Get Mystery Box with random crypto!

Alpha Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ alphamedia24 — Alpha Media A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alphamedia24 — Alpha Media
የሰርጥ አድራሻ: @alphamedia24
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.05K
የሰርጥ መግለጫ

Amhara Liberation People Harmonious Association!!!
Alphatv24

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-08-14 19:33:42
605 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 19:33:35 የAsaye Derbie "ዕልልታ የዋጠው እሪታ" የተሰኘው እና ባለፉት ዐራት ዓመታት ውስጥ በሕዝባችን ላይ ስለደረሰው ግፍ መረጃዎችን ሰንዶ የያዘው መጽሐፍ ወጥቶአል

"'እልልታ የዋጠው እሪታ' የአሳዬ ደርቤ አራተኛ መጽሐፍ ሲሆን ከሥልጣን ሽግግሩ ዋዜማ አንስቶ እስካለንበት ጊዜ ድረስ በመንግሥታዊ እልልታዎች የተዋጡትን ሕዝባዊ እሪታዎች በወግና በስንኝ ይተርካል።

እንደ ሕዝብ ያከሸፍናቸውን መልካም አጋጣሚዎች፣ የቀበርናቸውን ወገኖች፣ ያስተናገድናቸውን ማንነት ተኮር ወረራዎችና ጥቃቶች፣ እንዳጠቃላይም ባለፉት አራት ዓመታት ተከስተው የዘነጋናቸውን አበይት ክስተቶች፣ ከምሥልና ከቃል ማስረጃ ጋር ይዘረዝራል።

ከዚህ ባለፈም በጦርነቱ ወቅት የተከፈለውን ዋጋ፣ በኦነግ በትሕነግ፣ በጉምዝ፣ በመንግሥት የተፈጸሙብንን ጥቃቶች፣ በአገር ውስጥ የተፈጠሩትን የተለያዩ መንግሥታትና አገራት ይተርካል"
600 views16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:50:26
585 views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:50:22 የቅዱስ ላሊበላ የበጎ አድራጎት ልማት ማህበር (ላልማ) ተመሠረተ!

የላስታ ላሊበላንና የዙሪያውን ወረዳዎች መቄት፣ቡግና፣ግዳንናየሰቆጣ አጎራባች አካባቢዎችን ጨምሮ በልማት ተጠቃሚ ለማድረግ በማለም የቅዱስ ላሊበላ የበጎ አድራጎት ልማት ማህበር (ላልማ) ተመስርቷል።

የልማት ማህበሩ በኢትዮጵያ የበጎ አድራጎት ማህበራት መመዝገቢያና ማስተዳደሪያ አዋጅ 1994/2004 አንቀፅ 63 ንኡስ አንቀፅ 1 መሠረት የልማት ማህበር ሆኖ ተመዝግቧል። ማህበሩ የላሊበላ ከተማና የላስታ ወረዳ የስራ ሃላፊዎች፣የከተማዋ ነዋሪዎችና ሌሎችም በተገኙበት በይፍ መመስረቱ ይፋ ሆኗል።
554 views15:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:15:03
557 views15:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:14:53 እጃችንን እንዘርጋ!!!

የአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ልማት ፈንድ ጽ/ቤት ሐብት ለማሰባሰብ የከፈታቸው አካውንቶች ናቸው።

በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ለማቋቋም በተማከለ መንገድ ሐብት ማሰባሰብና በፍትሃዊነት ለመጠቀም የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ የእርስዎ አስተዋጽኦም ይፈለጋልና ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቦልዎታል።
543 views15:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:05:16
549 views15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:05:13 #SidamaRegion

ዛሬ እሁድ አስቸኳይ ስብሰባ የገባዉ የሲዳማ ክልል መንግስት የሲዳማ ዞኖችን መጀመሪያ ከጸደዉ አምስት ዞኖች ሁለት ዞኖችን በመቀነስ ሶስት አድርጎ ማለትም ሀዋሳ ዞን፣ አ/ወንዶ ዞንና በንሳ ዞን በማድረግ ለማጽደቅ ወሰነ።

የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥናት የጸደቀዉና በሲዳማ ህገ-መንግስት ላይ የተቀመጠዉ 5 ዞን ቢሆንም በጀት ለመመዝበር በማሰብ የዳሌ ይርጋዓለምና የሀዋሳ ዙርያ ዞኖችን በመቀነስ ሶስት ዞን ለማድረግ ወስኗል።

በዚህም መሰረት፦

1.ሀዋሳ ዞን፡ ሀዋሳ፣ ሀዌላ ፣ ቦርቻ ፣ለኩ ከተማ አስተዳደር፣ ሻባዲኖ ፣ ጎርቼ ፣ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር፣ ዴሌ ወረዳ፣ ወንሾ ፣ ወ/ገነት ፣ ማልጋ፣ ሀዋሳ ዙርያ ፣ ዳራራ፣ ወንሾ፣ ብላቴ ዙርያ እና ሎኮ አባያ።

2.አ/ወንዶ ዞን፦ አለታ ወንዶ ወረዳ ፣ቡርሳ ፣ አለታ ጩኮ ወረዳ ፣ ጭሮኔ፣ ጩኮ ከተማ አስተዳደር፣ ወንዶ ከተማ አስተዳደር፣ ጤጥቻ፣ ሁላ፣ ዳራ ኦትልቾና ዳራ ሲሆን።

3.በንሳ ዞን፦ በንሳ ወረዳ ፣ ዳዬ ከተማ አስተዳደር ፣ አሮሬሳ፣ አርበጎና፣ ጭሬ፣ ግርጃ ሆኮ፣ ቡራ፣ሻፋሞ፣ ዳኤላ፣ ቦና ዙርያ ወረዳ፣ ጫቤ ጋምበልቱ እና ቡራ ይገኙበታል።

የሲዳማ ክልል መንግስት ህገ-ወጥነት ጫፍ እየወጣ መጥቷል። ህግን ሳይሆን ለዝርፊያ የምመቻቸዉን መንገድ እየተከተሉም ይገኛል።
548 viewsedited  15:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:03:05
544 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 18:03:01 #Egypt

በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ 41 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

የሟቾችን ቁጥር የሀገሪቱ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የጤና ባለሙያዎችን ጠቅሶ አስታውቋል።

ሌሎች 14 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል።

በኢምባባ ሰፈር በሚገኘው የኮፕቲክ አቡ ሲፊን ቤተክርስቲያን 5,000 ምእመናን ለቅዳሴ በተሰበሰቡበት ወቅት የኤሌትሪክ እሳት መከሰቱን ምንጮች ለሮይተርስ የዜና አገልግሎት ገልጸዋል።

እሳቱ የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በር በመዝጋቱ አደጋውን እንዲባባስ ምክንያት መሆኑን የተገለፀ ሲሆን አብዛኞቹ ሟቾች ደግሞ ህጻናት መሆናቸውን ተናግረዋል።
560 views15:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ