ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?! ፩ ማዕዶት፦መሻገሪያ ማለት ነው ፪ ኖላዊ፦ጠባቂ ማለት ነው። ፫ ማኅቶት፦ብርሃን ማለት ነው ፬ ኂሩት፦በጎነት ማለት ነው። ፭ ሜላት፦የሐር ግምጃ ማለት ነው። ፮ ኅሩይ፦ምርጥ የተመረጠ ማለት ነው።ለሴት ኅሪት ፯ ሮዛ፦ጽጌረዳ ማለት ነው። ፰ ቀጸላ፦አክሊል ማለት ነው። ፱ አስካል፦ፍሬ ማለት ነው። ፲ በጽሐ፦ደረሰ ማለት ነው። ፲፩ መሐሪ፦ይቅር ባይ ማለት ነው። ፲፪ መንክር፦ልዩ ማለት ነው። ፲፫ ሥሙር፦የተወደደ ማለት ነው። ፲፬ ሐመልማል፦ለምለም ማለት ነው። ፲፭ ነጸረ፦አየ ተመለከተ ማለት ነው። ፲፮ ቅድስት፦ልዩ ምስጉን ማለት ነው፤ቅዱስ ለወንድ ፲፯ ይኄይስ፦ይሻላል ማለት ነው። ፲፰ ጥዑም፦ጣፋጭ ማለት ነው ፲፱ ግሩም፦የተፈራ ማለት ነው። ፳ ተቅዋም፦መቅረዝ ማለት ነው። ፳፩ ጸገየ፦አበበ ማለት ነው ፳፪ ደምፀ፦ተሰማ ማለት ነው። ፳፫ ጎሐጽባሕ፦የንጋት ኮከብ ማለት ነው። ፳፬ ሐዋዝ፦መልካሙ ማለት ነው። ፳፭ ሰናይ፦መልካሙ ማለት ነው።ሰናይት ለሴት ነው። ፳፮ ፈታሒ፦ፈራጁ ማለት ነው። ፳፯ መዓዛ፦ጥሩ ሽታ ማለት ነው። ፳፰ መራሒ፦መሪ ማለት ነው። ፳፱ ነጋሢ/ንጉሥ፦የነገሠ ማለት ነው። ፴ ስቡሕ፦የተመሰገነ ማለት ነው። ፴፩ ስብሐት፦ምስጋና ማለት ነው። ፴፪ ብሩህ፦የበራ ማለት ነው። ፴፫ ብርሃን፦ያው በቁሙ ብርሃን ማለት ነው። ፴፬ ትጉህ፦የተጋ ማለት ነው። ፴፭ አምኃ፦እጅ መንሻ ማለት ነው። ፴፮ ልዑል፦ከፍ ያለው ማለት ነው። ፴፯ ከሀሊ፦የሚችል ማለት ነው። ፴፰ ዳግም፦ዳግመኛ ማለት ነው። ፴፱ ማዕረር፦አዝመራ ማለት ነው። ፵ ክቡር፦የተከበረ ማለት ነው። ➹share &Join Us @ewentesfa 3.2K viewsedited 05:07