Get Mystery Box with random crypto!

ክስ ይዛወርልኝ • በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ የግዛት ስልጣን በሌለው | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ክስ ይዛወርልኝ

• በመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ የግዛት ስልጣን በሌለው ሌላ ፍርድ ቤት ወይም በዛው ፍርድ ቤት በሌላ ችሎት ተዛውሮ እንዲታይ በመጠየቅ በተከራካሪዎች የሚቀርብ አቤቱታ

በአንድ ወረዳ ፍ/ቤት በመታየት ላይ ያለ ጉዳይ ወደ ሌላ ወረዳ ፍ/ቤት ተዛውሮ እንዲታይ አንደኛው ወገን ሲያመለክት ተገቢ ምክንያቶች መኖራቸው ተረጋግጦ በክስ ይዛወርልኝ አቤቱታው እንደየሁኔታው አግባብነት ያለው ውሳኔ ሊሰጥ የሚችል ስለመሆኑ በፍ/ብ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 31 ተመልክቷል፡፡ በዚህ ድንጋጌ መሰረት የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ ለማቅረብ ጉዳዩ በክርክር ሂደት ላይ የሚገኝ መሆን ይኖርበታል፡፡ በስር ፍ/ቤት ክስ ተመስርቶ ፋይል ባልተከፈተበት ወይም ቀድሞ የተዘጋ መዝገብ ባልተንቀሳቀሰበት ሁኔታ የሚቀርብ የክስ ይዛወርልኝ አቤቱታ የክስ ምክንያት የለውም፡፡

ሰ/መ/ቁ. 93171 ቅጽ 16፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ. 31

የክስ ይዛወርልኝ ጥያቄ /Change of Venue/ የሚስተናገድበትን አግባብ ህጉ የዘረጋው ስርዓት ያለ ሲሆን በ1958ቱ የፍትሐብሔር ስነ ሥርዓት ህግ አንቀጽ 31 ስር የተመለከተው አንዱ ነው፡፡ ከዚህ ህግ በኋላ በፌደራልም ሆነ በክልሎች የወጡት የፍርድ ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጆች ተመሣሣይ ይዘት ያለውን ድንጋጌ ስራ ላይ አውለው ይገኛል፡፡ አንድ ክስ ወደ ሌላ ስፍራ ሊዛወር የሚችልበትን አግባብ ከሚደነግጉት የስነ ስርዓት ህግ ድንጋጌዎች ይዘትና መንፈስ መገንዘብ የሚቻለው ደግሞ ጥያቄው ከተከራካሪ ወገኖች የሚቀርብ መሆኑና ህጋዊ ምክንያቶች ተብለው በህጉ ከተመለከቱት ሁኔታዎች ውስጥ አንዱ መሟላት ያለበት መሆኑን ነው፡፡

ሰ/መ/ቁ. 66945 ቅጽ 11፣ ፍ/ስ/ስ/ህ/ቁ.
31
ኢትዮ-ሕግ Ethio-Law
ለቴሌግራም መረጃ ሊንኩን ይጫኑ
https://t.me/EthioLawtips