Get Mystery Box with random crypto!

Fana Tv/Fbc ™

የቴሌግራም ቻናል አርማ fanatvontg — Fana Tv/Fbc ™ F
የቴሌግራም ቻናል አርማ fanatvontg — Fana Tv/Fbc ™
የሰርጥ አድራሻ: @fanatvontg
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 2.04K
የሰርጥ መግለጫ

Join & share this channel
For true & fast news🙏🙏

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-07-18 22:24:33
የመኖሪያ ቤት ሽልማት ለባለ እድለኞች ከአሀዱ ባንክ፡፡
ሰላም ፍቅር ጤና እንዲሆንላቹ እየተመኘን የባንኩ ቦርድ ሊቀመንበር አቶ መላኩ ፋንታ ሀገራዊ ለዉጡን ተከትሎ ሀገራዊ ኢኮኖሚዉን ለማሳደግ የተከፈተ ባንኩ ሲሆን በሀገሪቱ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ላይ አስተዋጽዎ ለማድረግ የተጀመረ ባንክ ነዉ ብለዋል። በዚህም ባንካችን ስራ በመጀመሩ ምክንያት ለመላው ኢትዮጵያውያን መልካም ስጦታ ይዘን ቀርበናል እናም እድለኛ ለሆኑ 3 የአዲስ አበባ ወይም ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚኖሩ ነዋሪዎች የመኖርያ ቤት አፓርታማ ልንሸልምዎ ዝግጅታችንን ጨርሰናል፡፡
1ኛ እጣ ባለ 3 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
2ኛ እጣ ባለ 2 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
3ኛ እጣ ባለ 1 መኝታ ከነሙሉ እቃው፡፡
ቀጥሎ ላሉ 100 እድለኞች የ1000 ብር ያልተገደበ የኢንተርኔት አገልግሎት ሽልማት ይኖረዋል፡፡ ይህ እጣ የሚቆየው እስከ ሰኔ 30 ሲሆን ሰኔ 30 ላይ በኮምፒዩተር እጣ አወጣጥ ዘዴ በመታገዝ እድለኞችን ሰኔ 30 ላይ በዚ ቻናል ላይ ይፋ የምናደርግ ይሆናል፡፡
ከእናንተ ሚጠበቀው ቻናላችንን መቀላቀል እንዲሁም ደግሞ ለዘመድ አዝማድዎ ለወዳጅዎ ለግሩፖች እድላቸውን እንዲሞክሩ ቢያንስ ለ60 ሰዎች ሼር በማረግ እንዲቀላቀሉ መጋበዝ ብቻ ነው፡፡ ከ 60 ሰው በላይ መጋበዝ እድልዎን ያሰፋል፡፡

መልካም እድል ከ አሀዱ ባንክ፡፡

https://t.me/ahaduu_bank
https://t.me/ahaduu_bank
https://t.me/ahaduu_bank
1.4K viewsBUKII , 19:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 21:48:39 ከሻምፒዮኗ አትሌታችን ጎይቶም አንደበት...!

- ለቤተሰቤ 3ኛ ልጅ ነኝ። እናቴ እኔን አርግዛ በአካባቢው ትልቅ ክብር ታገኝ ነበር፣ ከዚያ ስወለድ "ጎቲይቶም" አለችኝ - 'እመቤት' እንደማለት።

- ደስ ብሎኛል፣ ደስታዬ ግን የተዘበራረቀ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ እንደተደሰተው የእኔ እናትና አባትም ሲደሰቱ ብሰማና ባያቸው ደስ ይለኝ ነበር። እግዚአብሔር ሰላሙን ያምጣና ... ። ደስታው ትልቅ ነው፣ ግን ደግሞ ትንሽ ተዘበራረቀብኝ።"

- አምና በዚህ ጊዜ የት እንደነበርኩ አውቃለሁ። መንገድ ተከፍቶ ነው የወጣሁት። በመጀመርያ እግዚአብሔር ነው የረዳኝ፣ ከዚያም በማሰልጠን ብቻ ሳይሆን እንደ ወንድም ሆነው እንዳይከፋኝ እያገዙ ለዚህ ያበቁኝ አሰልጣኞቼ ናቸው። አይዞሽ ሁሉም ያልፋል እያሉ እዚህ አደረሱኝ። አመሰግናቸዋለሁ!

Via Abiy W Mekonnen
759 viewsBUKII , 18:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-10 12:38:00
በምእራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ ከ130 ሺ ሊትር በላይ የተደበቀ ናፍጣ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡
1.2K viewsBUKII , 09:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-09 10:51:14 ለመላው የእስልምና እምነት ቤተሰቦች በሙሉ እንኳን ለ1443ኛው የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችው በዐሉ የሰላም ፣ የደስታ ፣ የስኬት እና የፍቅር ይሁንላችሁ!
1.0K viewsBUKII , 07:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-07 10:04:06 ጀምሯል!
ፓርላማው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ መወያየት ጀመረ!

ፓርላማው በዛሬው ውሎው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአንዳንድ የሀገራችን አካባቢዎች በንፁሃን ዜጎች ላይ በተደጋጋሚ እየተፈፀመ ስላለው ኢ-ሰብዓዊ ጥቃት ዐቢይ ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ ተገልጿል። በተጨማሪም ምክር ቤቱ በረቂቅ በጀቱ ላይ የሚቀርብለትን ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ ያጸድቃል።
1.1K viewsBUKII , 07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 23:41:02 የአፍሪካ ሕብረት፤ የፌዴራል እና የኦሮሚያ ባለስልጣናት የአናሳ ዜጎችን ደህንነት እንዲያስጠብቁ አሳሰበ!!

የህብረቱ ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ ማሃማት በኦሮሚያ ክልል በተከሰቱና እየተከሰቱ ባሉ የዜጎች ጭፍጨፋ ዙሪያ መግለጫ አውጥተዋል፡፡ኮሚሽን ሊቀመንበሩ የኦሮሚያ እና የፌዴራል መንግስታት በክልሉ የሚኖሩ በቁጥር አናሳ የሆኑ ዜጎችን ደህንነት እንዲጠብቁ አሳስበዋል፡፡

የኦሮሚያ እና የፌዴራል መንግስታት በክልሉ የሚኖሩ ዜጎችን ደህንነት መጠበቅ እንዳለባቸው ያሳሰቡት ሙሳ ፋኪ እነደዚህ አይነት ድርጊቶችን ቀድሞ መከላከል እንደሚገባም ጠቅሰዋል፡፡የአፍሪካ ሕብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር፤ በኦሮሚያ ክልል በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ግድያ በአፋጣኝ ምርመራ እንዲደረግበትምም ነው በመግለጫው ጥሪ ያቀረቡት፡፡

አህጉራዊው ተቋም ከኢትዮጵያ ሕዝብ አብሮነትን፣ አንድነትን፣ ሰላምንና እርቅን ከሚያቀነቅኑ ኃይሎች ጋር በጋራ እንደሚሰራ ገልጿል፡፡ በግድያው የተሰማቸውን ሃዘን የገለጹት ሊቀመንበሩ ከኢትዮጵያውያን ጎን መቆማቸውን አሳውቀዋል፡፡በግድያው ጉዳይ ላይ የመከረው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከደቂቃ የህሊና ጸሎት የዘለለ ተግባር እንዲፈጽም በአባላቱ ተጠይቋል፡፡
1.1K viewsBUKII , 20:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 15:39:02 የጋዜጠኛውን ዋስትና ባለመከበሩ ፖሊስ ኮሚሽነሩ ለፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ታዘዘ

የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ዋስትና ባለማክበር የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽነር ፍርድ ቤት እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ተሰጠ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሀሰን አርጋው የፍርድ ቤት ትዕዛዝን እንዲፈፅሙ አልያም ያልፈፀሙበትን ምክንያት እንዲያስረዱ ብይን ተሰጠ።

የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት 1ኛ የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በ100 ሺህ ብር የገንዘብ ዋስትና ከእስር እንዲፈታ ሰኔ 27 ቀን 2014 ዓ.ም. ትዕዛዝ መስጠቱ የሚታወስ ነው።

ይሁን እንጂ ትዕዛዙን እንዲፈጽም በፍርድ ቤት የታዘዘው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ሃላፊዎች የሉም በማለት ጋዜጠኛ ተመስገንን ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ በተቃራኒ አስሮ ይገኛል ሲል ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ገልጿል።

የጋዜጠኛው ጠበቃ ሔኖክ አክሊሉ በበኩላቸው የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመፈጸሙን አስመልክቶ በትናንትናው ቀን ያቀረቡትን አቤቱታ ችሎቱ ዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም. መርምሮ ትእዛዝ ሰጥቶበታል። አቤቱታውን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት የፀረ ሽብር ጉዳዮች ችሎት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዲፈጽሙ ወይም ያልፈፀሙበትን ምክንያት ቀርበው እንዲያስረዱ ለነገ ሰኔ 30 ቀን 2014 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ቀጠሮ ተሰጥቷል።
911 viewsBUKII , 12:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-06 11:56:19 የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተግባራዊ መሆን ጀመረ!

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሸከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ሰኔ 29 ቀን 2014 ዓ.ም ጀምሮ ከ160 ሺሕ በላይ ተሽከርካሪዎች ላይ ተግባራዊ መሆን መጀመሩን የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሸከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ ማድረጋቸውን ሚኒስቴሩ አስታውሷል።

የብሔራዊ የታለመለከት የነዳጅ ድጎማን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አስተማማኝና ቀልጣፋ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺሕ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ ተብሏል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሸከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት
- ባለሦስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) በቀን 7 ሊትር
- መለስተኛ የከተማ ታክሲ (ላዳ) በቀን 25 ሊትር
- ሚኒባስ ታክሲ በቀን 65 ሊትር
- መለስተኛ አውቶብስ በቀን 94 ሊትር
- የከተማ አውቶብስ በቀን 102 ሊትር
- የሕዝብ አውቶብስ በቀን 25 ሊትር
- ሀገር አቋራጭ አውቶብስ በቀን 65 ሊትር ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ሚኒስቴሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።

Share
821 viewsBUKII , 08:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ