Get Mystery Box with random crypto!

ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?! ፵፩ አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው። ፵፪ ደብሩ፦ተራራ | ጠቅላላ እውቀት

ለልጆቻችሁ የግእዝ ስም ማዉጣት ይፈልጋሉ ?!

፵፩ አዕምሮ፦እውቀት ማለት ነው።
፵፪ ደብሩ፦ተራራው ማለት ነው።
፵፫ ምሥራቅ፦የፀሐይ መውጫ ማለት ነው።
፵፬ ይባቤ፦እልልታ ማለት ነው።
፵፭ ጥበቡ፦ብልሀተኛው ማለት ነው።
፵፮ ሃይማኖት፦ሃይማኖት ማለት ነው።
፵፯ ትሕትና፦ትሕትና ማለት ነው።
፵፰ ተከሥተ፦ተገለጠ ማለት ነው።
፵፱ በየነ፦ፈረደ ማለት ነው።
መኮንን፦ገዢ ማለት ነው።
፶፩ ሐዳስ፦አዲሱ ማለት ነው።
፶፪ ትንሳኤ፦መነሳት ማለት ነው።
፶፫ ሢራክ፦ብልሀተኛ ማለት ነው።
፶፬ ቡሩክ፦ምስጉን የተመሰገነ ማለት ነው።
፶፭ ህላዌ፦መኖር ማለት ነው።
፶፮ ማኅደር፦መኖሪያ ማለት ነው።
፶፯ ሕይወት፦መኖር ማለት ነው።
፶፰ ቤዛ፦መድኃኒት ማለት ነው። ቤዛዊት ለሴት ነው።
፶፱ ኄራን፦ደጋጎች ማለት ነው።
መርአዊ፦ሙሽራ ማለት ነው። መርአዊት ለሴት
፷፩ ተስፋ፦ተስፋ ማለት ነው።
፷፪ ዜናዊ፦ነጋሪ ማለት ነው።
፷፫ ጸዐዳ፦ነጭ ማለት ነው።
፷፬ ጸጋ፦ስጦታ ማለት ነው።
፷፭ ብሥራት፦የምሥራች ማለት ነው።
፷፮ ኅሊና፦ማሰቢያ፥ሀሳብ እውቀት ማለት ነው።
፷፯ ማህሌት፦ምስጋና ማለት ነው።
፷፰ ሐሴት፦ደስታ ማለት ነው።
፷፱ ፍሥሓ፦ደስታ ማለት ነው።
ትርሲት፦ሽልማት ማለት ነው። በተጨማሪ ስርጉት ማለት የተሸለመች ያጌጠች ማለት ነው።
፸፩ ምዕራፍ፦ማረፊያ ማለት ነው።
፸፪ መቅደስ፦ማመስገኛ፥ መመስገኛ ማለት ነው።
፸፫ ዋካ፦ብርሃን ማለት ነው።
፸፬ ረድኤት፦ እርዳታ ማለት ነው።
፸፭ ጽጌ፦አበባ ማለት ነው።
፸፮ ሠረገላ፦መኪና ማለት ነው።
፸፯ አማን፦እውነት ማለት ነው።
፸፰ አሜን፦ይሁንልኝ ይደረግልኝ ማለት ነው።
፸፱ ሰዋስው፦ድልድይ ማለት ነው።
ጸዳሉ፦ብርሃኑ ማለት ነው።

➹share &Join Us

              @ewentesfa