Get Mystery Box with random crypto!

Ethio News Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewsmedianow — Ethio News Media E
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethionewsmedianow — Ethio News Media
የሰርጥ አድራሻ: @ethionewsmedianow
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 210
የሰርጥ መግለጫ

እለታዊና ወቅታዊ እውነተኛ ዜና ለበለፀገች እትዮጰያ

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

2

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-05-22 09:52:31 የአማራ ክልል ሕግ የማስከበር ሥራውን በአጭር ጊዜ እና በዝቅተኛ ጉዳት ለማጠናቀቅ መላው የጸጥታ መዋቅር ከሰላም ወዳዱ ሕዝብ ጋር በጋራ እየሠራ በሚገኝበት ወቅት ፈቃድ ያላገኘ ሰልፍም ሆነ የጎዳና ላይ ትዕይንት ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው መሆኑንም የክልሉ ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ገልጿል፡፡

በዚህ ድርጊት ላይ በቅስቀሳ እና አመጽ ጥሪ በሚያቀርቡ አካላት ላይ እንዲሁም በሰልፍ ሰበብ የሕግ ማስከበር ሥራውን ለማደናቀፍ በሚደረጉ ማንኛውም ድርጊቶች ላይ አስፈላጊውን የሕግ የማስከበር እርምጃ የሚወስድ መኾኑን ያሳውቃል።

የአማራ ክልል ሰላምና ጸጥታ ቢሮ
91 views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-22 09:52:31 "ዲፕሎማሲ ብቻ ነው ጦርነቱን ሊቋጭ የሚችለው" - የዩክሬን ፕሬዝዳንት

ጦርነቱ ደም አፋሳሽ ሊሆን ቢችልም የሚቋጨው በዲፕሎማሲያዊ መንገዶች ነው ሲሉም ለሃገራቸው የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል፡፡
መቼ፣ የት እና በእነ ማን በኩል ወይም በመሪዎች ደረጃ ሊሆን እንደሚችል በውል ባያውቁትም በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ውይይቶች እንደሚካሄዱ ግን ዜሌንስኪ በእርግጠኝነት ተናግረዋል፡፡
"በድርድር ብቻ የሚፈቱ ጉዳዮች አሉ፤ ሩሲያ አልፈቀደችም እንጂ ሁሉም ነገር ወደነበረበት እንዲመለስ እንፈልጋለን"ም ብለዋል፡፡
85 views06:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:30:13 የፌዴራል መንግስቱን እንጂ የህወሓት ባለስልጣናትን ለማግኘት ወደ ኢትዮጵያ እንዳልመጡ የአውሮፓ ህብረት የሰብዓዊ መብት ተወካይ ተናገሩ

ተወካዩ ኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ፈጻሚዎችን ተጠያቂ ማድረግ እንድትጀምር አሳስበዋል፡፡
ኢሞን ጊልሞር ሶስት ቀናት የወሰደውን የአዲስ አበባ ጉብኝታቸውን የተመለከተ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
84 views05:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 08:27:56
ፀረ-ታንክ ሚሳኤል የማይመታው አዲሱ የቱርክ ታንክ

#Ethiopia | የኤርዶጋኗ ቱርክ በወታደራዊ ቴክኖሎጂ እየተራቀቀች ትገኛለች ። በአየር በምድርና በባህር ሀይል ቴክኖሎጂዎቿ ከመሪዎቹ ተርታ ከመሰለፍም አልፋ በአንዳንድ የጦር ዘርፎች መሪዎቹን መምራትም ጀምራለች ። በተለይም በሰው አልባ የጦር ጄት ወይንም ድሮን ቱርክ ከአለም ቀዳሚ መሆኗን ከአዘርባጃን እስከ ዩክሬን አስመስክራለች ።

አሁን ደግሞ ፊቷን ወደ ምድር ጦር በማዞር ከዘመኑ የቀደሙ ታንኮችን በማምረት ተጠምዳለች ። እናም ቱርክ የትኛውም ፀረታንክ መሳሪያ ሊመታው የማይችልን ታንክ ሰርታ ጨርሳለች ። ስሙንም አልታይ #Altay ብላዋለች ። ስያሜውም የቱርክ ነፃነት ለማስከበር በተደረገው ፍልሚያ የቱርክን ጦር እየመራ በግሪክ ወራሪ ላይ ከፍተኛ ድል የተቀጃጄውን የቁርጥ ቀን ልጅ ፈህረዲን አልታይን ለማሰብ የተሰየመ ነው ።

አልታይ ታንክ ጃቫሊንን ከመሰሉ የተራቀቁ ፀረታንኮች ራሱን መጠበቅ የሚያስችለው 360 ድግሪ የተገጠመለት ፀረታንክ መከላከያ አለው ። በዚህም መሰረት ይህ የቱርክ ታንክ ፀረታንክ ሚሳኤል ሲተኮስበት በተገጠመለት ሴንሰር መሰረት በፍጥነት በመለየት ራሱን ራሱን ሙሉ በሙሉ ከጥቃት ይሸፍናል ። ከመሸፈን በተጨማሪም በተገጠመለት ሚሳኤል ማውደሚያ የሚተኮሱበትን ሚሳኤሎች መትቶ ማክሸፍም ይችላል ። ከዚያም አልፎ ፀረታንኮቹ የተወነጨፉበትን አቅጣጫ በቅፅበት መለየት ስለሚችል ከቦታው ማፅዳትም የሚችል የተራቀቀ ታንክ ነው ።

ይህ አዲሱ የቱርክ ኩራት አልታይ 65 ቶን ክብደት ያለው ሲሆን በሰአት 60 ኪሎሜትር መክነፍም ይችላል ። እናም አዲሱ የቱርክ ታንክ ዩክሬይን ውስጥ እንደረገፉት የሩሲያ ታንኮች ለጥቃት ተጋላጭ አይሆንም ።

ቱርክ በቅርብ ጊዜ 1,000 የአልታይ ታንኮችን ለማምረት እየሰራች ትገኛለች ።

Seid Mohammed
80 viewsedited  05:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:53:00
#NATO

ቱርክ ፤ ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ለመሆን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለምንድነው የማትደግፈው ?

ቱርክ ፤ የፊንላንድ እና ስውዲን NATOን መቀላቀል እንደማትደግፍ አስታወቀች።

የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ፤ ሀገራቸው ስዊድን እና ፊንላንድን NATOን በአባልነት የመቀላቀል እቅድ እንደማትደግፍ ገልፀዋል።

ምንም እንኳን ፕሬዝዳንቱ በግልፅ ባያብራሩም የኖርዲክ ሀገራት የብዙ አሸባሪ ድርጅቶች መገኛ ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

ዛሬ አንካራ ውስጥ ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት ኤርዶጋን ፥ " ስዊድን እና ፊንላንድን በሚመለከት ያለውን ሂደት እየተከታተልን ነው ፤ ነገር ግን በጉዳዩ ላይ አዎንታዊ አመለካከት የለንም " ብለዋል።

ከዚህ ቀደም NATO ግሪክን በአባልነት መቀበሉ ስህተት ነበር ሲሉም ተደምጠዋል። " እንደ ቱርክ ተመሳሳይ ስህተቶችን መድገም አንፈልግም " ሲሉ አክለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዝርዝር ባያብራሩም " የስካንዲኔቪያ አገሮች የአሸባሪ ድርጅቶች ማረፊያ ናቸው " ሲሉ የተደመጡት ፕሬዜዳንት ኤርዶጋን ፤ " እንደውም በአንዳንድ ሀገራት የፓርላማ አባላት ናቸው ፤ እኛ ደጋፊ መሆን አንችልም (NATOን የመቀላቀል ጉዳይ) " ብለዋል።

ቱርክ ስውዲንን እና ሌሎች የምዕራብ አውሮፓ ሀገራትን አሸባሪ ስትል የፈረጀቻቸውን እንደ ኩርዲሽ ሚሊሻ ቡድን PKK እና YPG ፤ እንዲሁም በአሜሪካ መቀመጫቸውን ያደረጉትን የፈቱላህ ጉለንን ተከታዮች ይደግፋሉ/ያስተናግዳሉ ስትል በተደጋጋሚ ስትወቅስ ይደመጣል።

አንካራ ጉሌኒስቶች እ.ኤ.አ. በ2016 መፈንቅለ መንግስት ሙከራ አድርገዋል ስትል የምትከስ ሲሆን ጉለን እና ደጋፊዎቹ ክሱን አይቀበሉትም።
82 viewsedited  16:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:49:17
#Update

#ፊንላንድ #ስውዲን #ሩስያ #NATO

የስዊድን ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አን ሊንዴ ሀገራቸው የNATO አባል እንድትሆን ማመልከቻ መፈራረማቸው ተነግሯል። ሚኒስትሯ የፈረመት የአባልነት ጥያቄ ማማልከቻ ከፊንላንድ የNATO ማመልከቻ ጋር አብሮ ይቀርባል ሲሉ የሀገሪቱ ሚዲያዎች ዘግበዋል።

ዛሬ የፊንላንድ ፓርላማ የNATO ወታደራዊ ጥምረት አባል ለመሆን የቀረበውን ሀሳብ በ188 ድምጽ በስምንት ተቃውሞ አፅድቋል።

ፊንላንድ ለNATO አባልነት ማማልከቻ ልታቀር መሆኑን ተከትሎ ሩሲያ የኒኩሊየር ጦር መሳሪያ አስወንጫፊ ሚሳየሎችን ወደ ፊንላንድ ድንበር ማስጠጋቷ ተነግሯል ፤ ወደ ፊንላንድ ድንበር ያስጠጋ የኢስካንደር ሚሳየሎች እንደሆነ ተሰምቷል።

ስዊድን ለNATO አባልነት ጥያቄ ለማቅረብ ከውሳኔ ላይ መድረሷን ተከትሎ ሩሲያ በብሔራዊ ደህንነቷ ላይ የሚደርሰውን ስጋት ለመቅረፍ ወታደራዊ-ቴክኒካል እና ሌሎች የምላሽ እርምጃዎችን እንደምትወስድ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ከሰዓት ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

የቱርክ ፕሬዜዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን በድጋሚ ሀገራቸው ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ለመሆን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ እንደማይደግፉ አረጋግጠዋል። ሀገራቱ ወደ አንካራ የአግባቢ ልዑክ ይልካሉ እየተባለ ሲሆን ኤርዶጋን ግን " አቋማችን ግልፅ ነው ወደ አንካራ ልኡክ በመላክ ባትለፉ እኛንም ባታስቸግሩን ይሻላችኃል " ብለዋቸዋል።

ቱርክ ፤ ፊንላንድ እና ስውዲን የNATO አባል ለመሆን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ ለምንድነው የማትደግፈው ? ከዚህ ቀጥሎ እንለቀዋለን ያንብቡ ፦

መረጃዎቹ የተሰባሰቡት ፦ ከአጃንስ ፍራንስ ፕሬስ፣ ሲጂቲኤን ፣ ቴሌግራፍ፣ ኤፒ ፣ ዬል ነው።
70 views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:42:12 #Somalia #USA

አዲሱ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሐመድ ፤ የአሜሪካን ጦር ወደ ሶማሊያ መልሶ ለማሰማራት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ያሳለፉትን ውሳኔ በደስታ ተቀብለዋል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ሀሩን ማሩፍ (ቪኦኤ)
52 views16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-17 19:41:41 ልዩ መረጃ!

ኤርትራ ከህወሓት ጥቃት እራሷን ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ መሆኗን ገለጸች

የኤርትራ መንግሥት በማስታወቂያ ሚኒስቴሩ በኩል ዛሬ ግንቦት 09/2104 ዓ.ም. ባሰፈረው መልዕክት ህወሓት በኤርትራ ድንበር በኩል እና በምዕራብ ትግራይ አቅጣጫ በሁለት ግንባሮች ጦርነት ለመክፈት እየተዘጋጀ ነው ብሏል።

ጨምሮም በዚህ በህወሓት ሊሰነዘር ይችላል ላለው ጥቃት የመጀመሪያው ዒላማ "ኤርትራ እና የኤርትራ ሕዝብ ናቸው" ሲል አቋሙን አንጸባርቋል።

ከወራት በፊት ከተደረገው ከባድ ውጊያ በኋላ ጋብ ብሎ የቆየው የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ዳግም ሊያገረሽ ይችላል የሚል ስጋት እየጨመረ በመጣበት ጊዜ ነው የኤርትራ መንግሥት ይህንን ያለው።

ከቀናት በፊት የአማራ ክልል ከህወሓት በኩል ሊሰነዘር ይችላል ላለው ሌላ ዙር ወረራ የክልሉ የፀጥታ መዋቅር ዝግጁ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላልፎ ነበር።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በበኩሉ በሰሜን ኢትዮጵያ በትግራይ ኃይሎች እና በፌደራል መንግሥት ኃይሎች መካከል ውጥረት እየጨመረ መምጣቱ እንዲሁም አልፎ አልፎም ግጭቶች ሪፖርት መደረጋቸው እንዳሳሰበው ገልጾ ነበር።

እያየለ ከመጣው የዳግም ጦርነት ስጋት በተጨማሪ ባለፈው ሳምንት የትግራይ ኃይሎች ከኤርትራ ድንበር አቅራቢያ ለጥቂት ሰዓታት የቆየ ጥቃት ሰንዝረው የከባድ መሳሪያ ተኩስ ልውውጥ እንደነበረ ቢቢሲ መዘገቡ ይታወሳል።

ዛሬ በኤርትራ መንግሥት ኢንፎርሜሽን ሚኒስቴር ድረ-ገጽ ላይ የወጣው ጽሑፍ ላይ ግን ሚያዚያ 30/2014 ዓ.ም. ራማ እና ባድመ አካባቢ ከህወሓት ኃይሎች ጋር ግጭት አጋጥሞ ነበር ስለመባሉ ያለው ነገር የለም።

የኤርትራ መንግሥት ባስተላለፈው መልዕክት በዓለም አቀፍ ሕግ የኤርትራ ሉዓላዊ ግዛት እንደሆነ ያረጋገጠወን አካባቢ ህወሓት ዳግም ለመውረር በዝግጅት ይገኛል ሲል ከሷል።

ከዚህ በተጨማሪም፤ ህወሓት ሊከፍት ነው ላለው አዲስ ጥቃት በምዕራብ ወልቃይት፣ ጸገዴ እና ሑመራን መልሶ በመቆጣጠር ከሱዳን ጋር የሚያዋስነውን ድንበር ለመክፈት አቅዷል ብሏል።

በመጨረሻም ከህወሓት ሊሰነዘር የሚችልን ጥቃት የኤርትራ ሕዝብ እና መንግሥት እራሱን መከላከል ይችላል በማለት ዝግጁ መሆኑን ገልጿል።

ለዚህ ከኤርትራ መንግሥት በኩል በይፋ ለቀረበው ወረራ ለመፈጸም የመዘጋጀት ክስ ከህወሓት በኩል አስካሁን የተባለ ነገር የለም ሲል ቢቢሲ ዘግቦታል።
61 views16:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ