Get Mystery Box with random crypto!

#ለእርጉዝ_ሴቶች_የተከለከሉ_ምግቦች ጁስ (ፓስቸራይዝድ ያልሆነ) ጁስ መጠጣት አትክልቶች እና | ጠቅላላ እውቀት

#ለእርጉዝ_ሴቶች_የተከለከሉ_ምግቦች

ጁስ (ፓስቸራይዝድ ያልሆነ)
ጁስ መጠጣት አትክልቶች እና ፍራፍሬዎችን በምግብ ገበታሽ ውስጥ በቀላሉ የምታካትችበት መንገድ ነው ነገር ግን ሁሉም ጁሶች ለአንቺ ንጽህና ጤናማ አይደሉም። ምክንያቱም ኢሸርሺያ ኮላይ ወይም ሊስቴሪያ (E. coli or Listeria) የተባሉ ባክቴሪያዎችን በውስጣቸው ሊይዙ ስለሚችሉ ነው።

በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋ
እርጉዝ በምትሆኝበት ጊዜ ጥሬ ሥጋ እና ጥሬ የአሳ ሥጋን ቻው ብለሽ መሰናበት አለብሽ። ባክቴሪያ እና ሌሎች በሽታ አምጪ ህዋሶች በደንብ ባልበሰለ ወይም በጥሬ ሥጋ ላይ እና በባህር ውስጥ ምግቦች ውስጥ መኖር ስለሚችሉ ነው።

በበቂ ሁኔታ ያልበሰለ እንቁላል
እንቁላል የፕሮቲን፣ ቫይታሚን እና ሜኔራል መገኛ ምንጭ ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ የምትመገቢው እንቁላል በደንብ መብሰሉን ማረጋገጥ አለብሽ። በትክክል ካልበሰለ ግን ሳልሞኔላ (Salmonella) ለተባለ ባክቴሪያ የመጋለጥ ዕድል አለሽ።

ቡና
ካፌይን ትልቅ ትኩረት የምትሰጭው ጉዳይ ነው። ከፍተኛ መጠን ያለው ቡና በእርግዝና ወቅት መጠጣት ከማስጨንገፍ/ ማስወረድ ጋር ይያያዛል።

ከፍተኛ ሜርኩሪ ያለው አሳ
እርጉዝ የሆነች ሴት ከፍተኛ የሆነ ሜርኩሪ ያላቸውን አሳዎች መመገብ ማቆም አለባት። ይህ ኬሚካል በሰውነትሽ ውስጥ የመከማቸት ባህሪ ስላለው የነርቭ ሥርዓትሽን ሊጎዳው ስለሚችል ነው።

አልኮል
ብዙ ኤክስፐርቶች እንደሚስማሙት አንድ እርጉዝ የሆነች በእርግዝናዋ ወቅት የአልኮል መጠጥ መጠጣት የለባትም የዚህም ምክንያት ልጅ ላይ የሚከሰተውን ፌታል አልኮሊክ ሲንድረምን (Fetal Alcohol Syndrome) ለመከላከል ሲባል ነው።

               @ewentesfa