Get Mystery Box with random crypto!

የትራምፕ ደህንነት አባላት ኮቪድ-19 ተገኘባቸው! ባለፈው ቅዳሜ ቱልሳ ውስጥ የተካሄደው የዶናልድ | etv zena

የትራምፕ ደህንነት አባላት ኮቪድ-19 ተገኘባቸው!

ባለፈው ቅዳሜ ቱልሳ ውስጥ የተካሄደው የዶናልድ ትራምፕ ምርጫ ቅስቀሳ ላይ የተገኙ የደኅንነት አባላት ለይቶ ማቆያ መግባታቸው ተሰምቷል።

የደህንነት አባላቱ ወደ ለይቶ ማቆያ የገቡት ከመካከላቸው የተወሰኑት የኮሮና ቫይረስ (COVID-19) ስለተገኘባቸው መሆኑ ተገልጿል።

መረጃውን መጀመሪያ ያወጣው ዋሽንግተን ፖስት ሲሆን ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አንድ የፖሊስ ባለሥልጣን ደግሞ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት በጣት የሚቆጠሩ አባላት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ከምርጫ ቅስቀሳው በፊት የፕሬዝደንት ትራምፕ የቅስቀሳ ቡድን አባላትና ሁለት የደኅንነት ሰዎችን ጨምሮ ስድስት ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተዘግቦ ነበር።

ፕሬዝደንት ትራምፕ፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ባልተገታባት ኦክላሆማ ግዛት የምርጫ ቅስቀሳ አደርጋለሁ ሲሉ ብዙ ወቀሳ ገጥሟቸው ነበር።

በስብሰባው ቦታ የተገኙት ታዳሚዎችም ሙቀታቸው ተልክቶ እንዲሁም የእጅ ማፅጃ ፈሳሽ ተሰጥቷቸው ቢገቡም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ማድረግ ግዴታ አልነበረም።

የቅስቀሳ ቡድኑ አባላት አንድ ሚሊዮን ሰዎች ለመታደም ቃል ገብተዋል ብለው የነበረ ቢሆንም 19 ሺህ ሰው በሚይዘው ስታደየም የተገኙት 6,200 ሰዎች ብቻ ነበሩ ሲል #BBC አስነብቧል።