Get Mystery Box with random crypto!

የዶሮ በሽታው በቁጥጥር ስር ውሏል 'ከዛሬ ጀምሮ የዶሮ ውጤቶችን ያለምንም ስጋት መመገብ እና መ | Fana Tv/Fbc ™

የዶሮ በሽታው በቁጥጥር ስር ውሏል

"ከዛሬ ጀምሮ የዶሮ ውጤቶችን ያለምንም ስጋት መመገብ እና መጠቀም ይቻላል" - የኢትዮጲያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር

በዶሮ ላይ ተከስቶ የነበረው በሽታ በቁጥጥር ስር በመዋሉ በዶሮ ውጤቶች ላይ ተጥሎ የነበረው የግብይትና የእንቅስቃሴ ገደብ ተነስቷል።

በዶሮና የዶሮ ዉጤቶች አጠቃቀም ላይ ከኢትዮጵያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር የተሰጠ መግለጫ!!

"ባለፉት ወራት በአንዳንድ የሀገራችን ክፍሎችና በአንዳንድ የዶሮ እርባታዎች ላይ የዶሮ በሽታ ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል። ይህንንም ተከትሎ የግብርና ሚኒስቴር ከኢትዮጲያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር ጋር እና ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ በሽታዉን የመከላከልና የመቆጣጠር ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በሽታዉን ለመቆጣጠር ያስችል ዘንድ በጊዜያዊነት በዶሮና የዶሮ ምርቶች ላይ ጊዜያዊ የግብይትና የእንቅስቃሴ ገደብ ተጥሎ የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በሽታዉ በቁጥጥር ስር በመዋሉ የዶሮ ዉጤቶች( እንቁላልና የዶሮ ስጋ) ላይ በግብርና ሚኒስቴር ተጥሎ የነበረዉ የግብይትና እንቅስቃሴ ገደብ በመነሳቱ ማህበረሰቡም ሆነ ዶሮ አርቢዎች ምርቶቹን መገበያየት እና ያለምንም ስጋት መመገብ መጠቀም የሚቻል መሆኑን እንገልፃለን፡፡"

የኢትዮጲያ ዶሮ አርቢዎችና አቀናባሪዎች ማህበር

ሀምሌ 20 2014ዓ.ም | አዲስአበባ