Get Mystery Box with random crypto!

GERD ? የግብፅ ሚዲያዎች እንዲሁም AFP ፣ አልጀዚራ ፣ ሮይተርስ (ሮይተርስን ዋቢ አድርገው | etv zena

GERD ?

የግብፅ ሚዲያዎች እንዲሁም AFP ፣ አልጀዚራ ፣ ሮይተርስ (ሮይተርስን ዋቢ አድርገው ደግሞ ሌሎች በርካታ የውጭ ሚዲያዎች) በሰበር ዜናቸው ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌት ስምምነት ላይ እስኪደረስ ድረስ አራዝማለች / ከስምምነት በፊት የውሃ ሙሌት ላለመጀመር ተስማምታለች እንዲሁም የኢትዮጵያ ፣ የሱዳን እና ግብፅ መሪዎች በሁለት (2) ሳምንት ውስጥ ከስምምነት ላይ ሳይደርስ የውሃ ሙሌቱ እንዳይጀመር ተስማምተዋል የሚሉ ዘገባዎችን አውጥተዋል።

ይህ ፅሁፍ የተፃፈው ከለሊቱ 8:40 በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ነው፤ መረጃዎች መሰራጨት የጀመሩት ከለሊት 6 ሰዓት በኃላ ቢሆንም በኢትዮጵያ መንግስት በኩል ምንም አልተባለም። ማብራሪያም አልተሰጠም!

በርካታ የሀገራችን ዜጎችን በጉዳዩ ላይ ምላሽ ለማግኘት፣ እውነቱን ለማወቅ ፣ በግብፅ ሚዲያዎች የሚነገረውን ለማረጋገጥ በዚህ ለሊት ማህበራዊ ሚዲያውን እያተራመሱት ነው።

በጉዳዩ ላይ ስጋት ያደረባቸው ፣ ያሳሰባቸው በርካታ የቤተሰባችን አባላት የደወሉልን ሲሆን ለጉዳዩ ቅርበት አላቸው ብለን ወዳሰብናቸው ሰዎች ስልክ ብንሞክርም ልናገኛቸው አልቻልንም።

ውድ የቲክቫህ አባላት ነገ በጉዳዩ ላይ በመንግስት በኩል የሚሰጠውን ማብራሪያ ተከታትለን እናሳውቃለን፤ በድጋሚ ሰላም እደሩ