድሞው የአል-ቃኢዳ መሪ ቢን ላደን ጋር በመሆን ከ20 ዓመታት በፊት የተፈጸመውን የ9/11 ጥቃትን የመራ ሲሆን አሜሪካ ለረጅም ዓመታት ስታፈላልገው የቆየችው የሽብር ቡድኑ መሪ ነው። አይማን አል-ዛዋሂሪ የኦሳማ ቢን-ላደን ሕልፈትን ተከትሎም አል-ቃኢዳን ሲመራ ቆይቷል።
711 viewsBUKII , 10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 21:48:39 በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአንድ መጋዘን ግንብ ተደርምሶ በሰው ህይወትና አካል እንዲሁም በንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ።


አደጋው የደረሰው ሐምሌ 24 ቀን 2014 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 9:30 ሰዓት ሲሆን በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ክልል ልዩ ቦታው አማኑኤል ሆስፒታል አካባቢ ነው።

በመጋዘን ቤት ውስጥ ውሃ በመሙላቱ ግንቡ ተደርምሶ ከስር በሚገኙ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ በነበሩ 3 ግለሰቦች ላይ ጉዳት በማድረስ የ1 ሰው ህይወት ሆስፒታል ከደረሰ በኋላ ሲያልፍ ፤ 2 ግለሰቦች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው የመሳለሚያ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የዕለቱ ተረኛ መኮንን ምክትል ኮማንደር መዓዛ ገብረማርያም ገልፀዋል።

ኮማንደሯ አክለው እንዳስታወቁት በአፋጣኝ አደጋው በደረሰበት ቦታ በመሄድ ከሌሎች የፀጥታ አካላትና ከአካባቢው ነዋሪዎች ጋር በመሆን ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች የማውጣትና ወደ ህክምና እንዲሄዱ የማድረግ እንዲሁም ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ሰዎችን ከአደጋው ቦታ የማሸሽ ስራዎች መሰራታቸውን ምክትል ኮማንደር መዓዛ አስረድተዋል።

ኃላፊዋ አያይዘው እንደተናገሩት ከክረምቱ ወቅት ጋር ተያይዞ ለአደጋ ስጋት የሆኑ ቦታዎችን በመለየት የሚመለከታቸው አካላት ጉዳት ከመድረሱ በፊት ትኩረት በመስጠት የመፍትሔ እርምጃዎችን መወሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል።

የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት አስተያየት የመጋዘኑ ግንብ ተደርምሶ በሰው ህይወትና በአካል ላይ ጉዳት በመድረሱ የተሰማቸውን ሃዘን ገልፀው ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ፖሊስ በፍጥነት ቦታው ላይ ደርሶ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት የሰራውን ስራ አድንቀው ቀጣይም መጋዘኑ መፍትሔ ካልተበጀለት ስጋት እንደሆነባቸው ተናግረዋል።
695 viewsBUKII , 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-31 13:36:56 አትሌት ደራርቱ ቱሉ “የትግራይ አትሌቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ” መንግስት መንገድ እንዲከፍት ጠየቀች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ይህን ያለችው በ18ኛው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በድል ለተመለሰው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት በብሄራዊ ቤተ መንግስት በተዘጋጀው የሽልማት መርሀ-ግብር ነው፡፡

“የትግራይ አትሌቶች ቤተሰብ የማግኘት እድል አሁንም አላገኙም” ያለችው አትሌት ደራርቱ መንግስት ይህንን ችግር ይቀርፋል ብላ እንደምታስብም ተናግራለች፡፡“ክብርት ፕሬዝዳንታችን በእርግጠኝነት ይህንን ነገር ይቀርፋሉ ብየ እገምታለሁ”ም ነው ያለችው ደራርቱ፡፡

አትሌት ደራርቱ፤ ደስታችን እውን እንዲሆንና ለሚቀጥለው ውድድር በሙሉ ልብ እንድንሰለፍ በትግራይ የሚገኙ አትሌቶች ባሉበት ስራቸው እንዲጀምሩ እንዲሁም መምጣት ያለባቸው አትሌቶች ደግሞ እዚህ እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ ነውም ብላለች፡፡

በተጨማሪም በ18ኛው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በድል ለተመለሰው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት በብሄራዊ ቤተ መንግስት ከ50 ሺ እስከ አስከ 2 ነጥብ 75 ሚሊዮን ብር ድረስ ሽልማት ተበረክቶላቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት
የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች
1.75 ሚሊዮን ብር ፣
የብር ሜዳሊያ ላስመዘገቡ አትሌቶች
1 ሚሊዮን ብር እንዲሁም
የነሃስ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች
700 ሺህ ብር ሽልማት አግኝተዋል፡፡

ክብረ ወሰን ላሻሻሉ አትሌቶች ደግሞ ተጨማሪ የ250 ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በ10ሺ ሜትር ሜዳሊያ ውስጥ ባትገባም አትሌት ለተሰንበት ግደይ ወርቅ እንድታገኝ ወሳኝ የቡድን ስራ የሰራችው አትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና አትሌት ሰንበት ግደይ በ5ሺ ሜትር ለነበራት የቡድን ስራ እያንዳንዳቸው የ500 ሺህ ብር ሽልማት አግኝተዋል፡፡
705 viewsBUKII , 10:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-28 20:19:41 ኢትዮ ቴሌኮም ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ!

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት ዓመት 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት ዓመቱ 70 ቢሊዮን ብር ለማስገባት ታቅዶ የእቅዱን 87 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት ጨምሮ ሌሎች በሀገሪቱ የተስተዋሉ አለመረጋጋቶች ለቴሌኮም መሰረተ ልማት መውደም እና ለእቅዱ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያት ሆነዋል ነው ያሉት። አክለውም አሁን ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 66 ሚሊየን መድረሱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል። (ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው)

ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።
862 viewsBUKII , 17:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 20:39:35 የዶሮ በሽታው በቁጥጥር ስር ውሏል

"ከዛሬ ጀምሮ የዶሮ ውጤቶችን ያለምንም ስጋት መመገብ እና መጠቀም ይቻላል" - የኢትዮጲያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር

በዶሮ ላይ ተከስቶ የነበረው በሽታ በቁጥጥር ስር በመዋሉ በዶሮ ውጤቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የግብይትና የእንቅስቃሴ ገደብ ተነስቷል።

በዶሮና የዶሮ ዉጤቶች አጠቃቀም ላይ ከኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር የተሰጠ መግለጫ!!

"ባለፉት ወራት በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎችና በአንዳንድ የዶሮ እርባታዎች ላይ የዶሮ በሽታ ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጲያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር ጋር እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በሽታዉን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በሽታዉን ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ በጊዜያዊነት በዶሮና የዶሮ ምርቶች ላይ ጊዜያዊ የግብይትና የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሽታዉ በቁጥጥር ስር በመዋሉ የዶሮ ዉጤቶች( እንቁላልና የዶሮ ስጋ) ላይ በግብርና ሚኒስቴር ተጥሎ የነበረዉ የግብይትና እንቅስቃሴ ገደብ በመነሳቱ ማህበረሰቡም ሆነ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቹን መገበያየት እና ያለምንም ስጋት መመገብ መጠቀም የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡"

የኢትዮጲያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር

ሀምሌ 20 2014ዓ.ም | አዲስአበባ
840 viewsBUKII , 17:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 23:11:04 ኢዜማ ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ አስታወቀ!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የበኩሉን ሚና እንደሚወጣ ገለጸ፡፡

ፓርቲው አዲስ የመረጣቸውን 21 የብሔራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ይፋ አድርጓል፡፡ በዚህም መሰረት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ የፓርቲው መሪ፣ አርክቴክት ዮሐንስ መኮንን ምክትል መሪ፣ ዶክተር ጫኔ ከበደ ሊቀመንበር፣ አቶ አበበ አካሉ ዋና ጸሐፊ እና አቶ አንድነት ሽፈራው የፋይናንስ ሃላፊ በመሆን በጉባኤ መመረጣቸው ተገልጿል።

የፓርቲው ዋና ፀሐፊ አቶ አበበ አካሉ በዚሁ ወቅት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ለሀገራዊ ምክክሩ ስኬታማነት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ሀገራዊ ምክክሩ የሀገሪቱን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ ፋይዳው የጎላ መሆኑን ጠቅሰው ከዚህ አኳያ ኢዜማ ለምክክሩ መሳካት በትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

የፓርቲው ሊቀመንበር ዶክተር ጫኔ ከበደ በበኩላቸው ፓርቲውን በእውቀትና በክህሎት የሚመራ የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት መመረጣቸውን ተናግረዋል።ኢዜአ እንደዘገበው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላቱ የ100 ቀናት ዕቅድ አውጥተው ወደ ስራ እንደሚገቡ አስታውቀዋል ፡፡
1.1K viewsBUKII , 20:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ