Get Mystery Box with random crypto!

37 የኮሮናቫይረስ ታካሚዎች ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል አገግመው ወጡ። በኮሮናቫይረስ ተይዘው በቅዱ | etv zena

37 የኮሮናቫይረስ ታካሚዎች ከቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል አገግመው ወጡ።

በኮሮናቫይረስ ተይዘው በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ማዕከል ህክምናቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 37 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸውን ሆስፒታሉ በፌስቡክ ገፁ አስታውቋል።
በቫይረሱ ተይዘው የመጡ ህሙማን ቁጥር በአጠቃላይ 178 መሆኑን ያስታወቀው ሆስፒታሉ በመጀመሪያው ዙር 44 ታካሚዎች አገግመው መውጣታቸውን ተከትሎ፤ በአጠቃላይ ከማዕከሉ አገግመው የወጡ ሰዎች ቁጥርም 81 ደርሷል።

ከዚህም በተጨማሪ ሆስፒታሉ በፌስቡክ ገፁ ላይ እንዳሰፈረው የኮሮናቫይረስ ሊኖርባቸው ይችላል ተብለው የተጠረጠሩ 205 ግለሰቦች መካከልም 144ቱ ነፃ ተብለው ወደ ቤታቸው ተሸኝተዋል። በሃገሪቱ ውስጥ በቫይረሱ ከተያዙት 4 ሺህ 848 ሰዎች መካከል1 ሺህ 412 አገግመዋል።