Get Mystery Box with random crypto!

#SidamaRegion ዛሬ እሁድ አስቸኳይ ስብሰባ የገባዉ የሲዳማ ክልል መንግስት የሲዳማ ዞኖችን | Alpha Media

#SidamaRegion

ዛሬ እሁድ አስቸኳይ ስብሰባ የገባዉ የሲዳማ ክልል መንግስት የሲዳማ ዞኖችን መጀመሪያ ከጸደዉ አምስት ዞኖች ሁለት ዞኖችን በመቀነስ ሶስት አድርጎ ማለትም ሀዋሳ ዞን፣ አ/ወንዶ ዞንና በንሳ ዞን በማድረግ ለማጽደቅ ወሰነ።

የሲዳማ ክልል ዞኖች በጥናት የጸደቀዉና በሲዳማ ህገ-መንግስት ላይ የተቀመጠዉ 5 ዞን ቢሆንም በጀት ለመመዝበር በማሰብ የዳሌ ይርጋዓለምና የሀዋሳ ዙርያ ዞኖችን በመቀነስ ሶስት ዞን ለማድረግ ወስኗል።

በዚህም መሰረት፦

1.ሀዋሳ ዞን፡ ሀዋሳ፣ ሀዌላ ፣ ቦርቻ ፣ለኩ ከተማ አስተዳደር፣ ሻባዲኖ ፣ ጎርቼ ፣ ይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር፣ ዴሌ ወረዳ፣ ወንሾ ፣ ወ/ገነት ፣ ማልጋ፣ ሀዋሳ ዙርያ ፣ ዳራራ፣ ወንሾ፣ ብላቴ ዙርያ እና ሎኮ አባያ።

2.አ/ወንዶ ዞን፦ አለታ ወንዶ ወረዳ ፣ቡርሳ ፣ አለታ ጩኮ ወረዳ ፣ ጭሮኔ፣ ጩኮ ከተማ አስተዳደር፣ ወንዶ ከተማ አስተዳደር፣ ጤጥቻ፣ ሁላ፣ ዳራ ኦትልቾና ዳራ ሲሆን።

3.በንሳ ዞን፦ በንሳ ወረዳ ፣ ዳዬ ከተማ አስተዳደር ፣ አሮሬሳ፣ አርበጎና፣ ጭሬ፣ ግርጃ ሆኮ፣ ቡራ፣ሻፋሞ፣ ዳኤላ፣ ቦና ዙርያ ወረዳ፣ ጫቤ ጋምበልቱ እና ቡራ ይገኙበታል።

የሲዳማ ክልል መንግስት ህገ-ወጥነት ጫፍ እየወጣ መጥቷል። ህግን ሳይሆን ለዝርፊያ የምመቻቸዉን መንገድ እየተከተሉም ይገኛል።