2023-03-30 17:36:13
#የሰላምታ_አሰጣጥ
#ክፍል_1
ሰላምታ የሚያቀርበው ሰው ፦ “አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ” (የአላህ ሰላም፣ እዝነትና በረከት በናንተ ላይ ይስፈን) ማለቱ የተወደደ ነው። ሰላምታ የሚቀርብለት ሰው አንድ ቢሆንም እንኳ በዚህ ብዙነትን የሚገልጽ ቃል ይጠቀም። መላሾችም ከመጀመሪያው ላይ “ወ” የሚል ፊደል በመጨመር “ወዐለይኩሙ ሰላም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ” (በናንተም ላይ የአላህ ሰላም፣ እዝነትና በረከት ይስፈን) ይበሉ።
#ሐዲሥ 132 / 851
ዒምራን ኢብኑ አል ሑሰይን رضي الله عنهما እንዲህ ሲሉ አስተላልፈዋል፦ አንድ ሰው ወደ ነቢዩ ﷺ መጣ። “አሰላሙ ዐለይኩም” አላቸው። መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩ ﷺ ፦ “አሥር” አሉት። ቀጥሎ ሌላ ሰው መጣና “አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላህ” በማለት ሰላምታ አቀረበ። መለሱለትና ተቀመጠ። ነቢዩም ﷺ፦ “ሃያ” አሉ። ከዚያም ሌላ ሰው መጣና፦ “አሰላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ” አለ። መለሱለትና ተቀመጠ። “ሠላሳ” አሉ። (አቡዳውድና ቲርሚዚ)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ መልክተኛው “አሥር” “ሃያ” “ሠላሳ” ያሉት ፣ ሰዎች የሚያገኙትን ምንዳ ለመግለጽ ነው። የመጀመሪያ “አሰላሙ ዐለይኩም” ብቻ በማለቱ አሥር ምንዳ አግኝቷል። ሁለተኛው “ወራሕመቱላህ” የሚል ቃል በመጨመሩ ሀያ ምንዳ አግኝቷል። ሦሥተኛው ሁለቱን በልጦ “ወበረካቱሁ” የሚል ቃል በማከሉ ሠላሳ ምንዳ አግኝቷል።
2/ እነዚህ የሰላምታ ዓይነቶች በሐዲሦች የተጠቀሱትን ያህል ምንዳዎች እንደሚያስገኝ ከዚህ ሐዲሥ እንማራለን።
#ሐዲሥ 132 / 852
ዓኢሻ እንዳስተላለፉት፣ የአላህ መልዕክተኛ “እነሆ ጂብሪል ሰላምታ ያቀርብልሻል” አሉኝ። እኔም “በርሱም ላይ የአላህ ሰላም፣ እዝነትና በረከት ይስፈን” በማለት መለስኩ። (ቡኻሪና ሙስሊም)
ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች
1/ የእመት ዓኢሻ ልቅና። የመላኢካ ሰላምታ ደርሷቸዋል።
2/ እገሌ ሰላም ብሎሃል ማለት ሸሪዓዊ ነው። መመለሱም ግዴታ ነው።
ቴሌግራም/ telegram/
https://t.me/ethiomuslim_1
107 viewsAm First, 14:36