Get Mystery Box with random crypto!

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ ከቀናት በፊት በ | Ethio News Media

ዶ/ር ሊያ ታደሰ የዓለም ጤና ድርጅት ስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል ሆነው ተመረጡ

ከቀናት በፊት በተደረገው የአለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተርነት ምርጫ ላይ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም ዳግም መመረጥ የተቃወመችው ኢትዮጵያ ከግንቦት 14 2014 ዓ.ም ጀምሮ በጄኔቭ እየተካሄደ በሚገኘው 75ኛው የአለም ጤና ድርጅት ጠቅላላ ጉባዔ ላይ ዶ/ር ሊያ ታደሰን የስራ አስፈጻሚ ቦርድ አባል አድርጋ አስመርጣለች።

ከመላው ዓለም የተውጣጡ 34 በጤና ዘርፍ ከፍተኛ እውቀት ያላቸው እና በአባል ሀገራት የተወከሉ ባለምያዎችን በሚይዘው ቦርድ ውስጥ ከአፍሪካ ኢትዮጵያን ጨምሮ ሰባት ሀገራት ተወካዮቻቸውን ያስመረጡ ሲሆን እነኚህ ተመራጮች ለቀጣዮቹ 3 ዓመታት ድርጅቱን ያገለግላሉ። የቦርዱ ዋነኛ ተግባር የጠቅላላ ጉባዔውን ውሳኔ እና ፖሊሲ ማስፈጸም እንዲሁም ምክረ-ሀሳብ ማቅረብ እና ስራዎችን ማመቻቸት ነው።