Get Mystery Box with random crypto!

የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewketbirhan — የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewketbirhan — የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት
የሰርጥ አድራሻ: @ewketbirhan
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.88K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት መንፈሳዊ ጽሑፎችን፣ የሰ/ት/ቤታችንን የአገልግሎት እንቅስቃሴ እንዲሁም ወቅታዊ የቤተ-ክርስቲያን መረጃዎችን የምንለቅበት የቴሌግራም ገፃችን ነው።
ይቀላቀሉን👉 https://t.me/EwketBirhan

ለማንኛውም ሀሳብ እና አስተያየት
👉 @meaZina19 ይላኩልን

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-09-01 17:43:11 በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!

              የአገልግሎት ጥሪ

ለእውቀት ብርሃን ሰንበት ት/ቤት አባላት በሙሉ


የ2014 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የመዝሙር ጥናት በታዕካ ነገሥት በአታ ለማርያም ገዳም ስለተጀመረ ካቴድራላችንን ወክላችሁ መሳተፍ የምትፈልጉ አባላት በአባላት እንክብካቤ እና ግንኙነት ክፍል ወይም በስልክ ቁጥር +251938035698/+251913166536 በመደወል መመዝገብ ትችላላችሁ።

የመዝሙር ጥናቱ ከጠዋቱ 2:00 - 6:00 ሲሆን የትምህርትና ሥራ ፈቃድ ለምትፈልጉ የሚፃፍላችሁ ይሆናል።

#እውቀት_ብርሃን_ሰንበት_ትምህርት_ቤት

     @EwketBirhan
246 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, edited  14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 17:43:31 Quiz '#ካነበቡት_እንጠይቅዎ /7/ በቴሌግራምና በፌስቡክ ገፅ ላይ ከቀረቡ ጽሑፎች ላይ የተወጣጡ ጥያቄዎች' 4 questions · 1 min
342 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, 14:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 12:39:08 የእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዓለ ዕረፍት አከባበር በደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቤ/ክ
   ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም
    ለዓመቱ በሰላም ያድርሰን
@PhotoEwketBirhan
https://t.me/PhotoEwketBirhan/1877?single
378 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, 09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 21:17:06 የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት pinned a photo
18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:49:22 Quiz '#ካነበቡት_እንጠይቅዎ /7/ በቴሌግራምና በፌስቡክ ገፅ ላይ ከቀረቡ ጽሑፎች ላይ የተወጣጡ ጥያቄዎች'
4 questions · 1 min
232 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, 17:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 20:28:44 ሰላም ለእናንተ ይሁን! እንዴት አመሻችሁ!!
እንኳን ለእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና ለአቡነ ተክለሃይማኖት በዓለ ዕረፍት አደረሳችኹ!!!
       ◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹     

             ካነበቡት እንጠይቅዎ /7/
ዛሬም በሰዓታችን ጥያቄዎችን ይዘን ቀርበናል። ጊዜዎንና ትኩረትዎን ሰጥተው በመሳተፍዎ እያመሰገንን ለሌሎችም ሼር በማድረግ ተደራሽነታችንን ያስፉ።

ጥያቄውን ለመጀመር ከስር የተፃፈውን መመሪያ እንድታነቡ እንጠይቃለን።
   
4 ጥያዎች የቀረቡ ሲሆን ለእያንዳንዱ ጥያቄ 1 ደቂቃ ተሰቷል ጥያቄውን ለመጀመር፦
➜ ከስር ያለውን "Start this quiz" የሚለውን ተጫኑ
➜ በመቀጠል ወደሚወስዳቹ ገፅ "start" ሚለውን ተጫኑ
➜ በመጨረሻ " i am ready" ሚለውን በመጫን ጥያቄውን መሠራት ጀምሩ መልካም ቆይታ!

   ◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹

ጥያቄው እስከ ሐሙስ ነሐሴ 26 ማታ 12:00 ድረስ ይቆያል።

ጥያቄዎቹን ዘወትር ሰኞ እና ሐሙስ ማታ
       2:30 ላይ እናቀርባለን!!
   ◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹ ◂▹◂▹◂▹◂▹◂▹
                   @EwketBirhan
                መልካም ምሽት

ጥያቄ
275 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, edited  17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 14:35:07 በድጋሜ እንኳን ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት፣ ለቅድስት ክርስቶስ ሠምራ እና ለቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ ክብረ በዓል አደረሳችሁ!!!
        
ሊንኩን በመጫን ስለቅዱሳኑ የተጻፉትን ጽሑፎች እንድታነቡ እንጋብዛለን

ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
https://t.me/EwketBirhan/5093

ቅዱስ ቶማስ ዘመርዓስ
https://t.me/EwketBirhan/5091

አቡነ ተክለ ሃይማኖት
  ልደታቸው /ታኅሣሥ 24/
https://t.me/EwketBirhan/3926

ፍልሰተ ሥጋሁ /ግንቦት 12/
https://t.me/EwketBirhan/4586

ዕረፍታቸው /ነሐሴ 24/
https://t.me/EwketBirhan/5099

           መልካም በዓል
           ነሐሴ 24/2014 ዓ.ም
          t.me/EwketBirhan

ለሌሎች #በማጋራት አገልግሎቱን ይደግፉ
352 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, edited  11:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 10:24:44 እንኳን ለእናታችን ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዓለ ዕረፍት አደረሳችኹ!!!
የቅድስት ክርስቶስ ሠምራ በዓለ ዕረፍት ቀጥታ ስርጭት ከደብረ ምጥማቅ ሰአሊተ ምሕረት ቤ/ክ በዩቲዩብ ገፃችን በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉ።
ሰብስክራይብ ላይክ እና ሼር በማድረግ  አገልግሎቱን ይደግፉ!


638 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, 07:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:01:48 ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ከፅንሰታቸው ጀምሮ በሐዋርያዊ ተግባራቸውና ተጋድሏቸው ውስጥ ፈቃደ እግዚአብሔርን  ሲፈጽሙ ነውና የኖሩት፤ ስለ ዕረፍታቸው ጌታቸውን እንዲህ ሲሉ ጠይቀዋል ‹‹ጌታዬ ወደ ሰማዕትነት አደባባይ ሄጄ በስምህ እንድሞት እዘዘኝ››፡፡ ጌታችንም ‹‹መጋደልንስ ፈጸምህ፣ ከሞት በቀር ምንም ምን አልቀረህም፤ እነሆ በክፉ ሞት በሕማመ ብድብድ በሆድ ሕመም በጽኑ ደዌ በንዳድ ትሞታለህ፤ እሷንም እንደ ስቅላቴና ካንተ በፊት እንደነበሩ ሰማዕታት ደም እቆጥረዋለሁ፤ ነገር ግን ለብቻህ አይደለም፤ በዚህች ገዳም በዚህ ዓይነት ደዌ የሚሞቱትን ቁጥራቸውን ከሰማዕታት ጋር አደርገዋለሁ፤ በመንግሥተ ሰማይም ለአንተ እሰጣቸዋለሁ›› አላቸው፡፡ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር መከራ ለቅዱሳን ክብራቸውን የሚያበዛላቸው ከተሰቀለው ክርስቶስ ጋር በግብር የሚያመሳስላቸው መሆኑን ነው፤ 1ኛ ጴጥ 4፥13፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተቀበላቸው ሕማማተ መስቀል ለቤዛ ዓለም ሲሆን የቅዱሳን ግን ስለ ክርስቶስ ክብር እስከ ደም ጠብታ ደርሶ መመስከርን የሚያጠይቅ ነው።
  ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት አስቀድሞ እንደ ነገራቸው ሦስት ደቀ መዛሙርቶቻቸው በሕማመ ብድብድ በሽታ ከሞቱ በኋላ ጻድቁ አባታችንም ለ10 ቀናት በሕመም ቆይተው ዕረፍታቸው ሲደርስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያምና ከቅዱሳን መላእክት ጋር ተገልጾላቸዋል፡፡ ‹‹ወዳጄ ተክለ ሃይማኖት ሆይ! ከብዙ ድካም ወደ ዕረፍት፣ ከመከራ ወደ ደስታ ላሳርፍህ መጥቻለሁ፤ ጾምና ጸሎትህን ተቀብዬልሃለሁ፤ ስምህን በቅን ሕሊና የሚጠራውን ሁሉ ከመከራው አድነዋለሁ፤ በስምህ ዝክር የሚዘክሩና መታሰቢያህን የሚያደርጉትን አንተ ከገባህበት ውሳጤ መንጦላዕት አስገባቸዋለሁ›› የሚል ቃል ኪዳንም ሰጥቷቸዋል፡፡ ‹‹ከአንተ በኋላ በመንበርህ ላይ ኤልሳዕ ይሾማል፤ ግን ብዙ ጊዜ አይቆይም ያርፋል›› አላቸው፡፡ የጻድቁ ተክለ ሃይማኖት ቅድስት ነፍስ ከክብርት ሥጋቸው ነሐሴ 24 ቀን በይባቤ መላእክት፣ በመዓዛ ገነት፣ በመዝሙረ ዳዊት ተለየች፡፡ አርድዕቱ ቅዱስ ሥጋቸውን እንደ ሥርዓቱ ገንዘው በስብሐተ እግዚአብሔር በማኅሌት ከቁመት ብዛት እግራቸው በተሰበረበት በትሩፋት ሥራ በስግደት ብዛት ወዛቸው በተንጠፈጠፈበት በደብረ አስቦ ዋሻ አሳረፉት፡፡
   አቡነ ተክለ ሃይማኖት ባረፉ በ56ኛው ዓመት ሦስተኛው ዕጨጌ አቡነ ሕዝቅያስ አበምኔት በሆኑ ጊዜ አቡነ ተክለ ሃይማኖት በራእይ ለአቡነ ሕዝቅያስ ተገልጠው ዐፅማቸውን ወደ ቤተ ክርስቲያኑ እንዲያስገቡ ነገሯቸው፤ እርሳቸውም በየቦታው የነበሩትን ደቀ መዝሙሮቻቸውን ጠርተው ግንቦት 12 ቀን ዋሻውን ከፍተው ዐፅማቸውን በክብር አወጡት፤ ወደ ደብረ ሊባኖስ ቤተ ክርስቲያንም አስገቡት፡፡
   የጻድቁ መላ ዕድሜያቸው 99 ዓመት ከዐሥር ወር ነው፡፡ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን በየዓመቱ የጻድቁን ፅንሰታቸውን መጋቢት 24 ቀን፣ልደታቸውን ታኅሣስ 24 ቀን፣ ስባረ ዐፅማቸውን ጥር 24 ቀን፣ ዕረፍታቸውን ነሐሴ 24 ቀን፣ ፍልሠተ ዐፅማቸውን ግንቦት 12 ቀን እግዚአብሔርን በማመስገን ጻድቁን በማክበር በመንፈሳዊ ሥነ ሥርዓት ታከብራለች፡፡ የጻድቁ በረከት ከሁላችን ጋር ትሁን አሜን!
               ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
       ምንጭ፦ ገድለ ተክለ ሃይማኖት ፣ ስንክሳር ዘነሐሴ 24
- ሕይወቱ ወገድሉ ለብፁዓዊ ቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት (አውሎግሶን)

            

ሊንኩን በመጫን ከዚ በፊት የተለቀቁትን ጽሑፎች እንድታነቡ እንጋብዛለን
  የአቡነ ተክለ ሃይማኖት ልደታቸው /ታኅሣሥ 24/
https://t.me/EwketBirhan/3926

  ፍልሰተ ሥጋሁ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት /ግንቦት 12/
https://t.me/EwketBirhan/4586

  አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዕረፍታቸው /ነሐሴ 24/
https://t.me/EwketBirhan/5099

        
347 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, edited  17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 20:01:37
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ዕረፍቱ_ለቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት (ነሐሴ 24)
ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ከዚ በፊት ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ፅንሰታቸውና ልደታቸው እና ፍልሰተ ሥጋሁ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ጽሑፋችን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ደግሞ የቅዱስ ተክለ ሃይማኖትን ዕረፍት በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ‹‹ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር - የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው›› መዝ 115፥6 እንዳለ፤ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል ማርያምንና 12ቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ አባታችን መጡ፡፡ በምን ዓይነት ሕማም ነፍሳቸው ከሥጋቸው እንደምትለይ አስቀድሞ ‹‹በሥራህ ሁሉ እነሆ እኔን ተከተልህ ወዳጄ ሆይ አሁንም በመንግሥተ ሰማያት መንገሥ  ከእኔ ጋር እንድትተካከል በሞቴም ልትመስለኝ ይገባሃል›› ብሎ አስታውቋቸው ነበር፤ ጌታችን በመንግሥተ ሰማያት ከእኔ ጋር እንድትተካከል ሲል የእርሱ የባሕርይው ሲሆን ለቅዱሳኑ ግን የጸጋ ንግሥና እንደሚሰጣቸው ለማጠየቅ ነው፡፡
  
295 views𓅪ሀገሬ ሰማይ ዘሬም ፍቅር𓅪, 17:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ