Get Mystery Box with random crypto!

በአዲስ አበባ ከተማ በ2 ህፃናት ላይ የተፈፀመው እጅግ ልብ የሚነካና አሳዛኝ ግድያ!! ዛሬ በማህ | Fana Tv/Fbc ™

በአዲስ አበባ ከተማ በ2 ህፃናት ላይ የተፈፀመው እጅግ ልብ የሚነካና አሳዛኝ ግድያ!!

ዛሬ በማህበራዊ ገፆች ሲሰራጭ የተሰማውና በሁለት ህፃናት ላይ ተፈፀመ ስለተባለው የግድያ ወንጀል ኢትዮ ኤፍ ኤም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ም/ ኮማንደር ማርቆስ ታደሰን አናግሯል።

በአዲስ አበባ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 4 ቦሌ አራብሳ የጋራ መኖሪያ (ኮምዶሚኒየም) በሁለት ህፃናት ላይ የተፈፀመው የግድያ ወንጀል፤ የተፈፀመው ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ነው፡፡

በቤት ሠራተኝነት ተቀጥራ በምትሰራ ተጠርጣሪ አማካኝነት ክርስቲያን መላኩና ወንጌላዊት መላኩ የተባሉ የሁለት ዓመትና የሦስት አመት ህፃናት ህይወት አልፏል፡፡

የአዲስ አበባ ፓሊስ ኮምሽን ም/ኮማንደር ማርቆስ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍኤም እንደተናገሩት ተጠርጣሪዋ በቁጥጥር ስር ውላለች፡፡ የህፃናቱ ህይወት በተጠርጣሪዋእንዴት እንዳለፈና ሌሎችንም መረጃዎች ፓሊስ ተጨማሪ መረጃ እያጣራ እንደሚገኝ እና ህብረሰተቡም እንዲረጋጋም ም/ ኮማንደር ማርቆስ አደራ ማለታቸውን ዘገባው ያሳያል።

Share fana 90