Get Mystery Box with random crypto!

ኮረማሽ - Koremash

የቴሌግራም ቻናል አርማ koremashtourassociation — ኮረማሽ - Koremash
የቴሌግራም ቻናል አርማ koremashtourassociation — ኮረማሽ - Koremash
የሰርጥ አድራሻ: @koremashtourassociation
ምድቦች: በጉዞ ላይ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 1.60K
የሰርጥ መግለጫ

251 993 949053
koremashtourassociation@gmail.com
https://t.me/joinchat/LDiPKN1nSKs3Yzk0

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-27 19:36:33 እንዴት አመሻችሁ!

ለተጨማሪ ማሳሰቢያ ተመልሰናል!

ነገ ጠዋት ከጣይቱ ሆቴል የሚነሱ ሌሎች የጉዞ አዘጋጆች ስለሚኖሩ ምናልባት ከሌሎቹ አዘጋጆች ጋር ተመሳሳይ የሆነ መኪና ልንጠቀም ስለምንችልና የጉዞ መደበላለቅ እንዳይፈጠር እኛ የምንጓዝበት ቢጫ የሬይንቦው  የትራንስፖርት አውቶብስ  የሠሌዳ ቁጥሩ  ኮድ 3- A59065 መሆኑን እንገልፃለን።

መልካም ምሽት!
166 viewsኮረማሽ, 16:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-26 10:58:54 እንዴት ናችሁ!

  የፊታችን እሁድ ነሐሴ 22 ቀን ወደ ገማሳ ገደል (የምኒልክ መስኮት) በምናደርገው ቀላል የእግር ጉዞ (Hiking) ፕሮግራም ላይ አብራችሁን የምትጓዙ ቤተሠቦቻችን!

*  በዕለቱ ከእናንተ የምንጠብቃቸው ነገሮች....

*  ከአዲስ አበባ የመነሻ ሠዓታችን ከጠዋቱ 12:30 በመሆኑ ይህንኑ አውቀን ከመነሻ ሰዓታችን ቀደም ብለን ከጣይቱ ሆቴል (ፒያሳ) ላይ እንድንገኝ ይሁን።

*  ለጉዞ የሚሆን በጀርባ የሚታዘል ቦርሳ

*   ወቅቱ የክረምት ወራት እንደ መሆኑ መጠን ዝናብ ሊኖር ስለሚችል የዝናብ መከላከያ አልባሳትን ወይም ዣንጥላ መያዝ እንዲሁም መዳረሻችን እጅግ ቀዝቃዛ የአየር ንብረት ስላለው ቅዝቃዜውን ለመከላከል የሚረዱ ልብሶችና የእጅ ጓንት ስካርፍ ኮፍያ የመሳሰሉትን በቦርሳችን ብንይዝ

*  በተጨማሪም በጉዟችን ላይ እርጥበታማ እና የሚያዳልጥ መንገድ ሊያጋጥመን ስለሚችል ለዚህ አይነት ጉዞ የሚሆንና ሶሉ የሚቆነጥጥ ለእግራችን የሚመቹ ሙቀት  ጫማዎችን እንድናደርግ ይመከራል።

*   ተጓዦቻችን በጉዞ ላይ እያሉ ሊመገቧቸው የሚችሉ ቀለል ያሉ የጉዞ ምግቦችንና መጠጦችን በግላቸው ይዘው መምጣት ይችላሉ።

ማሳሰቢያ :-  ማርፈድ አይፈቀድም

በተጨማሪም ተጓዦች ማንነታቸውን የሚገልፅ መታወቂያ መያዛቸው እንዳይረሳ ስንል ለማሳሰብ እንወዳለን።

በቸር እንገናኝ!

ለመረጃ በ0993949053 መደወል ይችላሉ!
326 viewsኮረማሽ, 07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 12:00:46 ኮረማሽ - Koremash pinned a photo
09:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 11:59:44
ትንሽ ስለ ገማሳ ገደል



ከደብረ ብርሃን ከተማ በስተሰሜን አቅጣጫ 40 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል።

ጥድ እና ጅብ ዋሻ የሚባሉ አካባቢዎች የሚያዋስኑት ትልቁ የስምጥ ሸለቆ በሚያልፍበት አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ መስህብ ነው የምኒልክ መስኮት፡፡

ይህ ድንቅ ስፍራ ስያሜውን ያገኘው አጼ ምኒልክ ወደዚህ ስፍራ በተደጋጋሚ እየተገኙ ይጎበኙት ስለነበር እንደኾነ ታሪክ ያስረዳል፡፡

አጼ ምኒልክ መቀመጫቸው አንኮበር በነበረበት ጊዜ ወደ ደብረሲና ዘመድ ለመጠየቅ ሲያልፉ ይጎበኙት እንደነበር እና ጠላትንም ይቆጣጠሩበት የነበረ ወሳኝ ቦታ ነው፡፡

የምኒልክ መስኮት ሥፍራ ላይ ሲገኙ ማራኪ አየር በጉም የተሸፈነ ስፍራ እና ለጎብኝዎች ቀልብን የሚስብ ስፍራ መኾኑን ይገነዘባሉ፡፡

በምኒልክ መስኮት አሻግረው ካዩ እስከ አዋሽ ሰባት ድረስ ያሉ ማንኛውንም ጉዳዮች ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ቦታ ነው፡፡

አካባቢው በርካታ ጎብኝዎችም የሚጎበኙት ድንቅ ስፍራም ነው፡፡

አካባቢው ላይ ጭላዳ ዝንጀሮዎች በሰፊ የሚታዩበት፤ አንኮበር ሳይድ የተባለች ልዩ ወፍም የምትገኝበት ነው፡፡

ሥፍራው አምስት ወረዳዎችን ማለትም፦ ጣርማ በርን፣ ቦሰና ወረናን፣ አንኮበርን፣ መንዝ ማማ ምድርን እና መንዝ ጌራን የሚያካልለውን የወፍ ዋሻን በከፊል የያዘ ነው፡፡
904 viewsኮረማሽ, 08:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-20 11:04:19
ለፆም ፍቺ ለክረምቱ መገባደጃ እና ለአዲሱ አመት መቀበያ ያዘጋጀነው ውብ የጉዞ ፕሮግራም ወደ ንጉሰ ነገስቱ ከተማ የምኒልክ መስኮት ልንገሰግስ ቀናቶች ቀርተውናል ። ባሉን ውስን ቦታወች ቀድመው ይመዝገቡ

በጥሬ ስጋ እና በሰሜን ሸዋ ባህላዊ መጠጦች የማይረሳ ጊዜ አሳልፈው ይመለሳሉ

0993949053 ይደውሉ
642 viewsኮረማሽ, 08:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-16 13:49:16
ሠላም ቤተሠቦቻችን!

ከቀጣዩ የውሎ ገብ የHiking ፕሮግራማችን ጋር ተመልሰናል!

  ቀጣይ መዳረሻ ገማሳ ገደል (የምኒልክ መስኮት)

  እሁድ ነሐሴ 22 ቀን 2014 ከአዲስ አበባ በስተሠሜን 160 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው ገማሳ ገደል (የምኒልክ መስኮት) ጀማሪ ተጓዦችን ያማከለ ቀለል ያለ የእግር ጉዞ (hiking) ፕሮግራም ተወዳጅ ከሆነው የደብረ ብርሃን የጥሬ ስጋ ቁርጥና ባሕላዊ መጠጦች ጋር አዘጋጅተናል።

የጉዞ አይነት

ቀለል ያለ የእግር ጉዞ

(ጀማሪ ተጓዦች ሊሳተፉበት የሚችል)

  በመሆኑም የተፈጥሮና የእግር መንገድ ወዳጆች በዚህ ጉዞ ላይ አብራችሁን እንድትሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን።


ጉዞው ውስን ሰዎችን የሚያሳትፍ ብቻ በመሆኑ በፕሮግራሙ ላይ ለመገኘት ቀድመው እንዲመዘገቡ እንመክራለን ።

የጉዞ ዋጋ

  ከፒያሳ ጣይቱ ሆቴል ገማሳ ገደል የደርሶ መልስ ትራንስፖርት ቀለል ያለ ቁርስ ምሳ (የቁርጥ ስጋ እና ባሕላዊ መጠጦች) የታሸገ ውሃ እንዲሁም የአስጎብኚ ክፍያን ጨምሮ:

ብር 1650

ለበለጠ መረጃ 0993949053 ይደውሉ!
763 viewsRas Mule, 10:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 21:32:45 ኮረማሽ - Koremash pinned a photo
18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 20:14:42
988 viewsኮረማሽ, 17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ