Get Mystery Box with random crypto!

etv zena

የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_zena_57 — etv zena E
የቴሌግራም ቻናል አርማ etv_zena_57 — etv zena
የሰርጥ አድራሻ: @etv_zena_57
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ሀገር: ኢትዮጵያ
ተመዝጋቢዎች: 6.73K
የሰርጥ መግለጫ

For any comment @etv_zena_57_bot

Ratings & Reviews

4.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2020-06-27 08:19:56
GERD ?

የግብፅ ሚዲያዎች እንዲሁም AFP ፣ አልጀዚራ ፣ ሮይተርስ (ሮይተርስን ዋቢ አድርገው ደግሞ ሌሎች በርካታ የውጭ ሚዲያዎች) በሰበር ዜናቸው ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ስምምነት ላይ እስኪደረስ ድረስ አራዝማለች / ከስምምነት በፊት የውሃ ሙሌት ላለመጀመር ተስማምታለች እንዲሁም የኢትዮጵያ ፣ የሱዳን እና ግብፅ መሪዎች በሁለት (2) ሳምንት ውስጥ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ የውሃ ሙሌቱ እንዳይጀመር ተስማምተዋል የሚሉ ዘገባዎችን አውጥተዋል።

ይህ ፅሁፍ የተፃፈው ከለሊቱ 8:40 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ነው፤ መረጃዎች መሰራጨት የጀመሩት ከለሊት 6 ሰዓት በኃላ ቢሆንም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም አልተባለም። ማብራሪያም አልተሰጠም!

በርካታ የሀገራችን ዜጎችን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት፣ እውነቱን ለማወቅ ፣ በግብፅ ሚዲያዎች የሚነገረውን ለማረጋገጥ በዚህ ለሊት ማህበራዊ ሚዲያውን እያተራመሱት ነው።

በጉዳዩ ላይ ስጋት ያደረባቸው ፣ ያሳሰባቸው በርካታ የቤተሰባችን አባላት የደወሉልን ሲሆን ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ብለን ወዳሰብናቸው ሰዎች ስልክ ብንሞክርም ልናገኛቸው አልቻልንም።

ውድ የቲክቫህ አባላት ነገ በጉዳዩ ላይ በመንግስት በኩል የሚሰጠውን ማብራሪያ ተከታትለን እናሳውቃለን፤ በድጋሚ ሰላም እደሩ
4.1K viewsedited  05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-27 08:19:56
ህይወታቸው ያለፈ 8 ሰዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦

1. የ40 ዓመት ወንድ የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ፤ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

2. የ26 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ በህክምና ማዕከል በህክምና ላይ የነበረ።

3. የ70 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ በጤና ተቋም በህክምና ላይ የነበሩ።

4. የ80 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

5. የ27 ዓመት ሴር የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባት የተረጋገጠ።

6. የ65 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

7. የ65 ዓመት ወንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።

8. የ60 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ፤ ከአስክሬን ላይ ከተወሰደ ናሙና ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጠ።
3.8K viewsedited  05:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 12:04:46

አሁን የsex ቻልና ነው ቢባል ሁሉም JOIN ያደርግ ነበር
ማሪያምን ዝም ብላቹ join በሉ ፈታ ነው ም ትሉት እመኑኝ አንዴ ብቻ ጠቅ አረጓት።

3.5K views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 10:56:32
ኮቪድ-19 ባለፋት 24 ሰዓት በአሜሪካና ብራዚል!

እንደ #worldometers መረጃ ባለፉት 24 ሰዓት በአሜሪካ 38,386 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ808 ሰዎች ህይወት አልፏል።

በብራዚል ደግሞ 40,995 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያቸው ሲረጋገጥ የ1,103 ሰዎች በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸው አልፏል።
3.4K viewsedited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 10:56:32
የትራምፕ ደህንነት አባላት ኮቪድ-19 ተገኘባቸው!

ባለፈው ቅዳሜ ቱልሳ ውስጥ የተካሄደው የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ የተገኙ የደኅንነት አባላት ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተሰምቷል።

የደህንነት አባላቱ ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡት ከመካከላቸው የተወሰኑት የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስለተገኘባቸው መሆኑ ተገልጿል።

መረጃውን መጀመሪያ ያወጣው ዋሽንግተን ፖስት ሲሆን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፖሊስ ባለሥልጣን ደግሞ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት በጣት የሚቆጠሩ አባላት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከምርጫ ቅስቀሳው በፊት የፕሬዝደንት ትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን አባላትና ሁለት የደኅንነት ሰዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተዘግቦ ነበር።

ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ባልተገታባት ኦክላሆማ ግዛት የምርጫ ቅስቀሳ አደርጋለሁ ሲሉ ብዙ ወቀሳ ገጥሟቸው ነበር።

በስብሰባው ቦታ የተገኙት ታዳሚዎችም ሙቀታቸው ተልክቶ እንዲሁም የእጅ ማፅጃ ፈሳሽ ተሰጥቷቸው ቢገቡም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ አልነበረም።

የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አንድ ሚሊዮን ሰዎች ለመታደም ቃል ገብተዋል ብለው የነበረ ቢሆንም 19 ሺህ ሰው በሚይዘው ስታደየም የተገኙት 6,200 ሰዎች ብቻ ነበሩ ሲል #BBC አስነብቧል።
3.4K viewsedited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-26 10:56:32
የቤት ለቤት ልየታ በአዲስ አበባ!

የአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የኮቪድ 19 ቫይረስ ወረርሽኝ የቤት ለቤት ልየታና ግንዛቤ ማስጨበጥ መርሐ ግብር በሁለት ዙር ከአምስት ሚሊዮን በላይ ግለሰቦችን ተደራሽ ማድረጉን ኢፕድ ዘግቧል። በሁለት ዙር በተከናወነው ልየታም በምርመራ 13 ግለሰቦች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ቢሮው አስታውቋል።
3.1K viewsedited  07:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-25 11:51:11
ሸገር ዳቦ : 2 ሚሊዮን ዳቦ በአንድ ቀን
2 ሚሊዮን ዳቦ በአንድ ቀን የሚያመርተው ሸገር ዳቦ ማምረቻ ግንባታው ተጠናቆ ዛሬ ይመረቃል
ዛሬ - ኢንጂነር ታከለ ኡማና ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እንዲሁም ልዩ ልዩ ባለስልጣናት በተገኙበት ይመረቃል።
3.2K viewsedited  08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-25 11:51:11
37 የኮሮናቫይረስ ታካሚዎች ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል አገግመው ወጡ።

በኮሮናቫይረስ ተይዘው በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማዕከል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸውን ሆስፒታሉ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።
በቫይረሱ ተይዘው የመጡ ህሙማን ቁጥር በአጠቃላይ 178 መሆኑን ያስታወቀው ሆስፒታሉ በመጀመሪያው ዙር 44 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸውን ተከትሎ፤ በአጠቃላይ ከማዕከሉ አገግመው የወጡ ሰዎች ቁጥርም 81 ደርሷል።

ከዚህም በተጨማሪ ሆስፒታሉ በፌስቡክ ገፁ ላይ እንዳሰፈረው የኮሮናቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ 205 ግለሰቦች መካከልም 144ቱ ነፃ ተብለው ወደ ቤታቸው ተሸኝተዋል። በሃገሪቱ ውስጥ በቫይረሱ ከተያዙት 4 ሺህ 848 ሰዎች መካከል1 ሺህ 412 አገግመዋል።
3.1K viewsedited  08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-25 11:51:11
የ186ቱ ታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገ 4034 የላቦራቶሪ ምርመራ 186ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 5,034 ደርሷል።

የታማሚዎችን ሁኔታ ስንመለከት
-181 ኢትዮጵያውያን እና 5 የውጪ ዜጎች ሲሆኑ 73ወንድ እና 113ሴት ናቸው። እድሜያቸው ከ6ወር-75 አመት መሆናቸው ተገልጿል።

የመኖሪያ ቦታቸውን ስንመለከት
_
•147ሰዎች- ከአዲስ አበባ
•16ሰዎች- ከሱማሌ ክልል
•4ሰዎች -ከኦሮሚያ ክልል
•10ሰው - ከአፋር ክልል
•8ሰዎች- ከድሬዳዋ
•1ሰው- ከደቡብ ክልል

በሌላ መልኩ በትላንትናው ዕለት ሰባ አራት (74) ሰዎች (63 ከአዲስ አበባ፣ 6 ከትግራይ ክልል፣ 2 ከሶማሊ ክልል፣ 2 ከደ/ብ/ብ/ሕ ክልል፣ እና 1 ሐረሪ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 1486 ነው።
3.0K viewsedited  08:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2020-06-24 08:44:35
በቤት ውስጥ የኮቪድ-19 በሽታ ህክምና አገልግሎት ለማግኘት የሚያስችሉ መስፈርቶች የሚከተሉት ናቸው፦

1. በቤት ሆኖ የኮቪድ-19 ህክምና ለማግኘት ፍቃደኛ የሆነ፣

2. ቀላል ወይም ምንም አይነት የኮቪድ-19 ምልክት የሌለበት፣

3. በቤት ውስጥ የቆይታ ጊዜ አጋዥ ወይም ረዳት ያለው እንዲሁም እራሱን መርዳት የሚችል፣

4. የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶችን ማግኘት ወይም ማሟላት የሚችል፣

5. በተመሳሳይ ቤት ውስጥ የሚኖር ሌላ ሰው የግል ንፅህና መጠበቂያዎችን እንዲሁም የአፍና የአፍንጫ ማሸፈኛ ጭንብሎችን ማግኘት የሚችል እንደሆነ፣

6. ኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከሌሎች ተዷጋኝ በሽታዎች ማለትም የልብና የደም ቧንቧ በሽታ ፣ የስኳር በሽታ፣ አስም፣ ኤች አይቪ፣ ቲቢ፣ ካንሰርና የመሳሰሉት በሽታዎች ካሉባቸው ሰዎች ጋር አብሮ የማይኖር ከሆነ፣

7. የኮቪድ-19 የተገኘበት ሰው ከቤት ላለመውጣት ወይም ማናቸውም ጠያቂ ወደቤት እንዳይመጣ ለማድረግ ማረጋገጫ የሚሰጥ ከሆነ፣

8. እራሱን ከሌሎች የቤተሰብ አባላት ለይቶ ማቆየት የሚያስችል ክፍል ወይም ከቤተሰብ አባላት በ2 ሜትር ርቀት ላይ መቆየት የሚያስችል ክፍል ያለው እንደሆነ፣

9. በጤና ቡድን በቋሚነት ለመደገፍ ፈቃደኛ የሆነ፣
3.0K viewsedited  05:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ