2023-03-20 08:48:10
#የሰላምታ_ትሩፋትና #ሰላምታን_ማብዛት_ስለመታዘዙ
#ክፍል_2
አላህ እንዲህ ብሏል፦
“በሰላምታ በተከበራችሁም ጊዜ ይበልጥ ባማረ (ሰላምታ) አክብሩ፤ ወይም (እርሷኑ) መልሷት፡፡” (አን ኒሳእ፡ 86)
#ሐዲሥ 131 / 846
አቡ ሁረይራ እንዳስተላለፉት ነቢዩ እንዲህ ብለዋል፦ “አላህ አደምን በፈጠረ ጊዜ ‘ለነዚያ _ለተቀመጡት መላእክት_ ሰላምታ አቅርብላቸው። ምላሻቸውንም በጥሞና ስማ። ያንተና የዝሪያዎችህ ሰላምታ ነውና’ አለው። ‘አስሰላሙ ዐለይኩም’ አላቸው። ‘አስሰላሙ ዐለይከ ወረሐመቱላሂ’ በማለት <<ወረሕመቱላህ>> የሚል አክለው መለሱለት፡፡” (ቡኻሪና ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ “አስሰላሙ ዐለይኩም” የሚለው ቃል ኢስላማዊ የሰላምታ አቀራረብ ስልት ነው። አላህ ይህን ቃል አደምን ከፈጠረበት ዕለት አንስቶ ለባሮቹ ሰላምታ አድርጎታል።
2/ ሰላምታ ሲመልሱ በርከት አድርጎ መመለስ በላጭ መሆኑን ሐዲሡ ያሳያል። “አስሰላሙ ዐለይኩም” ላለ “ወዐለይኩሙ ሰላም ወረሕመቱላሂ ወበረካቱሁ” በማለት ማከል በላጭ ነው።
ቴሌግራም
https://t.me/ethiomuslim_1
100 viewsAm First, 05:48