Get Mystery Box with random crypto!

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ L
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiolawtips
ምድቦች: ብድር, ግብሮች እና ህጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.61K
የሰርጥ መግለጫ

ስለቤተሰብ ሕግ ፣ስለንግድ ሕግ፣ስለወንጀል ሕግ፣ስለውርስ ሕግ፣ስለውል ሕግ ፣የሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
@lawyerhenoktaye 0953758395
🔔 👇
🛑 https://linktr.ee/lawyerhenok?

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-07-01 16:29:31
ምንጭ፡ www.fsc.gov.et

t.me/ethiolawtips
2.3K views13:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-18 16:44:27 ከባድ vs ቀላል የአካል ጉዳት
Cr. የሰ/መ/ቁ. 219862/ያልታተመ/
አንድ ሰው በሌላ ሰው ላይ በፈፀመው የድብደባ ድርጊት የአጥንት ስብራት መድረሱ ቢረጋገጥና ቆይቶ ስብራቱ መዳኑ ቢረጋገጥ ጉዳት ያደረሰው ሰው ጥፋተኛ ሊባል የሚገባው በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ሳይሆን በቀላል የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ነው። በከባድ የአካል ጉዳት ማድረስ ወንጀል ጥፋተኛ ለማለት ታሳቢ ሊደረግ የሚገባው ወንጀሉ ሲፈፀም የደረሰውን የጉዳት መጠን ሳይሆን በድብደባው ምክንያት የደረሰውን የመጨረሻ የጉዳት ውጤት ነው።
ሰ/መ/ቁ.156521፣የወንጀል ሕግ አንቀጽ 555፣የወንጀል ሕግ አንቀጽ 556
s - @ Daniel fikadu Law Office

t.me/ethiolawtips
6.6K viewsedited  13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-15 10:39:46 ከብድር ጋር በተገናኘ ብድር ከመክፈያ ጊዜዉ ሳይከፈል ከዘገዬ የሚታሰበዉ ወለድ እንጅ መቀጮ ሊታሰብ እንደማይገባ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2489(2) መሰረት ተመላክቷል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ59882 በሰጠዉ እና ቅፅ 12 ላይ በታተመዉ ዉሳኔ መሰረት ለዘገዬ ብድር ወለድ እንጅ መቀጮ አይከፈልም የሚል ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በቅርብ በሰበር ሰሚ ችሎቱ በሰ/መ/ቁ217051 በተሰጠ ዉሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2489(2) እና በቅፅ12 ላይ በሰፈረዉ በሰ/መ/ቁ 59882 የተሰጠዉ ዉሳኔ ተፈፃሚነት የሚኖረዉ በግለሰቦች መካከል የሚደረግ ብድር እንጅ በድርጅቶች መካከል የሚደረግን ብድር እንደማይመለከት፤ ብድሩ የተደረገዉ ከድርጅቶች ጋር ከሆነ ከወለድ በተጨማሪ መቀጮ ሊከፈል እንደሚገባ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡
6.3K viewsedited  07:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:57:37 ሰመ.ቁ. 219736 ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም የ ሁከት ተግባር ምንነት
የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) የሁከት ተግባርን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮችን ከመጥቀስ ባለፈ በራሱ “ሁከት” ለሚለው ቃል የሰጠው ግልፅ ትርጉም የለም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለውም የሁከት ተግባር የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ተብለው የተጠቀሱት ሁለት ድርጊቶች ናቸው፡፡ አንደኛው ባለይዞታው በሀብቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም መብቱ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት አልያም የሚፈጠር እንቅፋት (Interferance) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በባለይዞታው እጅ የነበረን ንብረት/ይዞታ/ በሙሉ ወይም በከፊል በመውሰድ ባለይዞታውን በዚያው መጠን ይዞታ አልባ ማድረግን (Dispossession) የሚመለከት ነው፡፡

በሌላ በኩል የሁከት ተግባሩ በሁለት መንገድ ሊፈፀም የሚችል ስለመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ከተደረጉ ጥናቶች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ አንደኛው ይዞታውን ከባለይዞታው እጅ በመውሰድ ወይም በይዞታው ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብት ላይ በተጨባጭ/በተግባር/ የሚፈፀም ጣልቃ ገብነት /Disturbance in fact/ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በባለይዞታው የይዞታ መብት ላይ በህግ ረገድ የሚፈጠር ሁከት/Disturbance in law/ የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው የሁከት ዓይነት አብዛኛውን ጊዜ የሚፈፀመው አስተዳደር ክፍል ይዞታውን በተመለከተ በራሱ ተነሳሽነትም ሆነ በሌላ ወገን ጠያቂነት በተለያየ መንገድ የባለይዞታውን የይዞታ መብት በሚነካ መልኩ በሚወሰደው አስተዳዳራዊ እርምጃ ነው፡፡ ይህ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደየሁኔታው ባለይዞታው ይዞታውን በተመለከተ አንድን ድርጊት እንዲፈፅም ወይም እንዳይፈፅም በማድረግ አልያም የባለሃብትነት መብቱን የሚያሳጣ ተግባር በመፈፀም ሊሆን ይችላል፡፡

በእነዚህ ሁኔታዎች በይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ባለይዞታ የተወሰደበት ነገር እንዲመለስለት ወይም የተነሳው ሁከት እንዲወገድለት እና በድርጊቱ ስለደረሰው ጉዳት ኪሳራ እንዲሰጠው በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ እና ዳኞችም ይኸው ስለመፈፀሙ ሲያረጋገጡ የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድ እና ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ካሳ እንዲከፈል ሊወስኑ እንደሚችሉ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149 ድንጋጌ ጠቅላላ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
@habeshaadvocatesllp

t.me/ethiolawtips
6.9K views04:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:50:45 ሰመ.ቁ. 219736 ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም የ ሁከት ተግባር ምንነት
የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) የሁከት ተግባርን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮችን ከመጥቀስ ባለፈ በራሱ “ሁከት” ለሚለው ቃል የሰጠው ግልፅ ትርጉም የለም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለውም የሁከት ተግባር የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ተብለው የተጠቀሱት ሁለት ድርጊቶች ናቸው፡፡ አንደኛው ባለይዞታው በሀብቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም መብቱ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት አልያም የሚፈጠር እንቅፋት (Interferance) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በባለይዞታው እጅ የነበረን ንብረት/ይዞታ/ በሙሉ ወይም በከፊል በመውሰድ ባለይዞታውን በዚያው መጠን ይዞታ አልባ ማድረግን (Dispossession) የሚመለከት ነው፡፡

በሌላ በኩል የሁከት ተግባሩ በሁለት መንገድ ሊፈፀም የሚችል ስለመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ከተደረጉ ጥናቶች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ አንደኛው ይዞታውን ከባለይዞታው እጅ በመውሰድ ወይም በይዞታው ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብት ላይ በተጨባጭ/በተግባር/ የሚፈፀም ጣልቃ ገብነት /Disturbance in fact/ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በባለይዞታው የይዞታ መብት ላይ በህግ ረገድ የሚፈጠር ሁከት/Disturbance in law/ የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው የሁከት ዓይነት አብዛኛውን ጊዜ የሚፈፀመው አስተዳደር ክፍል ይዞታውን በተመለከተ በራሱ ተነሳሽነትም ሆነ በሌላ ወገን ጠያቂነት በተለያየ መንገድ የባለይዞታውን የይዞታ መብት በሚነካ መልኩ በሚወሰደው አስተዳዳራዊ እርምጃ ነው፡፡ ይህ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደየሁኔታው ባለይዞታው ይዞታውን በተመለከተ አንድን ድርጊት እንዲፈፅም ወይም እንዳይፈፅም በማድረግ አልያም የባለሃብትነት መብቱን የሚያሳጣ ተግባር በመፈፀም ሊሆን ይችላል፡፡

በእነዚህ ሁኔታዎች በይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ባለይዞታ የተወሰደበት ነገር እንዲመለስለት ወይም የተነሳው ሁከት እንዲወገድለት እና በድርጊቱ ስለደረሰው ጉዳት ኪሳራ እንዲሰጠው በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ እና ዳኞችም ይኸው ስለመፈፀሙ ሲያረጋገጡ የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድ እና ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ካሳ እንዲከፈል ሊወስኑ እንደሚችሉ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149 ድንጋጌ ጠቅላላ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
@habeshaadvocatesllp
t.me/ethiolawtips
4.4K views04:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 07:49:34
ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማከናወን ወንጀል ሰ/መ/ቁ 211028
ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማከናወን ወንጀል ጋር በተያያዘ የድርጅት ሥራ አስኪያጅ የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ለሌላ ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ስራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም።

አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው በአንቀጽ 56/1/፤ አንቀጽ 22/1/ እና አንቀጽ 50/ለ/1 መሠረት የአንድ የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው እሱ የሚመራው ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ፤ የድርጅቱ ሃላፊነት ከተረጋገጠ የሥራ አስኪያጁ ሃላፊነት የሕግ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ እንገነዘባለን።
4 ለ 1 አብለጫ ድምጽ የተሰጠ
የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁ 983/08 አንቀጽ 131(1)(ለ)፤ 131(1)(ለ)፤ 128
@habeshaadvocatesllp
t.me/ethiolawtips
3.5K views04:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 15:25:09 ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce)
=====================
ጋብቻ የቤተሰብ መሰረት በመሆኑ በህግ እውቅና የተሰጠው እና ከምስረታው ጀምሮ ጥበቃ የሚደረግለት ተቋም ነው፡፡ በዚህም የሚፈርስበት ሁኔታ ጭምር በቤተሰብ ህጉ በግልፅ ተመላክቷል፡፡ በተሻሻለው የፌደራል የቤተሰብ ህግ እንደተደነገገው ጋብቻ የሚፈርሰው ከተጋቢዎች አንዱ ሲሞት ወይም በፍርድ ቤት የመጥፋት ውሳኔ ሲሰጥ፣ ጋብቻ ለመፈፅም መሟላት ካለባቸው ሁኔታዎች አንዱ በመጣሱ ምክንያት በህግ መሰረት ጋብቻ እንዲፈርስ ሲወሰን ወይም የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ ነው፡፡ በዚህ አጭር ፅሁፍ በቤተሰብ ህጉ ፍቺ የሚፈፀምባቸውን ሁኔታዎች እና በፍርድ ቤት ሳይወሰን ተለያይቶ መኖር በህጉ የሚስተናገድበትን ሁኔታ እንመለከታለን፡፡

ፍቺ የሚፈፀምበት ሁኔታ

ጋብቻ በፍቺ እንዲፈርስ ሊወሰን የሚችለው ባልና ሚስት በስምምነት ለመፋታት ሲወስኑና ይህንኑ ለፍርድ ቤት አቅርበው ውሳኔያቸው ተቀባይነት ሲያገኝ እና ከተጋቢዎቹ አንዱ ወይም ሁለቱም ተጋቢዎች በአንድነት ጋብቻቸው በፍቺ እንዲፈርስ ለፍርድ ቤት ጥያቄ ሲያቀርቡ ነው፡፡ ጋብቻ በስምምነት ሲፈርስ ፍርድ ቤት የፍቺ ስምምነቱን የሚያፀድቀው የባልና ሚስቱ ትክክለኛ ፍላጎት መሆኑን እንዲሁም ስምምነቱ ከህግና ሞራል ጋር የማይቃረን መሆኑን ሲያምን ነው (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ (አንቀጽ 80 ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2)፡፡ ፍርድ ቤቱ የፍቺን ስምምነት ያፀደቀው እንደሆነ ስለፍቺው ውጤት ያደረጉትንም ስምምነት አብሮ ሊያፀድቀው የሚችል ሲሆን ባልና ሚስቱ ስለፍቺ ውጤት ያደረጉት ስምምነት የልጆቻቸውን ደህንነትና ጥቅም በበቂ ሁኔታ የማያስጠብቅ ወይም የአንደኛውን ተጋቢ ጥቅም የሚጎዳ ሆኖ ካገኘው ፍርድ ቤት የፍቺውን ስምምነት ብቻ በማፅደቅ የፍቺውን ውጤት በተመለከተ ጉድለቶቹ እንዲስተከካሉ ተገቢ መስሎ የታየውን ውሳኔ ይሰጣል (የቤተሰብ ህግ አንቀፅ 80/3)። በመሆኑም ጋብቻ በፍቺ የሚፈርሰው ፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሲሰጥ መሆኑን መረዳት ይቻላል::

ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce) ምንነት

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በ1999 ዓ.ም በሰበር መዝገብ ቁጥር 20938 ሰጥቶት በነበረው ውሳኔ መሰረት ሳይፋቱ ፍቺ ማለት በፍርድ ቤት የፍቺ ውሳኔ ሳይሰጥበት ባልና ሚስት ለበርካታ ዓመታት ተለያይተው በመኖር፣ የየራሳቸውን ሕይወት እየኖሩ (አግብተው ወይም ሳያገቡ) ከቆዩ፣ ምንም እንኳን ቀደም ብሎ የተፈጸመ ጋብቻ የነበራቸው ቢሆንም ሁለቱም በየፊናቸው የየራሳቸውን ሕይወት መጀመራቸው ከተረጋገጠ ጋብቻቸው እንደፈረሰ የሚቆጠርበትን ሁኔታ የሚያመለክት ነው፡፡

ሳይፋቱ ፍቺ (Defacto Divorce) በኢትዮጵያ ህግ የሚታይበት ሁኔታ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠው ውሳኔ በሥር ፍርድ ቤቶች ላይ አስገዳጅ በመሆኑ ምክንያት ችሎቱ የሰጠው የህግ ትርጉም ሥራ ላይ ሲውል የቆየ ቢሆንም በርካታ ሴቶች ሀብት ንብረታቸውን እንዳሳጣቸው ቅሬታ ሲቀርብበት ቆይቷል፡፡ ይኸውም በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79 ሕግ የመተርጎም ሥልጣን ለፍርድ ቤት፣ በአንቀጽ 55 ደግሞ ሕግ የማውጣት ሥልጣንን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተሰጠ ቢሆንም ሰበር ሰሚ ችሎት ግን ከሕጉ ዓላማ ውጪ የሆነ አስገዳጅ ትርጉም መስጠቱ ሕገ መንግሥቱን እንደሚቃረን በመጥቀስ ለህገ መንግስት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አቤቱታ ቀርቧል፡፡

ሰበር ሰሚ ችሎት በውሳኔው ጋብቻ ሊፈርስ የሚችልባቸውን ምክንያቶች በተመለከተ በተሻሻለው የቤተሰብ ሕግ አንቀጽ 75 እና 82 የተመለከቱ ድንጋጌዎችን በማለፍ አራተኛ ምክንያት ማስቀመጡም ተገቢ አለመሆኑ፣ የጋብቻን ፍቺ የመወሰንና የጋብቻው በፍቺ መፍረስ የሚያስከትለውን ውጤት የመወሰን ሥልጣን የፍርድ ቤት ብቻ ሆኖ የተደነገገበት የራሱ ዓላማ ያለው መሆኑን፣ ጋብቻ በፍቺ ሲፈርስ የተጋቢዎችን የንብረት ክፍፍልና የሕፃናትን የአስተዳደግ ሁኔታ አገናዝቦ ውሳኔ መስጠት ያለበት ፍርድ ቤት መሆኑ እንዲሁም ተጋቢዎች ተለያይተው በመኖራቸውና የየራሳቸውን ሌላ ሕይወት በመጀመራቸው ‹‹ጋብቻቸው ፈርሷል›› የሚል መደምደሚያ ላይ መድረስ ተጋቢዎች በቸልተኝነት ጋብቻቸውን ከፍርድ ቤት ዕውቅና ውጪ በፍቺ መልክ እንዲያቋርጡ መንገድ የሚከፍትና ሕገ-ወጥነትን የሚያበረታታ መሆኑ ቅሬታው ተቀባይነት እንዲያገኝ ያስቻሉ ምክንያቶች ናቸው፡፡

በመሆኑም የሰበር ሰሚ ችሎቱ አስገዳጅ ውሳኔ ከሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 55 ከተመለከተው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሥልጣንና ተግባር፣ በአንቀጽ 51 ከተመለከተው የፌዴራል መንግሥት ሥልጣንና ተግባር ድንጋጌዎች ጋር የሚጋጭ ሆኖ ስላገኘው የሕገ መንግሥት ትርጉም እንዲሰጥበት ጉባዔው በሙሉ ድምፅ በመወሰን በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 84(1) እና በአዋጅ ቁጥር 798/2005 አንቀጽ 3(1) ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳቡን አቅርቧል፡፡ ፌዴሬሽን ምክር ቤትም የቀረበለትን የውሳኔ ሐሳብ በመቀበልና ይሁንታ በመስጠት አስገዳጁን የሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ ሰርዞ ጋብቻ ሊፈርስባቸው ከሚችሉ ሦስት በህግ ከተመለከቱ ምክያቶች ውጪ ዝም ብሎ መለያየትና መቆየት ጋብቻን ሊያፈርስ እንደማይችል በፌደሬሽን ምክር ቤት 5ኛ የፓርላማ ዘመን፣ 5ኛ ዓመት፣ 1ኛ መደበኛ ጉባዔ መስከረም 27 ቀን 2012 ዓ.ም የመዝገብ ቁጥር 49/10 ውሳኔ ሰጥቷል፡፡ የፌዴሬሽን ምክር ቤትን ለማጠናከርና ሥልጣንና ተግባሩን ለመዘርዘር በወጣው አዋጅ ቁጥር 251/93 አንቀጽ 11/1 እና 56 መሰረት በህገ-መንግስት ትርጉም ላይ ምክር ቤቱ የሚሰጠው የመጨረሻ ውሳኔ አጠቃላይ ውጤት የሚኖረው ሲሆን ወደፊት በሚወሰኑ ተመሳሳይ ህገ-መንግስታዊ ጉዳዮች ላይ የአስገዳጅነት ባህርይ ይኖረዋል፡፡ ስለሆነም ምክር ቤቱ በቀረበለት ጉዳይ ላይ የሚሰጠው ውሳኔ የመጨረሻ ሲሆን ጉዳዩ የሚመለከታቸው ወገኖች ውሳኔውን የማክበርና የመፈፀም ግዴታ ይኖርባቸዋል፡፡

በአጠቃለይ የጋብቻ መፍረስ በልጆች እና በንብረት አስተዳደር ላይ ውጤት ያለው በመሆኑ በህጉ የተቀመጡትን የጋብቻ መፍረስ ምክንያቶች ብቻ መከተል ግዴታ መሆኑን የፌደሬሽን ምክር ቤት ከሰጠው የህገ-መንግስት ትርጉም መረዳት ይቻላል፡፡ ስለሆነም በጋብቻ ውስጥ ያሉ ሰዎች መለያየት ከፈለጉ በህጉ መሰረት ፍቺ መፈፀም ይኖርባቸዋል፡፡

በፍትህ ሚኒስቴር በንቃተ ህግ ትምህርትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት የተዘጋጀ
t.me/ethiolawtips
3.9K views12:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-08 15:10:29 ክስ ይዛወርልኝ

• በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ የግዛት ስልጣን በሌለው ሌላ ፍርድ ቤት ወይም በዛው ፍርድ ቤት በሌላ ችሎት ተዛውሮ እንዲታይ በመጠየቅ በተከራካሪዎች የሚቀርብ አቤቱታ

በአንድ ወረዳ ፍ/ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ ወደ ሌላ ወረዳ ፍ/ቤት ተዛውሮ እንዲታይ አንደኛው ወገን ሲያመለክት ተገቢ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጦ በክስ ይዛወርልኝ አቤቱታው እንደየሁኔታው አግባብነት ያለው ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31 ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ለማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ በስር ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ ፋይል ባልተከፈተበት ወይም ቀድሞ የተዘጋ መዝገብ ባልተንቀሳቀሰበት ሁኔታ የሚቀርብ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 93171 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 31

የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ /Change of Venue/ የሚስተናገድበትን አግባብ ህጉ የዘረጋው ስርዓት ያለ ሲሆን በ1958ቱ የፍትሐብሔር ስነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 31 ስር የተመለከተው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ህግ በኋላ በፌደራልም ሆነ በክልሎች የወጡት የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጆች ተመሣሣይ ይዘት ያለውን ድንጋጌ ስራ ላይ አውለው ይገኛል፡፡ አንድ ክስ ወደ ሌላ ስፍራ ሊዛወር የሚችልበትን አግባብ ከሚደነግጉት የስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ጥያቄው ከተከራካሪ ወገኖች የሚቀርብ መሆኑና ህጋዊ ምክንያቶች ተብለው በህጉ ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ መሟላት ያለበት መሆኑን ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 66945 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
31
ኢትዮ-ሕግ Ethio-Law
ለቴሌግራም መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
https://t.me/EthioLawtips
9.0K viewsedited  12:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 20:05:12 ከውርስ በዝምታ ወይም ያለበቂና ህጋዊ ምክንያት የተነቀለ የመጀመሪያ ደረጃ ወራሽ ከጠቅላላ የኑዛዜ ተጠቃሚ ጋር እኩል ወራሽ ሆኖ የሟችን የውርስ ሃብት ሊካፈል የሚገባ ስለመሆኑ፣
ሟች ካለው ሃብት እጅግ አነስተኛ የሆነ ንብረት /ሀብት/ ለተወላጁ በኑዛዜ የሰጠ እንደሆነ በውጤት ደረጃ ተወላጁ የተነቀለ መሆኑን መገንዘብ የሚቻልና ተወላጁ ከሌሎች የጠቅላላ ኑዛዜ ተጠቃሚዎች ጋር እኩል መካፈል ያለበት ስለመሆኑ የፍ/ብ/ህ/ቁ. 912, 938, 939, 915, 1014 እና 1123 ላይ ከተቀመጡት ድንጋጌዎች ግንዛቤ መውሰድ ይቻላል ። ቅጽ/11 ሰ/መ/ቁ/58338
t.me/ethiolawtips
share #Join
1.8K viewsedited  17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-04 19:55:34 አውራሽ/ሟች/ በህይወት እያለ ከይዞታ ቦታው ላይ ለሌላ ሠው ቤት እንዲሠራ ፈቅዶ ቢሰጠው ሟች በሚሞትበት ጊዜ በሟች ፈቃድ ቤት የሠራው የቤቱ ባለቤት እንደሚሆንና ከሌላው ቦታ ጋር ሆኖ የውርስ ክፍል የሚሆን ስላለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 826/2/ እና 1179/1/። ሰ/መ/ቁ-96628 ቅፅ-17.
በመሆኑም ፈቅዶ የሰጠው ሟች የቦታውን መብት ለባለ ሀብቱ እያስተላለፈ /እያጠ/ ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ/826/2/ መሰረት አውራሻቸው የሌለው መብት ለወራሾች ሊተላለፍ የሚችልበት የሕግ መሠረት የለም፡፡በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1179(1) መሠረት ባለመብት የሚሆነው አውራሽ ሳይቃወመው በራሱ ወጭ በሠራቸው ቤቶችና ቤቶቹ በተሰሩበት ወይም ባረፉበት ቦታ ላይ ብቻ ይሆናል ።ይህ ቦታም የውርስ ሀብት ክፍል በሆኑ ንብረቶቹ ውስጥ ሊካተት አይችልም ።
t.me/ethiolawtips
Share #Join
1.9K viewsedited  16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ