Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላላ እውቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewentesfa — ጠቅላላ እውቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewentesfa — ጠቅላላ እውቀት
የሰርጥ አድራሻ: @ewentesfa
ምድቦች: በጉዞ ላይ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.58K
የሰርጥ መግለጫ

🗣➹ #ይመልሱ_ይሸለሙ!
🗣➹ #መፅሐፍትን_ያውርዱ
👇👇👇👇👇👇
@ewentesfa
"አንባቢ አይሰርቅም" ሌባ ደግሞ አያነብም

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-06-20 21:28:31 #MotherOfSanitaryPad
ሜሪ ቢያትሪስ ዴቪድሰን ኬነር:-በህይወት ዘመኗ አምስት የባለቤትነት መብቶችን የተቀበለች አፍሪካዊ አሜሪካዊ ፈጣሪ ነበረች። በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ለጥቁር ሴት የተሰጡ የአብዛኞቹን የፈጠራ ባለቤትነት ሪከርድ ትይዛለች። የኬነር የመጀመሪያ እና በጣም ታዋቂው የፈጠራ ባለቤትነት እ.ኤ.አ. በ 1957 የንፅህና መጠበቂያ ቀበቶ ፣ የንፅህና መጠበቂያ ፓድ ቀዳሚ ፈጠራ ነበር።

ትልቅ ክብር እመቤት

➹share &Join Us

              @ewentesfa
2.7K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-17 20:47:01 #በዓለም_የመጀመሪያው_ዩኒቨርሲቲ

በአለም የመጀመሪያው ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተው በአፍሪካ (ሞሮኮ ) በሴት ነው። ፋጢማ ቢንት ሙሐመድ አል-ፊህሪያ አል-ቁራሺያ (فاطمة بنت محمد الفهرية القرشية) በ895 ዓ.ም በዓለም የመጀመሪያውን ዩኒቨርሲቲ በፌዝ መሰረተች ይህም አሁን በሞሮኮ ይገኛል። እሷ በተለምዶ ፋጢማ አል-ፊህሪ በመባል ትታወቃለች።
ከአባቷ ከእህቷ ጋር ባወረሰችው ሀብት ያላትን ድርሻ በመጠቀም የአል ቃራዊን ዩኒቨርሲቲ አቋቁማለች። ዩኒቨርሲቲው ትልቅ መስጊድ ሆኖ ተጀምሮ ወደ ትምህርት ቦታ አድጓል።

➹share &Join Us

              @ewentesfa
3.3K views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-14 21:17:08
ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?!

፵፩ አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው።
፵፪ ደብሩ፦ተራራው ማለት ነው።
፵፫ ምሥራቅ፦የፀሐይ መውጫ ማለት ነው።
፵፬ ይባቤ፦እልልታ ማለት ነው።
፵፭ ጥበቡ፦ብልሀተኛው ማለት ነው።
፵፮ ሃይማኖት፦ሃይማኖት ማለት ነው።
፵፯ ትሕትና፦ትሕትና ማለት ነው።
፵፰ ተከሥተ፦ተገለጠ ማለት ነው።
፵፱ በየነ፦ፈረደ ማለት ነው።
መኮንን፦ገዢ ማለት ነው።
፶፩ ሐዳስ፦አዲሱ ማለት ነው።
፶፪ ትንሳኤ፦መነሳት ማለት ነው።
፶፫ ሢራክ፦ብልሀተኛ ማለት ነው።
፶፬ ቡሩክ፦ምስጉን የተመሰገነ ማለት ነው።
፶፭ ህላዌ፦መኖር ማለት ነው።
፶፮ ማኅደር፦መኖሪያ ማለት ነው።
፶፯ ሕይወት፦መኖር ማለት ነው።
፶፰ ቤዛ፦መድኃኒት ማለት ነው። ቤዛዊት ለሴት ነው።
፶፱ ኄራን፦ደጋጎች ማለት ነው።
መርአዊ፦ሙሽራ ማለት ነው። መርአዊት ለሴት
፷፩ ተስፋ፦ተስፋ ማለት ነው።
፷፪ ዜናዊ፦ነጋሪ ማለት ነው።
፷፫ ጸዐዳ፦ነጭ ማለት ነው።
፷፬ ጸጋ፦ስጦታ ማለት ነው።
፷፭ ብሥራት፦የምሥራች ማለት ነው።
፷፮ ኅሊና፦ማሰቢያ፥ሀሳብ እውቀት ማለት ነው።
፷፯ ማህሌት፦ምስጋና ማለት ነው።
፷፰ ሐሴት፦ደስታ ማለት ነው።
፷፱ ፍሥሓ፦ደስታ ማለት ነው።
ትርሲት፦ሽልማት ማለት ነው። በተጨማሪ ስርጉት ማለት የተሸለመች ያጌጠች ማለት ነው።
፸፩ ምዕራፍ፦ማረፊያ ማለት ነው።
፸፪ መቅደስ፦ማመስገኛ፥ መመስገኛ ማለት ነው።
፸፫ ዋካ፦ብርሃን ማለት ነው።
፸፬ ረድኤት፦ እርዳታ ማለት ነው።
፸፭ ጽጌ፦አበባ ማለት ነው።
፸፮ ሠረገላ፦መኪና ማለት ነው።
፸፯ አማን፦እውነት ማለት ነው።
፸፰ አሜን፦ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ነው።
፸፱ ሰዋስው፦ድልድይ ማለት ነው።
ጸዳሉ፦ብርሃኑ ማለት ነው።

➹share &Join Us

              @ewentesfa
3.2K viewsedited  18:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-12 08:07:29 ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?!

ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው
ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው።
ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው
ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው።
ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው።
ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት
ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው።
ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው።
አስካል፦ፍሬ ማለት ነው።
በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው።
፲፩ መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው።
፲፪ መንክር፦ልዩ ማለት ነው።
፲፫ ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው።
፲፬ ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው።
፲፭ ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው።
፲፮ ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው፤ቅዱስ ለወንድ
፲፯ ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው።
፲፰ ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው
፲፱ ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው።
ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው።
፳፩ ጸገየ፦አበበ ማለት ነው
፳፪ ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው።
፳፫ ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው።
፳፬ ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው።
፳፭ ሰናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው።
፳፮ ፈታሒ፦ፈራጁ ማለት ነው።
፳፯ መዓዛ፦ጥሩ ሽታ ማለት ነው።
፳፰ መራሒ፦መሪ ማለት ነው።
፳፱ ነጋሢ/ንጉሥ፦የነገሠ ማለት ነው።
ስቡሕ፦የተመሰገነ ማለት ነው።
፴፩ ስብሐት፦ምስጋና ማለት ነው።
፴፪ ብሩህ፦የበራ ማለት ነው።
፴፫ ብርሃን፦ያው በቁሙ ብርሃን ማለት ነው።
፴፬ ትጉህ፦የተጋ ማለት ነው።
፴፭ አምኃ፦እጅ መንሻ ማለት ነው።
፴፮ ልዑል፦ከፍ ያለው ማለት ነው።
፴፯ ከሀሊ፦የሚችል ማለት ነው።
፴፰ ዳግም፦ዳግመኛ ማለት ነው።
፴፱ ማዕረር፦አዝመራ ማለት ነው።
ክቡር፦የተከበረ ማለት ነው።

➹share &Join Us

              @ewentesfa
3.2K viewsedited  05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-06 22:49:39
#ለእርጉዝ_ሴቶች_የተከለከሉ_ምግቦች

ጁስ (ፓስቸራይዝድ ያልሆነ)
ጁስ መጠጣት አትክልቶች እና ፍራፍሬዎችን በምግብ ገበታሽ ውስጥ በቀላሉ የምታካትችበት መንገድ ነው ነገር ግን ሁሉም ጁሶች ለአንቺ ንጽህና ጤናማ አይደሉም። ምክንያቱም ኢሸርሺያ ኮላይ ወይም ሊስቴሪያ (E. coli or Listeria) የተባሉ ባክቴሪያዎችን በውስጣቸው ሊይዙ ስለሚችሉ ነው።

በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋ
እርጉዝ በምትሆኝበት ጊዜ ጥሬ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋን ቻው ብለሽ መሰናበት አለብሽ። ባክቴሪያ እና ሌሎች በሽታ አምጪ ህዋሶች በደንብ ባልበሰለ ወይም በጥሬ ሥጋ ላይ እና በባህር ውስጥ ምግቦች ውስጥ መኖር ስለሚችሉ ነው።

በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ እንቁላል
እንቁላል የፕሮቲን፣ ቫይታሚን እና ሜኔራል መገኛ ምንጭ ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ የምትመገቢው እንቁላል በደንብ መብሰሉን ማረጋገጥ አለብሽ። በትክክል ካልበሰለ ግን ሳልሞኔላ (Salmonella) ለተባለ ባክቴሪያ የመጋለጥ ዕድል አለሽ።

ቡና
ካፌይን ትልቅ ትኩረት የምትሰጭው ጉዳይ ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና በእርግዝና ወቅት መጠጣት ከማስጨንገፍ/ ማስወረድ ጋር ይያያዛል።

ከፍተኛ ሜርኩሪ ያለው አሳ
እርጉዝ የሆነች ሴት ከፍተኛ የሆነ ሜርኩሪ ያላቸውን አሳዎች መመገብ ማቆም አለባት። ይህ ኬሚካል በሰውነትሽ ውስጥ የመከማቸት ባህሪ ስላለው የነርቭ ሥርዓትሽን ሊጎዳው ስለሚችል ነው።

አልኮል
ብዙ ኤክስፐርቶች እንደሚስማሙት አንድ እርጉዝ የሆነች በእርግዝናዋ ወቅት የአልኮል መጠጥ መጠጣት የለባትም የዚህም ምክንያት ልጅ ላይ የሚከሰተውን ፌታል አልኮሊክ ሲንድረምን (Fetal Alcohol Syndrome) ለመከላከል ሲባል ነው።

               @ewentesfa
3.2K views19:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 17:11:04 ይቀጥል??
public poll

አዎ – 53
95%

አይ – 3
5%

56 people voted so far.
2.8K views14:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-04 17:08:36 #ለእርጉዝ_ሴቶች_የተከለከሉ_ምግቦች

ጉበት
ቫይታሚን ኤ ህፃኑ በማህፀን ውስጥ ለሚኖረው እድገት አስፈላጊ ነው። ይህን ቫይታሚን እርጉዝ ሴቶች ከፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ሥጋ እና እንቁላል ያገኙታል። ነገር ግን ከመጠን በላይ የሆነ ቫይታሚን ኤ ለህፃኑ መጥፎ ሲሆን በወሊድ ጊዜ ችግር ያስከትላል

የወተት ምርቶች (ፓስቸራይዝድ ያልሆኑ)

እርጉዝ ሴት በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ የወተት ምርቶችን ማግኘት አለባት። በውስጣቸውም ካልሲየም፣ ፕሮቲን እና ቫይታሚን ዲ ሲይዙ የሚወለደውን ህፃን ታዳጊ አጥንት፣ ጥርስ፣ ልብ እና ነርቭ በመገንባት ይጠቅማሉ። ነገር ግን ሁሉም የወተት ምርቶች ለአንቺ ምግብነት መልካም አይደሉም ስለዚህ ጥሬ ወተት እና ሌሎች ጥሬ የወተት ምርቶችን መጠቀም የለብሽም።

በሂደት ያለፈ ሥጋ (Processed Meat)

በፍጥነት የሚደርስ እና ቀላል ምግብ መመገብ ስናስብ የአብዛኛዎቻችን ምርጫ ሳንድዊች ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ ሳንዱዊቹ ከምን ከምን እንደተሰራ በቅርበት መመልከት አለብሽ። ምክንያቱም ሊስቴሪያ ለተባለ ባክቴሪያ ሊኖረው ይችላል የሚል ስጋት ስላለ ነው። ይህ ባክቴሪያ በጣም በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እድገቱን የሚቀጥል ብቸኛ ባክቴሪያ ነው።

ሳላድ

ሳላድ ከትኩስ አትክልትና ፍራፍሬ የሚዘጋጅ ነው። ይህም ቁጥር አንድ ተመራጭ ጤናማ ምግብ ያደርገዋል። ነገር ግን በአትክልት ቤት፣ ጁስ ቤት እና ካፍቴሪያ ውስጥ ሳላድ መመገብሽን አቁሚ ምክንያቱም አትክለቶቹ የሚቀመጡበት የሙቀት ሁኔታ፣ የተዘጋጁበት ሰዓት የምግቦቹን ለጤና ተስማሚነት ስለሚወስን ነው። ስለዚህ በቤትሽ ውስጥ ሰርተሽ መመገቡ ተመራጭ ነው።

@ewentesfa @ewentesfa
2.8K views14:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-02 22:32:16
#Did_You_know??
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ከፍተኛው የቀርከሃ ክምችት የሚገኝባት ሃገር ናት ፣ 1 ሚሊዮን ሄክታር መሬት የሚሸፍን የቀርከሃ ጫካዎች ሲኖሯት አፍሪካ ውስጥ ከሚገኘው ቀርከሃ ውስጥ 67% በኢትዮጵያ ይገኛል።
በአጠቃላይ ከመላው አለም ላይ ከሚገኘው ቀርከሃ ውስጥ 7 % የሚሆነው የኛው ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ ይገኛል።

➹share &Join Us

              @ewentesfa
2.7K views19:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 12:09:20 #አስደናቂ_ጤና_ነክ_39_እውነታዎች

፳፩ ጡት ጠብተው ያደጉ ልጆች ጡት ሳይጠቡ ከማያድጉ ልጆ ይልቅ ሸንቃጣ ናቸው፡፡

፳፪ ነጣ ያለ ቆዳ ያላቸው ሰዎች ጠቆር ያለ ቆዳ ካላቸው የበለጠ ቆዳቸው ቶሎ ይጨማደዳል፡፡

፳፫ አለርጂ ያለባቸው ሰዎች በመሳቅ የአለርጂ መጠናቸውን መቀነስ ይችላሉ፡፡

፳፬ የሚያጨሱ ሰዎች ከማያጨሱ ሰዎች የበለጠ ቆዳቸው ይጨማደዳል፡፡

፳፭ ጡት ጠብቀው ያደጉ ልጆች ጡት ጠብተው ካላደጉ ልጆች የበለጠ IQ ሊኖራቸው ይችላል፡፡

፳፮ በወር ሶስት ጊዜ ቸኮሌት መብላት ከልክ በላይ ከሚበሉና እንደውም ከማይበሉ ሰዎች የበለጠ ረጅም ጊዜ ለመኖር ያስችላል፡፡

፳፯ በአማካይ አንድ ሰው በአንድ ሌሊት ውስጥ 7 ህልም ይመለከታል፡፡

፳፰ አንድ ሰው በዕድሜ ዘመኑ በአማካይ የምድርን ዙሪያ ሁለት እጥፍ ያህል ይጓዛል፡፡

፳፱ አንድ ሰው በአማካይ በቀን 15 ጊዜ ያህል ይስቃል፡፡

፴ የአንድ አማካይ ሰው መዝገበ ቃላት ብዛት ከ5,000 እስከ 6,000 ነው፡፡

፴፩ የዓለማችን 10% ያህል ህዝብ ግራኝ ነው፡፡መሸከም ይችላል፡፡

፴፪ ፈገግ ከማለት ይልቅ ኮስተር ማለት ብዙ ጡንቻ ይጠይቃል፡፡

፴፫ 1/3 የካንሰር ህመምን መከላከል ይቻላል፡፡

፴፬ በምታስነጥሱበት ወቅት ሁሉም የሰውነታችሁ ስራ ይቆማል ልባችሁን ጨምሮ፡፡

፴፭ የሰው ልጅ ጉበት ከአምስት መቶ በላይ ተግባሮችን ያከናውናል፡፡

፴፮ የልባችሁ መጠን የአንድ እጅ ጭብጣችሁን ያህል ነው፡፡

፴፯ በሳምንት ለሶስት እና አራት ሰዓት ያህል ፈጣን የእግር ጉዞ ማድረግ በልብ ህመም የመያዝ ዕድልን በ65% ይቀንሳል፡፡

፴፰ ከመሳሳም የበለጠ በመጨባበጥ ከሰው ወደ ሰው ሊተላለፉ የሚችሉ ብዙ ጀርሞች አሉ፡፡

፴፱ እንቅልፍ ከምግብ የበለጠ አስፈላጊ ነው፡፡ አንድ ሰው በእንቅልፍ እጦት ከምግብ እጦት አስቀድሞ ሊሞት ይችላል።

➹share &Join Us

              @ewentesfa
3.3K views09:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 21:32:32 ይቀጥል??
public poll

አዎ – 61
92%

አይ – 5
8%

66 people voted so far.
2.9K views18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ