Get Mystery Box with random crypto!

#LWEQESH-Ethiopia

የቴሌግራም ቻናል አርማ lweqesh_events — #LWEQESH-Ethiopia L
የቴሌግራም ቻናል አርማ lweqesh_events — #LWEQESH-Ethiopia
የሰርጥ አድራሻ: @lweqesh_events
ምድቦች: በጉዞ ላይ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 3.99K
የሰርጥ መግለጫ

ልወቅሽ የተለያዩ በሀገራችን ውስጥ ያሉ ነገርግን ያልታዩ እና ያልተዳሰሱ ታሪኮችን፣ ተፈጥሮአዊ መልክኣ ምድረዎችን እናማህበረሰቦችን አጠር በለ መልኩ የሚዳስስ ሲሆን በተጨማሪም ጉዞዎችን እንዲሁም ልዩ ዝግጅቶችን ያዘጋጃል ።"የለንን በማሳወቅ ሀገራዊ እሴትን እንገንባ !!!!!"ዕሮብ እና ቅዳሜ ፪ሰአት ይጠብቁን ለበለጠ መረጃ
@Bersihailu ፥ @fikirhailu ፥ @LWEQESH_Events

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-31 20:47:17
ጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ

የተፈጥሮን ሚዛንን ከሚጠብቁ ተፈጥሮአዊ ፀጋዎች መካከል እፅዋት ዋነኞቹ ናቸው።በሀገራችን ከሰሃራ በረሃ የሚመጣውን ሞቃታማ አየር ከሚገቱ ና በደን የተሸፈኑ አካባቢዎች በሀገራችን ሰሜናዊ ክፍል የሚገኘው የጎደቤ ብሔራዊ ፓርክ አንዱ ነው።
ፓርኩ 18987 ሄክታር የሚሸፍን ሲሆን ውብ ከሆነ የመልካምድር አቀማመጡና እንደ ዘብ ከቆሙ ተራራዎች ልዩ ውበት ተችሮታል።
በውስጡ ከ27 በላይ የዱር እንስሳት ከ57 በላይ የወፍ ዝርያዎች እንዲሁም እየተመናመነ የመጣውን የእጣን ዛፍ ለቅርፃ ቅርፅ መስሪያ አስተዋፅኦ ያለውን የቆላ ቀርከሃ ና ከ81 በላይ እፅዋትን የያዘ ነው።
@LWEQESH_Events
130 viewsሚክሎል, 17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:08:52
ውበት እንደተመልካቹ!!!

ውበት እንደተመልካቹ ሲልቅም ማህበረሰብ እንደዳበረበትና የባህል እይታ የተወሰነ ይሆናል።
በመካከለኛው አፍሪካ በምስራቅ ኮንጎ በማንግቤቱ ማህበረሰብ ዘንድ ውበትን ለማጉላትና ደምቆ ለመታየት የሚጠቀሙት መንገድ ከተለምዶ ለየት ያለ ነው።

ይህም በማህበረሰብ ዘንድ ትልቅ እና ሾጣጣ ጭንቅላት የውበት የእውቀት እንዲሁም የክብር መገለጫ መሆኑ ሲሆን ቅርፁን ለማምጣት አንድ ህፃን ከአራስነት ጀምሮ አናቱን በጨርቅ በመጠምጠም ሾጣጣ ያደርጉታል።ሂደቱም ልፖምቦ በመባል ይታወቃል።
@LWEQESH_Events
464 viewsBersi "Lucky", 17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 20:33:19
ከሴ(ከስየ) አጨዳ በአል
ቀዝቃዛ ክረምት ነሀሴ ሲጋመስ ሁሌም የልጃገረዶች ባህላዊ ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።እነዚህ ቱፊታዊ በአሎች በሀገራችን በድምቀት ከሚከበሩ በአሎች መካከልም ይካተታሉ።በአሎቹ ልጃገረዶች በተለየ መልኩ በጌጣጌጦች አምረው እና ተውበው ከማንኛውም ተፅእኖ ነፃ በመሆን ያለምንም ክልከላ ከእድሜ እኩዮቻቸው ጋራ ነፃነታቸውን የሚያውጁበት ሲሆን በሀገራችንም የተለያየ ስያሜ ይሰጣቸው እንጂ ሁሉም አላማቸው ሴቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።ከነዚህም ሻደይ፣አሸንዳ፣አሸንድየ፣ሶለን፣ከሴ(ከስየ) አጨዳ በአል ይካተታሉ።ዛሬ ከሴ(ከስየ) አጨዳ በአል ልናስቃኛቹ ወደድን።በአሉ በየአመቱ ነሀሴ 16(፲፮) ቀን ሴቶች ልጃገረዶች በባህላዊ ልብስ እና ጌጣጌጥ ተውበው ከሴ የተሰኘውን የተክል አይነት ከሜዳ ቆርጠው ያመጣሉ።ከዛም ለበአሉ ተብሎ የሚዜም ዜማ እያዜሙ ለጎረቤቶቻቸው የከሴ ተክልን እንደ ስጦታ እያደሉ እንኳን አደ
ረሳቹ ይላሉ። ከሴ ደግሞ ጥሩ መአዛ ያለው ተክል ስለሆነ ሰዎቹ እየተቀበሉ ተክሉን ለተለያየ አላማ ይጠቀሙታል። እንዲህ በማድረግ በአሉን ያሳልፋሉ።ነገር ግን ይህ በአል እየደበዘዘ የመጥፋት አደጋ ስለተጋረጠበት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።
ልወቅሽ ኢትዮጵያ https://t.me/LWEQESH_Events
751 viewsሚክሎል, 17:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-17 19:58:56
የዝናብ ነገስታት
ጫምሲቱዎች በሀገራችን መንፈሳዊ በሆነ ጥበብ ዝናብን የሚቆጣጠሩ ሰዎች ናቸው።በተመሳሳይ ከሀገረ ደቡብ አፍሪካ ይህን በመሰለ ጥበብ የተካኑ ሰዎች ሲኖሩ ይህን አይነት ጥበብ የታደሉት ደግሞ ሴቶች ናቸው።
የባሎቤዱ ማህበረሰብ እነዚህን ሴቶች ዝናብን የመቆጣጠር እና የማዘዝ ሀይል አላቸው ብለው ያምናሉ።የአስተዳደሩንም ስርአት እነዚሁ ሴቶች ብቻ ይዘው ከትውልድ እየተላለፈ መጥቷል።
ስልጣኑ የሚተላለፈው ንግስቷ መሞቻዋ ሲቃረብ ይህ መንፈስ ላደረባት የንግስቲቱ ሴት ልጅ ከሌለችም ለቅርብ ዘመድ ስልጧኗን በማውረስ እሯሷን ታጠፋለች።
ከ1800 ዓም  በፊት ወንዶች የአስተዳደር ስርአቱን ሊቆጣጠሩ ቢሞኩርም ሴቶች ብቻ ስልጣኑን ይዘው ቆይተዋል።ለምሳሌ በቅርብ ዘመን የነበረች እና ከፕሬዝዳን ኔልሰን ማንዴላ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራት (Mokope Modjadjiv) ትባላላች።
@LWEQESH_Events
804 viewsሚክሎል, 16:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-13 20:06:17 ጫምሲቱ
ጫምስቲ በኦሮምኛ ቋንቋ ዝናብ የሚያቆም ማለት ነው።ይህ ስያሜ ከተፈጥሮ ለየት ባለ መልኩ አንዳንድ ዝናብ እንዳይዘንብ የሚያደርጉ አልያም ከዘነበ በኋል እንዲቆም ማድረግ የሚያስችል ስልጦን ወይም እውቀት አላቸው ተብሎ ለሚታመን ሰዎች የሚሰጥ ሲሆን በውርስም በመማርም ሊገኝ ይችላል።
ይህንን በሚያደርጉበት ወቅት እርሾ ያልገባበት ቂጣ ሲመገቡ ለዚሁ ተግባር ብቻ የሚውል ቅጠል ቋጥኝ ላይ በማስቀመጥ ለረጅም ሰአት እራሳቸው ብቻ የሚረዱትን ፀሎት ይደግማሉ።
በተጨማሪ በደዌ ምክንያት ጫምሲቱ የሚሆኑ ሲኖሩ ጋፎ ይሰኛሉ።ዝናብ ሲመጣ ህመሙ ይነሳብናል ብለውም ስለሚያስቡ ዝናቡ እንዳይዘንብ ያደርጋሉ ተብሎ ይታመናል።
@LWEQESH_Events
936 viewsሚክሎል, 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-06 19:59:57
ሮዋ የመኢኒት ብሔረሰብ የለቅሶ ስርአት
የመኢኒት ማህበረሰብ በቤንች ማጂ ዞን የሚገኙ ከደቡብ ኦሞ ወንዝ ፈልሰው የመጡ ህዝቦች ናቸው።እነዚህ ህዝቦች ካላቸው ለየት ያሉና ትልቅ ቦታ ከሚሰጣቸው ባህሎች መካከል ለለቅሶ የሚድረግ ስርአት ነው።ስርአቱ በእድሜ ክልልና በማህበራዊ ስልጠና የተለያየ ሲሆን ለአዋቂዎች የሚደረገው ከህፃናትና ከወጣቶች የተለየ ነው።በመሆኑም አዋቂ ከሆነ የሞተው ትልቅ ድግስ ተደግሶ እየተበላ እየተጣ ለቅሶው ይካሄዳል።በተጨማሪም በድንጋይ እየተቀጠቀጠ በሬ፣ኮርማና ጥጃ ይገደልና ለቀስተኛ ስጋውን እየበሉ ወደ ቀብሪ ቦታው ያመራሉ።ቀብሩ የሚፈፀመው ተቀጥጦ በተገደለው በሬ ቆዳ ተከፍኖ ነው።በተጨማሪም ለቅሶው በዘፈን እና በተለያዩ የሙዚቃ መሳሪያዎች በመታገዝ ስርአቱ ይፈፀማል።
@LWEQESH_Events
1.2K viewsሚክሎል, 16:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-03 20:00:54
አባባ ተስፋዬ(የኢትዮጵያ የልጆች አባት)
በሙሉ ስማቸው ተስፋዬ ሳህሉ በኢትዪጵያ ልጆችን ማዕከል ያደረገ መርሃግብሮችን በማዘጋጀት እና ለ41(፵፩) አመታት ያለመታከት ያደረሱ ናቸው።ትውልዳቸው በ1916 አ.ም ሰኔ 20 ቀን በባሌ ኮዳ በምትባል መንደር ሲሆን በጎባ ከተማ በቄስ ት/ቤት ፊደል ቆጥረው በኮከበ ፅባህ ት/ቤት።አዲስ አበባም ሲገቡ ገና የ14 አመት ታዳጊ ነበሩ።የጣልያንኛ እና የፈረሳይኛ ቋንቋ ይችሉ ስለነበረ በአስተርጓሚነት እንዲሁም በእትጌ ሆቴል(ራስ ሆቴል) ይሰሩ ነበር።የኪነጥበብን ዘርፍ የተቀላቀሉት በ1937 በማዘጋጃ ትያትር ቤት ሲሆን በ1948 በተከፈተው የብሔራዊ ትያትር ቤትን ተቀላቅለዋል።በዛም ከ70 በላይ ቲያትሮች ላይ ተሳትፈዋል።ሌላው ደግሞ በዘመኑ ሴት ተዋናዮችን ማግኘት ከባድ ስለነበር የሴት ገፀባህሪን ተላብሰው ተጫውተዋል።ኮሪያ በዘመተው የቃኘው ሻለቃ ጦር ቡድንም አባል ነበሩ።የውዝዋዜ አሰልጣኝ ደራሲ የልጆች መፅሐፍት አዘጋጅ ዜማና ግጥም ደራሲ ወዘተ የእርሳቸው ሙያዎች ናቸው።እኚህ ታላቅ አባት በ93 አመታቸው በ2009 ሐምሌ 24 ቀን ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል።
@LWEQESH_Events
1.2K viewsሚክሎል, 17:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-30 20:37:08
ሀፍለታ ሻሂ
በሀገራችን የተለያየ አይነት የመረዳጃ ማህበራዊ ድርጅቶች ሲኖሩ በደስታም በሀዘንም ሁሉን የበኩልን አስተዋፅኦ ያደርጋል።በበርታ ማህበረሰብም ሀፍለታ ሻሂ/የሻይ እንጠጣ የተባለ ፕሮግራም በህብረተሰቡ የተለመደ የመረዳጃ ማህበር ነው።ማህበሩ አንድ ሚስት ለማግባት የሚጣል ለጥሎሽ የሚከፈል ገንዘብ እጥረት ሲኖር፣በማንኛውም ምክንያት ለረጅም ሆነ ለአጭር ጊዜ ቦታ ለመቀየር ገንዘብ ሲቸግር ከቤተሰብ እና ቅርብ ዘመድን ጋር በመሰባሰብ ሻይ እና የተለያዩ ነገሮቹን በማዘጋጀት መክረው ገንዘብ የሚሰበስቡብት እና አስፈላጊውን የሚያደርጉበት ማህበር ነው።በተጨማሪም ይህ ማህበር እርዳታ ለጠየቀ ብቻ ሳይሆን በጓደኞች እና በጎረቤቶች ተነሳሽነት ሊካሄድ ይችላል።በዝግጅቱም ወቅት ጭፈራና ዘፈን ስለሚኖር ለመተጫጨት ይጠቅማል።
@LWEQESH_Events
1.2K viewsሚክሎል, 17:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-27 20:06:51
የዲዚ ማህበረሰብ
የዲዚ ማህበረሰብ በደቡብ ኢትዮጵያ ማጂ ወረደ የሚገኙ ኑሮአቸውን በግብርና ላይ ያደረጉ የኦሞቲክ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ናቸው።ማህበረሰብ በዘመናት ሂደት የራሱን ባህል እና የኑሮ ዘዴ ያዳበሩ ሲሆን በተለያየ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የራሳቸውን አፈታሪክ አዳብረዋል።ከነዚህም ስለሞት የሚነገረውን አፈታሪክ ነው።አፈታሪኩ ጥንት በዲዚዎች ምድር ሰማይና ምድር የተቀራረበ ደስታ የሞላበት እና ሞት የማይታወቅበት ቦታ ነበር።ነገር ግን እንግዳ ሰዎች መጥተው ክፉ ነገር እነሱን በማስተማራቸው ሰማይ ምድር ተራርቀው ሞት በምድሪቱ ነገሰ ብለው ይተርካሉ።
በተጨማሪም በማህበረሰብ ናሊ የተሰኘ የጓደኝነት አመሰራረት ስርአት ሲኖራቸው በተመሳሳይ ፆታዎች መካከል የጠበቀ ወዳጅነት ከዛም አልፎ እንደ ስጋ ዝምድና ለመመስረት ሲፈለግ የሚደረግ ስርአት ነው።
@LWEQESH_Events
1.3K viewsሚክሎል, 17:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-07-23 20:09:13
የጥርስ ነቀላ(የኬት) ስነስርአት በመኢኒት ማህበረሰብ
እንደማህበረሰብ ገለፃ መኢኒት ማለት ሰው ነኝ ማለት ነው።ማህበረሰብ በደቡብ ብሔረሰብ በቤንች ማጂ ዞን ሲገኝ የአካባቢው ተወላጆች እንደሚጠቅሱትም ከደቡብ ኦሞ ወንዝ ፈልሰው እንደመጡ ይነገራል።
በማህበረሰብ አስገራሚ ከሆኑ ባህሎች መካከል የጥርስ ነቀላ ወይም የኬት ስነስርአት ነው።የጥርስ ነቀላ አንድ ጎረምሳ ወይም አንዲት ኮረዳ ለጋብቻ መድረሳቸውን የሚያመለክት ክብረበአል ነው።በዚህ መሰረት አንድ ሰው ወደወጣትነት የመሸጋገር ባህሪ ወይም የሰውነት አካል ለውጥ ሲያመጣ ሁለት የታችኛውን የፊት ጥርስ በማውለቅ ለጋብቻ መድረሱን/መድረሷን ያሳውቃሉ።
ለስርአቱ ድምቀትም ወጣቶች የተለያዩ ባህላዊ ዘፈን እና ጭፈራ በመጫወት እንዲሁም ቫሉ የተሰኘ ባህላዊ መጠጥ በማዘጋጀት ደስታቸውን ይገልፃሉ።
@LWEQESH_Events
1.4K viewsሚክሎል, 17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ