Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮ ቴሌኮም ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ! ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት ዓመት 61 ነጥ | Fana Tv/Fbc ™

ኢትዮ ቴሌኮም ከ61 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ አገኘ!

ኢትዮ ቴሌኮም በ2014 በጀት ዓመት 61 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ በበጀት ዓመቱ 70 ቢሊዮን ብር ለማስገባት ታቅዶ የእቅዱን 87 ነጥብ 6 በመቶ ማሳካት መቻሉን ተናግረዋል።

በሰሜን ኢትዮጵያ የተፈጠረውን ጦርነት ጨምሮ ሌሎች በሀገሪቱ የተስተዋሉ አለመረጋጋቶች ለቴሌኮም መሰረተ ልማት መውደም እና ለእቅዱ አለመሳካት ዋነኛ ምክንያት ሆነዋል ነው ያሉት። አክለውም አሁን ላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 66 ሚሊየን መድረሱን ዋና ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

ይህን በማስመልከት ለሦስት ቀናት የሚቆይ ነጻ ጥቅል ስጦታ ማቅረቡን ገልጿል።

ኢትዮ ቴሌኮም ያስመዘገበውን ስኬት አስመልክቶ ከህብረተሰቡ ጋር ለመጋራት ሲል የዳታ፣ ድምፅ እና የመልዕክት ጥቅል ስጦታዎችን ማቅረቡን ነው ዛሬ ያሳወቀው።

በዚህም፦

1.5 ጌጋባይት ዳታ በቀን 512 ሜባ፤

45 ደቂቃ በቀን 15 ደቂቃ፤

100 መልዕክት በቀን 33 መልዕክቶችን፤

የ10 ደቂቃ አለምአቀፍ ጥሪ በቀን 3 ደቂቃ ለተጠቃሚዎች በነጻ አቅርቧል። (ዓለም አቀፍ የጥሪ ስጦታው የተበረከተው ያልተገደበ የድምጽ ጥቅል፣ የጹሑፍና የኢንተርኔት ለሚጠቀሙ ነው)

ስጦታው ከዛሬ ሐምሌ 21 ከሌሊቱ 06:00 ሰአት - እስከ ምሽቱ 12 ሰአት ድረስ ለ3 ቀናት ይቆያል።