Get Mystery Box with random crypto!

Ethio News Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewsmedianow — Ethio News Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewsmedianow — Ethio News Media
የሰርጥ አድራሻ: @ethionewsmedianow
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 210
የሰርጥ መግለጫ

እለታዊና ወቅታዊ እውነተኛ ዜና ለበለፀገች እትዮጰያ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-06-20 18:27:31 የአውሮፓ ህብረት “ሩሲያ የእህል ምርት ወደ ውጭ እንዳይወጣ መከልከሏ የጦር ወንጀል ነው” አለ

ሩሲያ በድርጊቱ የምትቀጥልበት ከሆነ “ተጠያቂ መሆን አለባት” ሲልም ህብረቱ አሳስቧል። የአውሮፓ ህብረት ሩሲያ ምግብን እንደ “ድብቅ ሚሳዔል” እየተጠቀመች ነው የሚል ክስ ሲያቀርበ እንደነበር አይዘነጋም።
66 views15:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 22:10:45
በ2021 ኒውክሌር የታጠቁ ሀገራት ያወጡት ወጪ
የኒውክሌር የጦር መሳሪያን የታጠቁ 9 ሀገራት በፈረንጆቹ 2021 ብቻ የአውቶሚካ መሳሪያቸውን ለማሻሻል 82.4 ቢሊየን ዶላር ወጪ ማድረጋቸው ተገለፀ።
ከፍተኛ ወጪ ካወጡ ሀገራት ውስጥ አሜሪካ ቀዳሚውን ስፍራ የምትይዝ ሲሆን፤ ቻይና እና ሩሲያ ተከታዩን ደረጃ ይዘዋል።
105 viewsedited  19:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-06-15 22:02:50 ከህውሃት ጋር ይፋዊ ድርድር እንዳልተደረገ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሳወቁ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለምክር ቤት አባላት ከድርድር ጋር በተገናኘ በሰጡት ምላሽ ከህውሃት ጋር ድርድር የሚደረግ ከሆነ በድብቅ ድርድር አይደረግም ያሉ ሲሆን በድርድሩ ሂደት የኢትዮጲያን ፍላጎት የሚመረምር እና የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩንም ጠቁመዋል።

የተወካዮች ምክርቤት አባል በሆኑት አቶ ክርስትያን ታደለ መንግስት ህግ በማስከበር ስም በአፈና እየወሰደ የነበረዉ እርምጃ ህዝብን አዲስ ወንጀል ማስተማር መሆኑን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸዉን አካሄድ እንዲያስረዱ በጠየቁት መሰረት ጠ/ሚኒስትሩ በመልሳቸዉ የህግ ማስከበሩ ፋኖ ላይ ያነጣጠረ አለመሆኑን ተናግረዉ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋለዉ ሀይል ዉስጥ 3 ሺህ 500 ግለሰቦች ከልዩ ሀይሉ የከዳ እና ህብረተሰቡን ሲያሸብር የቆየ ነዉ ብለዋል። የነበረዉን ስርአት አልበኝነትን ማስቆምና መከላከል በማስፈለጉ እርምጃዉ እንደተወሰደ ጠ/ሚኒስትሩ በማብራሪያቸዉ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ሆነው ያልተገባ ተግባር የፈጸሙ ከ 5 ሺህ በላይ የብልፅግና አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳውቀዋል፡፡
90 views19:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:30:16
" የዝንጀሮ ፈንጣጣ / መንኪፖክስ / ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለን አንጠብቅም " - የዓለም የጤና ድርጅት

እስካሁን በመቶዎች የተቆጠሩ ሰዎች መያዙ የታወቀው መንኪፖክስ ወይም የዝንጀሮ ፈንጣጣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ደረጃ ይደርሳል ብለው እንደማይጠብቁ የዓለም የጤና ድርጅት ከፍተኛዋ የበሽታው ኤክስፐርት ተናገሩ።

ያን ይበሉ እንጂ በሽታው እንዴት እንደሚስፋፋ ሆነ ከአያሌ አሰርት በፊት የፈንጣጣ መከላከያ ክትባት ዘመቻ መቋረጡ ያስከተለው አንድምታ ይኖር እንደሆን ጨምሮ ብዙ የማይታወቁ ነገሮች መኖራቸውን አልደበቁም።

ዶክተር ሮዛሙንድ ሉዊስ በሰጡት ማብራሪያ ድርጅታቸው መንኪፖክስ በግብረ ስጋ ግንኙነት ወይም በአየር በትንፋሽ ይተላለፍ እንደሆን በተጨማሪም የህመም ምልክት የሌላቸው ሰዎች በሽታውን ያስተላልፋሉ ወይ የሚሉትን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን ይዞ እየመረመረ መሆኑን አመልክተዋል።

ካሁን ቀደም በሽታው በተቀሰቀሰባቸው ጊዜያት በቀላሉ የሚዛመት እንዳልሆነ ታይቷል ያሉት የዓለም የጤና ድርጅቱ ባለሙያ አሁንም ሥርጭቱን ለመቆጣጠር ጊዜ እንዳለ መግለፃቸውን ቪኦኤ /VOA ዘግቧል።
121 views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:13:28 ሩሲያ የዶምባስ ግዛትን “ያለምንም ቅድመ ሁኔታ” ነጻ ማውጣት ቅድሚያ የሚሰጠው ነው አለች


የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስርጌ ላቭሮቭ እንደተናገሩት ዶምባስ ግዛትን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ነጻ ማውጣት ሩሲያ ቅድሚያ የምትሰጠው ተግባር ነው፤ ሌሎች የዩክሬን ግዛቶች እጣፋንታቸውን በራሳቸው ይወስናሉ ብለዋል፡፡
82 views18:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-30 21:09:56
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በዳግማዊ ምኒሊክ ሪፈራል ሆስፒታል የተገነባውን የኩላሊት እጥበት ማዕከል መረቁ

በምረቃው መርሐ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተገኝተዋል።

አዲስ አበባን የጤና ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ እየሰራ የሚገኘው የከተማ አስተዳደሩ ዘመናዊና ብቁ የጤና ተቋማት በመገንባት ተመጣጣኝና ፍትሀዊ የጤና አገልግሎት ለመስጠት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል ተብሏል።

የኩላሊት እጥበት ማዕከሉ ቀድሞ በሁሉም የመንግስት ሆስፒታሎች ይሰጥ የነበረውን አገልግሎት በአምስት እጥፍ እንደሚያሳድገው መገለጹን የከንቲባ ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
77 viewsedited  18:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-28 23:37:33
ዶ/ር ሊያ ታደሰ የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ

ከቀናት በፊት በተደረገው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ምርጫ ላይ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ዳግም መመረጥ የተቃወመችው ኢትዮጵያ ከግንቦት 14 2014 ዓ.ም ጀምሮ በጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የአለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰን የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል አድርጋ አስመርጣለች።

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 34 በጤና ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው እና በአባል ሀገራት የተወከሉ ባለምያዎችን በሚይዘው ቦርድ ውስጥ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት ሀገራት ተወካዮቻቸውን ያስመረጡ ሲሆን እነኚህ ተመራጮች ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት ድርጅቱን ያገለግላሉ። የቦርዱ ዋነኛ ተግባር የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔ እና ፖሊሲ ማስፈጸም እንዲሁም ምክረ-ሀሳብ ማቅረብ እና ስራዎችን ማመቻቸት ነው።
81 viewsedited  20:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-25 02:36:15 የዩክሬን ፐሬዝዳንት ዘለንስኪ “ስለ ጦርነቱ ማብቃት የምናወራ ከሆነ ያለ ፑቲን የሚሆን አይደለም” አሉ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጦርነቱን ለመቋጨት ብቸኛው መንገድ የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ማግኘት እንደሆነ ተናገሩ።

ዘለንስኪ ፑቲንን በግንባር አግኝቶ ማውራቱ ጦርነቱን ለማቆም ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።

በሩሲያ ሁሉ ነገር የሚወሰነው በፕሬዝዳንቱ ነው ያሉት ዘለንስኪ ስለ ጦርነቱ ማብቃት የምናወራ ከሆነ ያለ ፑቲን የሚሆን አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይሄን ያሉት ትናንት ሰኞ ፤ በስዊዘርላንድ ዴቮስ በመካሄድ ላይ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ነው።
98 views23:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 20:22:37
ማንችስተር ሲቲ 6ኛ የፕሪሜርሊግ ዋንጫቸውን ማሳካት ችለዋል
ከነዚህ ውስጥ 4ቱ ባለፉት 5 ሲዝኖች የተገኙ ናቸው ።
103 viewsedited  17:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 20:16:39 ግብጽ ከስዊዝ ካናል ሰባት ቢሊዮን ዶላር ገቢ እንደምታገኝ ገለጸች


የግብጽ ዋነኛ የገቢ ምንጭ የሆነው የስዊዝ ካናል በፈረንጆቹ 1869 ዓመት ጀምሮ ለአገልግሎት ክፍት የሆነ ሲሆን ይህ የመርከቦች መጓጓዣ መስመር በቀን 50 መርከቦችን በማጓጓዝ ላይ ይገኛል፡፡
85 views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ