Get Mystery Box with random crypto!

#ሕልምና_ከርሱ #ጋር #የተያያዙ_ነገሮች      #ክፍል_6 #ሐዲሥ 130 / 844 አቡል አስ | Muslim ሙስሊም

#ሕልምና_ከርሱ #ጋር #የተያያዙ_ነገሮች     
#ክፍል_6

#ሐዲሥ 130 / 844

አቡል አስቀዕ ዋሢለት ኢብኑ አል አስቀዕ እንዳስተላለፉት የአላህ መልዕክተኛ እንዲህ ብለዋል፦ “ከትልልቅ ቅጥፈቶች ውስጥ አንድ ሰው አባቱ ያልሆነውን አባቴ ነው ማለቱ፣ ወይም ዓይኖቹን ያላዩትን ሕልም ማሳየቱ ወይም በአላህ መልዕክተኛ ላይ ያላሉትን ማለቱ ነው።” (ቡኻሪ)

ከሐዲሡ የምንማራቸው ቁምነገሮች

1/ አባቱ ያልሆነውን አባቴ ነው በማለት ወደርሱ መጠጋት ትልቅ ጥፋት ነው። የዘር መቀላቀልን ይፈጥራል።
2/ በሕልም መዋሸት፣ ያላዩትን አየሁ ማለት ትልቅ ጥፋት ነው። ምክንያቱም በአላህ ላይ መዋሸት ነውና። በእውን መዋሸት በፍጡራን ላይ መዋሸት ነው። እርሱም ቢሆን ትልቅ ወንጀል ቢሆንም በአላህ ላይ መዋሸት ግን ይበልጥ አስከፊ ነው።
3/ በነቢዩ ላይ መዋሸትና እርሳቸው ያላሉትን እንዳሉ አድርጎ ማቅረብም ትልቅ ጥፋት ነው። ምክንያቱም ሰዎችን ወደ ማሳሳት እና ወደ ማጠመም ይመራልና። ወደ ሸሪዓው የርሱ አካል ያልሆነን ነገር ማስጠጋት ነውና።
ቴሌግራም
https://t.me/ethiomuslim_1