Get Mystery Box with random crypto!

Alpha Media

የቴሌግራም ቻናል አርማ alphamedia24 — Alpha Media A
የቴሌግራም ቻናል አርማ alphamedia24 — Alpha Media
የሰርጥ አድራሻ: @alphamedia24
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 5.05K
የሰርጥ መግለጫ

Amhara Liberation People Harmonious Association!!!
Alphatv24

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2022-08-14 14:52:25 https://t.me/FanoTV24
651 views11:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 14:38:04
687 views11:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 14:37:57 በ2005 ዓም ለ20/80 የጋራ መኖሪያ ቤት የተመዘገቡ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬም ቅሬታቸውን እያቀረቡ።ባቋቋሙት ኮሚቴ የሚዲያ ሽፋን ቢጠይቁም ምላሽ የሚሰጣቸው እንዳጡ ተናግረዋል።
ከታች ያለው የኮሚቴው ሃሳብ ነው

"እኛ የ2005 የ20/80 ባለ ሶስት መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ላነሳናቸው ጥያቄዎች ከ15 በላይ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና ተቋማት ጥያቄያችንን እና ቅሬታችንን በደብዳቤ አቅርበን ተጨባጭ የሆነ የተብራራ ምላሽ ማግኘት ባለመቻላችን ቅሬታችንን በብዙሃን መገናኛ ተቋማት በኩል እንዲደርስልን በማሰብ ከ20 በላይ ለሚሆኑ በከተማችን ለሚገኙ የቴሌቭዥን፣ የሬዲዮ እና የኢተርኔት መገናኛ ተቋማት የዘገባ ሽፋን በመስጠት ድምፅ እንዲሆኑን በደብዳቤ የጠየቅን ቢሆንም ያገኘነው ግብረ-መልስ የሚያሳዝን ሆኖ አግኝተነዋል፡፡
መገናኛ ብዙሃን ከሰብዓዊ መብት ከመልካም አስተዳደርና ከፍትሃዊ የኢኮኖሚ ክፍፍል ጥያቄ የበለጠ ምን ቢመጣላችሁ ነው ትኩረት ሰጥታችሁ የዘገባ ሽፋን የምትሰጡት? ከተቋቋማችሁበት አላማ አንፃር አይጋጭባችሁም?
የመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ከሁሉም ዜጋ በተሰበሰበ ግብር የምትተዳደሩ እንደመሆኑ መጠን ለዜጎች የፍትህ፣ የመልካም አስተዳደርና የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጥያቄ እና ቅሬታ ሽፋን በመስጠት በመንግስት እና በህዝብ መካከል ድልድይ በመሆን የህዝብ አግልጋይነት ሚናችሁን ካልተወጣችሁ ከተቋቋማችሁበት አላማና ተልእኮ አንፃር አላማችሁን እያሳካችሁ አይደለምና ቅሬታችን ከፍ ያለ ነው፡፡
የግል የመገናኛ ብዙሃንም የተቋቋማችሁበት ዋና አላማ ያለውን የሚዲያ ክፍተት በመሙላት የህዝብ ድምፅ ለመሆን እንደመሆኑ መጠን ሽፋን ላለመስጠት ያገዳችሁ ምን ይሆን?
714 views11:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 12:04:55
763 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 12:04:52 #Update

ዘሪቱ ከበደ የሰው ምስል ያለፈቃድ ያካተተችበትን ቪዲዮ አጥፍታ ብቻዋን በሚያሳይ ቀይራዋለች። ይሁንና ያኛው ቪዲዮ ከተለቀቀ 24 ሰአት ባይሞላውም በበርካቶች ዳውን ሎድ ተደርጎ አሁንም ማሕበራዊ ሚዲያዎች ላይ በስፋት ተሰራጭቶ ይገኛል።
743 views09:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 08:54:26
835 views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 08:54:21 ሐዋርያት ካልሰበኩት "ከሌላኛው ኢየሱስ" ራሳችሁን ጠብቁ፦
"ያልሰበክነውን ሌላ ኢየሱስ ...."
(2ኛ ቆሮንቶስ 11፥4)

"another Jesus whom we have not preached ..."

"ኀበ ካልእ [ኢየሱስ] ዘኢሰብክነ ለክሙ..."

ገና ለገና "ያድናል" ስላልክ ማንም ዝም ብሎ አይከተልህም። እኔ የማምነው "ኢየሱስ" አንተ የምታምነው ነው ልትለኝ አትችልም። ሐዋርያት የሰበኩለትን፣ ሰማዕታት መከራ የተቀበሉለትን፣ ቅዱሳን በገድል በትሩፋት የተጋደሉለትን ያንን ኢየሱስን ነው የማምነው። ሑር እምኔየ ሰይጣን!!!

@AlphaMedia24
803 views05:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 08:52:09
714 views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 08:52:04 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙት ጥቂት ቅኔ አዋቂ እናቶች መካከል የነበሩት አርበኛ መንበር ማዘንጊያ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ !!!

(ነሐሴ 8 ቀን 2014 ዓ.ም)

በሀገራችን ከሚገኙት ጥቂት ቅኔ አዋቂ እናቶች መካከል የሆኑት አርበኛ መንበር ማዘንጊያ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዳግማዊ አጼ ቴዎድሮስ በነገሱባት በታሪካዊቷ መንበረ መንግስት ጸርሐ ጽዮን ደረስጌ ቅድስት ማርያም ከአለቃ ማዘንጊያ ጣፈጠና ከወ/ሮ ገነት በለጠ በ1933 ዓም የተወለዱት አርበኛ መንበር ማዘንጊያ በተወለዱባት አጥቢያ ደረስጌ ቅድስት ማርያም የአብነት ትምህርታቸውን የተከታተሉ ሲሆን ቅኔን ከነአገባቡ በመማር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ከሚገኙ ጥቂት ቅኔ አዋቂ እናቶች መካከል አንዷ ለመሆን በቅተዋል።

አርበኛ መንበር ማዘንጊያ ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በሕክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ81 ዓመታቸው  ትናንት ነሐሴ 7 ቀን 2014 ዓም ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል። አርበኛ መንበር ማዘንጊያ የአንድ ወንድ ልጅና የሁለት ሴት ልጆች እናት ነበሩ። ለወዳጅ ቤተሰቦቻቸው እና ለመላው ኢትዮጵያውያን መጽናናትን እንመኛለን።
945 views05:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-14 08:18:23
706 views05:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ