Get Mystery Box with random crypto!

ጠቅላላ እውቀት

የቴሌግራም ቻናል አርማ ewentesfa — ጠቅላላ እውቀት
የቴሌግራም ቻናል አርማ ewentesfa — ጠቅላላ እውቀት
የሰርጥ አድራሻ: @ewentesfa
ምድቦች: በጉዞ ላይ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 7.58K
የሰርጥ መግለጫ

🗣➹ #ይመልሱ_ይሸለሙ!
🗣➹ #መፅሐፍትን_ያውርዱ
👇👇👇👇👇👇
@ewentesfa
"አንባቢ አይሰርቅም" ሌባ ደግሞ አያነብም

Ratings & Reviews

2.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-29 18:49:49 5. የአበሻ አይብ:- የአበሻ አይብ ከአብዛኞቹ አይቦች የሚለየው ቅቤው የውጣለት መሆኑ ነው። አይብ በካልሲዩምና በፕሮቲን የበለጸገ ነው። እንደ አይብ አይነት የወተት ምርቶችን በበቂ መጠቀም insulin resistance (የስኳር በሽታ ዋነኛው ችግር) ይዋጋል።

6. የወይራ ዘይት:- በአንዳንድ የጤና አኳያ ሲታይ የወይራ ዘይት ፈሳሽ ወርቅ ነው ተብሎ በብዙዎች ተሰይሟል። የወይራ  ዘይት ከፍተኛ  anti inflamatory ባህሪይ አለው። ይህ ደግሞ ስኳርን እና የልብ በሽታን የሚዋጋ ባህሪይ አለው ማለት ነው።

7. ስኳር ድንች:-  ለምሳሌ ያህል በድንች ፋንታ ስኳር ድንች መብላት ደም ውስጥ ያለው ስኳር 30% ያህል ከፍ እንዳይል ያግዛል። ስኳር ድንች በበሽታ ተከላካይ ፋይበር የበለጸገ ነው። ከዛ ውስጥ 40% የሚሟሟና ኮለስተሮልን የሚቀንሱና digestion በፍጥነት እንዳይካሄድ የሚረዱ ናቸው። ሌላ ደግሞ በ ኦሬንጅና ቢጫ carotenoids የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም ሰውነታችን ለ insulin respond እንዲያደርግ ይረዳሉ። ከዛ በተረፈ በ chlorogenic acid የበለጸጉ ሲሆኑ እነሱም የስኳር በሽታ መንስኤ የሆነውን  insulin resistance ይዋጋሉ።

8. ቀይ ስጋ በመጠኑ:-  ቀይ ስጋ በ ፕሮቲን የበለጸገ እና ሰውነታችን ጮማ ከሚሆን በቂ የአካል እንቅስቃሴ ካደረግን በጡንቻ እንዲተካ ይረዳል።

     @ewentesfa  @ewentesfa
968 viewsedited  15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-29 18:49:36
#ስኳር_በሽታ_ላለባቸው_ሰዎች_8_ምርጥ_ምግቦች

1. ገብስ:-  ለምሳሌ ያህል በነጭ ሩዝ ፋንታ ገብስ መብላት ደም ውስጥ ያለውን ስኳር 70% ይቀንሳል። እሱ ብቻ ሳይሆን ገብስ በ ፋይበር የበለጸገ ስለሆነ የደም ስኳር መጠን ለሰዓታት ወይም ለረጅም ጊዜ ዝቅ ብሎ እንዲቆይ ይረዳል። ስለዚህ ገብስ ስኳር ላለበት እጅግ ምርጥ ምግብ ነው ተብሎ ይታወቃል።

2. ባቄላ እና ዘሮቹ:- ባቄላ፣ አተር እና ሽምብራ አይነት ጥራጥሬዎች አንደኛ በፋይበር የበለጸጉ ናቸው። ሁለተኛ ደግሞ በፕሮቲንም የበለጸጉ ስለሆኑ የደም ስኳር መጠንን ዝቅ አድርጎ ለመጠበቅና እንዳይርብ አስተዋጽኦ ያደርጋሉ።

3. እንቁላል(በመጠኑ):-  እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ምግብ ከመሆኑም በላይ እንቁላል የፕሮቲኖች ወርቅ ተብሎ ተሰይሟል። በቀን አንድ ወይም ሁለት እንቁላል  መብላት ኮለስትሮልንም ከፍ አያደርግም። ስለዚህ እንቁላል በፕሮቲን የበለጸገ ስለሆነ ቶሎ እንዳንራብ ይረዳል።

4. አሳ:- የስኳር በሽታ ዋነኛው መዘዝ የሚባለው የልብ በሽታ ነው። አሳ ደግሞ በሳምንት አንዴ ብቻ እንኳን መብላት ሰው በየትኛውም አይነት የልብ በሽታ የመያዙን እድል 40% ይቀንሳል።

@ewentesfa @ewentesfa
950 viewsedited  15:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-19 21:28:17
#የመሬት_መዋቅር_ምን_ይመስላል?

መሬት በመዋቅሯ ከእንቁላል ጋር ተመሳሳይ መዋቅር አላት፡፡ ውስጣዊ እና ውጫዊ ይዘቷ በአጠቃላይ በሶስት ይከፈላል፡፡ ይህም በእንቁላል አካል የውጨኛው ቅርፊት፣ የመካከለኛው ፈሳሽ እና የውስጠኛው አስኳል ብለን እንደምንከፍለው በመሬትም ተመሳሳይ አቀማመጥ ያላቸው ክፍሎች አሉ፡፡

ውጫዊ ክፍል

የመጀመሪያው ውጫዊው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ክረስት የሚባለው ሲሆን የመሬት ቅርፊት ልንለው እንችላለን፡፡ በአብዛኛው ከተለያዩ የቋጥኝ አይነቶች የተገነባ ሲሆን ህይወት ያላቸው ነገሮች በሙሉ የሚኖሩት በዚህኛው የመሬት ክፍል ላይ ነው፡፡ ይህ ክፍል ውፍረቱን በሁለት ከፍሎ ማየት ይቻላል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ በውቅያኖሶች ስር ያለው የውፍረቱ መጠን እና በአህጉራት ላይ ያለው መጠን ስለሚለያይ ነው፡፡ የመሬት ቅርፊት በውቅያኖሶች ስር ያለው ውፍረት ከ5000 ሜትር እስከ 10000 ሜትር ነው፡፡ ይህ ውፍረት በአህጉሮች ላይ ከ30 ኪ.ሜ እስከ 50 ኪ.ሜ ነው፡፡

መካከለኛው ክፍል

ሁለተኛው የመሬት ክፍል መካከለኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ማንትል በመባል ይጠራል፡፡ ይህ የመሬት ክፍል ፈሳሻማ ይዘት አለው፡፡ ውፍረቱ እስከ 2890 ኪ.ሜ ይደርሳል፡፡ የመሬትን 84 በመቶ መጠን ይሆናል፡፡ በአብዛኛው በቅልጥ አለት ወይም ማግማ የተሞላ ነው፡፡

ውስጠኛው የመሬት ክፍል

የመጨረሻው እና ሶስተኛው ደግሞ ውስጠኛው የመሬት ክፍል ወይም በእንግሊዝኛው ኮር የሚባለው ነው፡፡ በእንቁላል የውስጠኛው አስኳል መወከል ይቻላል፡፡ እጅግ በጣም ሞቃት ሲሆን የፀሐይን የውጨኛ ክፍል መጠነ ሙቀት ይኖርዋል፡፡ ይህ ክፍል መጠኑ አነስተኛ ሲሆን በራዲየስ እስከ 1220 ኪ.ሜ ብቻ ነው፡፡ በዚህም የጨረቃን መጠን 70 በመቶ ጋር ይነጻጸራል፡፡

@ewentesfa @ewentesfa
2.2K views18:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 19:24:44
የአውቶማቲክ መኪናን ጊርቦክስ ሊያበላሹ የሚችሉ ቀላል የሚመስሉ ነገር ግን አደገኛ የሆኑ 5 ስህተቶች!!

➊ D ላይ ሆኖ እየተነዳ ያለን መኪና ሙሉ በሙሉ እንቅስቃሴውን በ ፍሬን ሳያቆሙ ወደ ሗላ ለመሄድ R ማስገባት::

➋ ነዳጅ ለመቆጠብ ተብሎ ቁልቁለት ላይ መኪናውን በ N መልቀቅ::ይህ ድርጊት አሽከርካሪው መኪናውን መቆጣጠር እንዳይችል በማድረግ እንዲሁም የመኪናውን የማርሽ ታይሚንግ ዙር ሲንኮራይዚንግ በማዛባት ለ አደጋ ያጋልጣል::

➌ በ እንቅስቃሴ ላይ ያለን መኪና በቅድሚያ በፍሬን ሳያቆሙ P ማስገባት ::

➍ በረጃጅም የመንገድ መጨናነቅ (ረጅም ሠልፍ) ወቅት መኪናችንን D አድርጐ አለመጠበቅ ምክንያቱም ለከፍተኛ ሙቀት overheating ስለሚያጋልጠው በተቻለ አቅም p ላይ አድርገን መጠበቅ ተመራጭ ነው::

➎ መኪናችን N እንዳለ ከፍተኛ ነዳጅ ሰጥቶ በቀጥታ ወደ D ማስገባት ይህ የአውቶማቲክ ጥርሶችን በአንድ ጊዜ ከጥቅም ውጪ ያረጋቸዋል

➹share &Join Us

               @ewentesfa
2.6K views16:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-08 08:41:33
#መኪኖች_የተሰሩበት_ሀገር
የቀጠለ

18. ሱባሩ(Subaru)☞ ጃፓን
19. ላንድዊንድ(Landwind)☞ ቻይና
20. ዳዉ(Daewoo)☞ ደ.ኮሪያ
21. ፌራሪ(Ferrari)☞ ጣሊያን
22. ኦፔል(Opel)☞ ጀርመን
23. ጂፕ(Jeep)☞ አሜሪካ
24. ሀዩነዳይ(Hyundai)☞ ደ.ኮሪያ
25. ቡጋቲ(bugatti)☞ ፈረንሳይ
26. ቤንትሌ(Bentley)☞ እንግሊዝ
27. ሌክሰስ(lexus)☞ ጃፓን
28. ቴስላ(tesla) ☞ አሜሪካ
29. ጃጓር(jaguar)☞እንግሊዝ
30. ኡዲ(audi) ☞ ጀርመን
31. ኒሳን(Nissan)☞ ጃፓን
32. ላንድ ሮቨር(land rover) ☞ እንግሊዝ
33. ሮልስ ሮይስ(rols Royce)☞ እንግሊዝ
34.ታታ(tata)☞ ህንድ

➹share &Join Us

               @ewentesfa
2.7K viewsedited  05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-07 00:19:03
#መኪኖች_እና_የተሰሩበት_ሀገር

1. ላምበርጊኒ(lamborghini)☞ ጣሊያን
2. ቮልቮ(volvo)☞ ስዊድን
3. ሬኖልት(Renault)☞ ፈረንሳይ
4. ኪያ(kia)☞ ደ.ኮሪያ
5. ቢኤምደብልዩ(BMW)☞ ጀርመን
6. ፎርድ(ford)☞ አሜሪካ
7. ሆንዳ(honda)☞ ጃፓን
8. ሣይክ(saic)☞ ቻይና
9. ቶዮታ(toyota)☞ ጃፓን
10. ቮልስዋገን(volkswagen)☞ ጀርመን
11. መርሰዲስ(Mercedes)☞ ጀርመን
12. ፔጆ(Peugeot)☞ ፈረንሳይ
13. ጋክ ግሩፕ(GAC Group)☞ ቻይና
14. ፓርስቼ(Porsche)☞ጀርመን
15. ማዝዳ(Mazda)☞ ጃፓን
16. ሚትሱቢሺ(Mitsubishi)☞ ጃፓን
17. ዶጅ(Dodge)☞ አሜሪካ

ከወደዳችሁት ይቀጥላል......
➹share &Join Us

               @ewentesfa
2.5K viewsedited  21:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 21:04:44
#አምስት_የመብረቅ_ደህንነት_ምክሮች
1. ነቅቶ መጠበቅ
ምንም እንኳን አውሎ ነፋሱ 5 ማይል ርቀት ላይ ቢሆንም አሁንም በጠራራ ሰማይ ስር ብርሃን መፍጠር ይችላል። ነጎድጓድ ሲጮህ ወደ ውስጥ ግባ።

2. ንቀል
የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች በመብረቅ ምክንያት ለሚከሰት የኤሌትሪክ መጨናነቅ የተጋለጡ ናቸው።በተለይ ከከተማ ከወጡ ሶኬቱን ይንቀሉ ።

3. እራስዎን ያርቁ
ከመስኮቶች፣ ከበር እና በረንዳዎች ራቁ።

4. ውሃ ያጥፋ
ሁሉንም መታጠቢያዎች ፣ ሳህኖች እና ሌሎች ውሃን የሚያካትቱ ሌሎች እንቅስቃሴዎችን ማዘግየት ።

5. እርዳታ መስጠት
መብረቅ ካጋጠመው ሰው ወደ ሆስፒታል ይደውሉ። አካባቢው ግልጽ ከሆነ CPRን ማስተዳደር ደህንነቱ የተጠበቀ ነው።

@ewentesfa @ewentesfa
2.8K viewsedited  18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 19:57:04
የትኞቹ ኢትዮጲያውያን አትሌቶች የአለም ሪከርድን ሰበሩ??

የጎዳና ሩጫ ሴቶች
➊ ገንዘቤ ዲባባ 1500ሜ 3፡50.07
➋ ለተሰንበት ግደይ 5000ሜ 14፡06.62
➌ ሰንበሬ ተፈሪ 5ኪሜ 14፡29
➍ እጅጋየሁ ታዬ 5ኪሜ 14:19 Mx
➎ ለተሰንበት ግደይ 10000ሜ 29፡01.03
➏ ያለምዘርፍ የኀላው10ኪሜ 29፡14
➐ ለተሰንበት ግደይ ግማሽ ማራቶን 1፡02፡52

የቤት ውስጥ ሴቶች
➊ ጉዳፍ ፀጋዬ 1500ሜ 3፡53.09
➋ ገንዘቤ ዲባባ 1 ማይል 4፡13.31
➌ ገንዘቤ ዲባባ 3000ሜ 8፡16.60
➍ ገንዘቤ ዲባባ 5000ሜ 14፡18.86

ወንዶች የጎዳና
➊ በሪሁ አረጋዊ 5ኪሜ 12፡49
➋ ከተማ በቀለ ነጋሳ 50ኪሜ 2፡42፡07

ወንዶች የቤት ውስጥ
➊ ዮሚፍ ቀጄልቻ 1 ማይል 3፡47.01
➋ ቀነኒሳ በቀለ 5000ሜ 12፡49.60

➹share &Join Us

               @ewentesfa
3.2K views16:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-18 20:31:52
እናት ከፍ በይልን ማንም የማይተካው ከዘር ከብሔር የነፃች ድንቅ ኢትዮጲያዊት

ደራርቱ_ቱሉ

@ewentesfa @ewentesfa
3.6K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-16 23:10:52
ከዶሃ 2019 በኋላ የአለም ሪከርድ ባለቤቷ ለተሰንበት ግደይ በመጨረሻ የአለም 10,000ሜ. ሄለን ኦቢሪን እና ማርጋሬት ቼሊሞ ኪፕኬምቦይ በአለም መሪነት 30፡09.94 አሸንፋለች።

እንኳን ደስ ያለን፡፡ ምርጥ የቡድን ስራ


@ewentesfa @ewentesfa
3.4K viewsedited  20:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ