Get Mystery Box with random crypto!

ከህውሃት ጋር ይፋዊ ድርድር እንዳልተደረገ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሳወቁ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ | Ethio News Media

ከህውሃት ጋር ይፋዊ ድርድር እንዳልተደረገ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሳወቁ

ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ለምክር ቤት አባላት ከድርድር ጋር በተገናኘ በሰጡት ምላሽ ከህውሃት ጋር ድርድር የሚደረግ ከሆነ በድብቅ ድርድር አይደረግም ያሉ ሲሆን በድርድሩ ሂደት የኢትዮጲያን ፍላጎት የሚመረምር እና የሚያጣራ ኮሚቴ መዋቀሩንም ጠቁመዋል።

የተወካዮች ምክርቤት አባል በሆኑት አቶ ክርስትያን ታደለ መንግስት ህግ በማስከበር ስም በአፈና እየወሰደ የነበረዉ እርምጃ ህዝብን አዲስ ወንጀል ማስተማር መሆኑን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩ የመንግስታቸዉን አካሄድ እንዲያስረዱ በጠየቁት መሰረት ጠ/ሚኒስትሩ በመልሳቸዉ የህግ ማስከበሩ ፋኖ ላይ ያነጣጠረ አለመሆኑን ተናግረዉ በህግ ቁጥጥር ስር ከዋለዉ ሀይል ዉስጥ 3 ሺህ 500 ግለሰቦች ከልዩ ሀይሉ የከዳ እና ህብረተሰቡን ሲያሸብር የቆየ ነዉ ብለዋል። የነበረዉን ስርአት አልበኝነትን ማስቆምና መከላከል በማስፈለጉ እርምጃዉ እንደተወሰደ ጠ/ሚኒስትሩ በማብራሪያቸዉ ጠቁመዋል።

በተጨማሪም በብልፅግና ፓርቲ ውስጥ ሆነው ያልተገባ ተግባር የፈጸሙ ከ 5 ሺህ በላይ የብልፅግና አባላት ላይ እርምጃ መወሰዱን ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ አሳውቀዋል፡፡