2022-08-02 12:37:43
#የሪዝቅ_በር_መክፈቻ
1. *ኢማን* ፡- ይህንን በተመለከተ አሏህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል ገልጿል፡-
" _የከተማዋም ሰዎች ባመኑና በተጠነቀቁ ኖሮ በእነሱ ላይ ከሰማይም ከምድርም በረከቶችን በከፈትንላቸው ነበር፡፡ ግን አስተባበሉ፡፡ ይሠሩት በነበሩትም ኃጢኣት ያዝናቸው_ ፡፡" አል- አዕራፍ፡96
2, *ትዳርን መያዝ* (ማግባት)፡- ይህንን በተመለከተ አሏህ በተከበረው ቃሉ እንዲህ ሲል ገልጿል፡- " _ከናንተም ትዳር የሌላቸውን አጋቡ_፡፡ _ከወንዶች ባሮቻችሁና ከሴቶች ባሮቻችሁም ለጋብቻ ብቁ የኾኑትን (አጋቡ)፡፡ ድኾች ቢኾኑ አላህ ከችሮታው ያከብራቸዋል_ ። _አላህም ስጦታው ሰፊ ዐዋቂ ነው_፡፡ " አን-ኑር፡ 32
3, *ተወኩል* ፡- ይህንን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ ተወኩልን ሪዝቅ እንደሚያሰፋ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡- " _ትክክለኛ (ተገቢ) የሆነች መመካትን በአሏህ ላይ ብትመኩ ኖሮ በራሪን ወፍ ምግቧን እንደሚረዝቃት ሁሉ እናንተንም ይረዝቃችሁ ነበር፡፡ ጠዋት በባዶ ሆድዋ ወጥታ ማታ ሆድዋን ሞልታ ትመለሳለች_፡፡ " ቲርሚዚይ ዘግበውታል ሸኽ አልባኒም ሐዲሱ
ሰሒሕ ብለውታል
4. *ስለቱ ረሒም* (ዝምድና መቀጠል) ፡- ይህንን በተመለከተ የአላህ መልእክተኛ ዝምድናን መቀጠል የሪዝቅ በር እንደሚያሰፋ ስገልጹ እንዲህ
ብለዋል፡- " _ሪዝቁን እንዲሰፋለት ደስ የሚለው ሰው፣ ወይም ዕድሜውን እንዲረዝምለት የሚፈልግ ሰው ዝምድናን ይቀጥል_፡፡" ቡኻሪ
ዘግበውታል
5,*ደካማዎችን ማገዝ* ፡- የሪዝቅን በር ሊያሰፉ ከሚችሉ መልካም ነገሮች መካከል ሌላው ደግሞ ለደካሞች መልካምን መዋል ነው፡፡ ይህንን በተመለከተ የአላህ መልዕክተኛ ለደካሞች መልካምን መዋል የሪዝቅ በር እንደሚያሰፋ ሲገልጹ እንዲህ ብለዋል፡-
" _ነስር (ድል) እና ሪዝቅ እያገኛችሁት ያለው በደከማዎቻችሁ (ላይ በምታደርጉት በጎ ነገር) ምክንያት እንጂ በሌላ አይደለም፡፡"
ቡኻሪ ዘግበውታል
ሼር ማድረግ አትርሱ።
*አላህ ሐላል የሆነ የሪዝቅ በሩን ይክፈትላች፣ ሪዝቃችሁንም ያስፋላችሁ*። አሚን
123 viewsAm First, 09:37