Get Mystery Box with random crypto!

#ለእርጉዝ_ሴቶች_የተከለከሉ_ምግቦች ጉበት ቫይታሚን ኤ ህፃኑ በማህፀን ውስጥ ለሚኖረው እድገ | ጠቅላላ እውቀት

#ለእርጉዝ_ሴቶች_የተከለከሉ_ምግቦች

ጉበት
ቫይታሚን ኤ ህፃኑ በማህፀን ውስጥ ለሚኖረው እድገት አስፈላጊ ነው። ይህን ቫይታሚን እርጉዝ ሴቶች ከፍራፍሬ፣ አትክልት፣ ሥጋ እና እንቁላል ያገኙታል። ነገር ግን ከመጠን በላይ የሆነ ቫይታሚን ኤ ለህፃኑ መጥፎ ሲሆን በወሊድ ጊዜ ችግር ያስከትላል

የወተት ምርቶች (ፓስቸራይዝድ ያልሆኑ)

እርጉዝ ሴት በቀን ከሁለት እስከ ሶስት ጊዜ የወተት ምርቶችን ማግኘት አለባት። በውስጣቸውም ካልሲየም፣ ፕሮቲን እና ቫይታሚን ዲ ሲይዙ የሚወለደውን ህፃን ታዳጊ አጥንት፣ ጥርስ፣ ልብ እና ነርቭ በመገንባት ይጠቅማሉ። ነገር ግን ሁሉም የወተት ምርቶች ለአንቺ ምግብነት መልካም አይደሉም ስለዚህ ጥሬ ወተት እና ሌሎች ጥሬ የወተት ምርቶችን መጠቀም የለብሽም።

በሂደት ያለፈ ሥጋ (Processed Meat)

በፍጥነት የሚደርስ እና ቀላል ምግብ መመገብ ስናስብ የአብዛኛዎቻችን ምርጫ ሳንድዊች ነው። ነገር ግን እርጉዝ ከሆንሽ ሳንዱዊቹ ከምን ከምን እንደተሰራ በቅርበት መመልከት አለብሽ። ምክንያቱም ሊስቴሪያ ለተባለ ባክቴሪያ ሊኖረው ይችላል የሚል ስጋት ስላለ ነው። ይህ ባክቴሪያ በጣም በቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ እድገቱን የሚቀጥል ብቸኛ ባክቴሪያ ነው።

ሳላድ

ሳላድ ከትኩስ አትክልትና ፍራፍሬ የሚዘጋጅ ነው። ይህም ቁጥር አንድ ተመራጭ ጤናማ ምግብ ያደርገዋል። ነገር ግን በአትክልት ቤት፣ ጁስ ቤት እና ካፍቴሪያ ውስጥ ሳላድ መመገብሽን አቁሚ ምክንያቱም አትክለቶቹ የሚቀመጡበት የሙቀት ሁኔታ፣ የተዘጋጁበት ሰዓት የምግቦቹን ለጤና ተስማሚነት ስለሚወስን ነው። ስለዚህ በቤትሽ ውስጥ ሰርተሽ መመገቡ ተመራጭ ነው።

@ewentesfa @ewentesfa