Get Mystery Box with random crypto!

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! #ዕረፍቱ_ለቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት | የደ/ም/ሰ/ም/ቅ/ማርያምና ቅ/ክርስቶስ ሠምራ ካቴድራል እውቀት ብርሃን ሰ/ት/ቤት

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
#ዕረፍቱ_ለቅዱስ_ተክለ_ሃይማኖት (ነሐሴ 24)
ስለ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ታሪክ ከዚ በፊት ሐዲስ ሐዋርያ አቡነ ተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ፅንሰታቸውና ልደታቸው እና ፍልሰተ ሥጋሁ ለአቡነ ተክለ ሃይማኖት በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ጽሑፋችን ማቅረባችን ይታወሳል፡፡ በዚህ ጽሑፍ ደግሞ የቅዱስ ተክለ ሃይማኖትን ዕረፍት በአጭሩ እንዳስሳለን፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ዳዊት ‹‹ክቡር ሞቱ ለጻድቅ በቅድመ እግዚአብሔር - የጻድቅ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው›› መዝ 115፥6 እንዳለ፤ ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት የዕረፍታቸው ጊዜ ሲደርስ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅድስት ድንግል ማርያምንና 12ቱን ሐዋርያት ይዞ ወደ አባታችን መጡ፡፡ በምን ዓይነት ሕማም ነፍሳቸው ከሥጋቸው እንደምትለይ አስቀድሞ ‹‹በሥራህ ሁሉ እነሆ እኔን ተከተልህ ወዳጄ ሆይ አሁንም በመንግሥተ ሰማያት መንገሥ  ከእኔ ጋር እንድትተካከል በሞቴም ልትመስለኝ ይገባሃል›› ብሎ አስታውቋቸው ነበር፤ ጌታችን በመንግሥተ ሰማያት ከእኔ ጋር እንድትተካከል ሲል የእርሱ የባሕርይው ሲሆን ለቅዱሳኑ ግን የጸጋ ንግሥና እንደሚሰጣቸው ለማጠየቅ ነው፡፡