Get Mystery Box with random crypto!

አትሌት ደራርቱ ቱሉ “የትግራይ አትሌቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ” መንግስት መንገድ እንዲከፍ | Fana Tv/Fbc ™

አትሌት ደራርቱ ቱሉ “የትግራይ አትሌቶች ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲገናኙ” መንግስት መንገድ እንዲከፍት ጠየቀች

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ይህን ያለችው በ18ኛው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በድል ለተመለሰው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት በብሄራዊ ቤተ መንግስት በተዘጋጀው የሽልማት መርሀ-ግብር ነው፡፡

“የትግራይ አትሌቶች ቤተሰብ የማግኘት እድል አሁንም አላገኙም” ያለችው አትሌት ደራርቱ መንግስት ይህንን ችግር ይቀርፋል ብላ እንደምታስብም ተናግራለች፡፡“ክብርት ፕሬዝዳንታችን በእርግጠኝነት ይህንን ነገር ይቀርፋሉ ብየ እገምታለሁ”ም ነው ያለችው ደራርቱ፡፡

አትሌት ደራርቱ፤ ደስታችን እውን እንዲሆንና ለሚቀጥለው ውድድር በሙሉ ልብ እንድንሰለፍ በትግራይ የሚገኙ አትሌቶች ባሉበት ስራቸው እንዲጀምሩ እንዲሁም መምጣት ያለባቸው አትሌቶች ደግሞ እዚህ እንዲመጡ ማድረግ አስፈላጊ ነውም ብላለች፡፡

በተጨማሪም በ18ኛው የዓለም አትሌቲክሰ ሻምፒዮና በድል ለተመለሰው የአትሌቲክስ ልዑካን ቡድን አባላት በብሄራዊ ቤተ መንግስት ከ50 ሺ እስከ አስከ 2 ነጥብ 75 ሚሊዮን ብር ድረስ ሽልማት ተበረክቶላቸዋል፡፡

በዚሁ መሰረት
የወርቅ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች
1.75 ሚሊዮን ብር ፣
የብር ሜዳሊያ ላስመዘገቡ አትሌቶች
1 ሚሊዮን ብር እንዲሁም
የነሃስ ሜዳሊያ ላመጡ አትሌቶች
700 ሺህ ብር ሽልማት አግኝተዋል፡፡

ክብረ ወሰን ላሻሻሉ አትሌቶች ደግሞ ተጨማሪ የ250 ሺ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ በ10ሺ ሜትር ሜዳሊያ ውስጥ ባትገባም አትሌት ለተሰንበት ግደይ ወርቅ እንድታገኝ ወሳኝ የቡድን ስራ የሰራችው አትሌት እጅጋየሁ ታዬ እና አትሌት ሰንበት ግደይ በ5ሺ ሜትር ለነበራት የቡድን ስራ እያንዳንዳቸው የ500 ሺህ ብር ሽልማት አግኝተዋል፡፡