Get Mystery Box with random crypto!

#Egypt በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ | Alpha Media

#Egypt

በግብጽ ዋና ከተማ ካይሮ በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰ የእሳት ቃጠሎ ቢያንስ 41 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

የሟቾችን ቁጥር የሀገሪቱ ኮፕቲክ ቤተክርስቲያን የጤና ባለሙያዎችን ጠቅሶ አስታውቋል።

ሌሎች 14 ሰዎች ቆስለዋል ተብሏል።

በኢምባባ ሰፈር በሚገኘው የኮፕቲክ አቡ ሲፊን ቤተክርስቲያን 5,000 ምእመናን ለቅዳሴ በተሰበሰቡበት ወቅት የኤሌትሪክ እሳት መከሰቱን ምንጮች ለሮይተርስ የዜና አገልግሎት ገልጸዋል።

እሳቱ የቤተክርስቲያኑ መግቢያ በር በመዝጋቱ አደጋውን እንዲባባስ ምክንያት መሆኑን የተገለፀ ሲሆን አብዛኞቹ ሟቾች ደግሞ ህጻናት መሆናቸውን ተናግረዋል።