Get Mystery Box with random crypto!

የAsaye Derbie 'ዕልልታ የዋጠው እሪታ' የተሰኘው እና ባለፉት ዐራት ዓመታት ውስጥ በሕዝባች | Alpha Media

የAsaye Derbie "ዕልልታ የዋጠው እሪታ" የተሰኘው እና ባለፉት ዐራት ዓመታት ውስጥ በሕዝባችን ላይ ስለደረሰው ግፍ መረጃዎችን ሰንዶ የያዘው መጽሐፍ ወጥቶአል

"'እልልታ የዋጠው እሪታ' የአሳዬ ደርቤ አራተኛ መጽሐፍ ሲሆን ከሥልጣን ሽግግሩ ዋዜማ አንስቶ እስካለንበት ጊዜ ድረስ በመንግሥታዊ እልልታዎች የተዋጡትን ሕዝባዊ እሪታዎች በወግና በስንኝ ይተርካል።

እንደ ሕዝብ ያከሸፍናቸውን መልካም አጋጣሚዎች፣ የቀበርናቸውን ወገኖች፣ ያስተናገድናቸውን ማንነት ተኮር ወረራዎችና ጥቃቶች፣ እንዳጠቃላይም ባለፉት አራት ዓመታት ተከስተው የዘነጋናቸውን አበይት ክስተቶች፣ ከምሥልና ከቃል ማስረጃ ጋር ይዘረዝራል።

ከዚህ ባለፈም በጦርነቱ ወቅት የተከፈለውን ዋጋ፣ በኦነግ በትሕነግ፣ በጉምዝ፣ በመንግሥት የተፈጸሙብንን ጥቃቶች፣ በአገር ውስጥ የተፈጠሩትን የተለያዩ መንግሥታትና አገራት ይተርካል"