Get Mystery Box with random crypto!

የዩክሬን ፐሬዝዳንት ዘለንስኪ “ስለ ጦርነቱ ማብቃት የምናወራ ከሆነ ያለ ፑቲን የሚሆን አይደለም” | Ethio News Media

የዩክሬን ፐሬዝዳንት ዘለንስኪ “ስለ ጦርነቱ ማብቃት የምናወራ ከሆነ ያለ ፑቲን የሚሆን አይደለም” አሉ

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ ጦርነቱን ለመቋጨት ብቸኛው መንገድ የሩሲያውን ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ማግኘት እንደሆነ ተናገሩ።

ዘለንስኪ ፑቲንን በግንባር አግኝቶ ማውራቱ ጦርነቱን ለማቆም ብቸኛው መንገድ ነው ብለዋል።

በሩሲያ ሁሉ ነገር የሚወሰነው በፕሬዝዳንቱ ነው ያሉት ዘለንስኪ ስለ ጦርነቱ ማብቃት የምናወራ ከሆነ ያለ ፑቲን የሚሆን አይደለም ሲሉ ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ ይሄን ያሉት ትናንት ሰኞ ፤ በስዊዘርላንድ ዴቮስ በመካሄድ ላይ ባለው የዓለም የኢኮኖሚ ፎረም ላይ ነው።