Get Mystery Box with random crypto!

Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ L
የቴሌግራም ቻናል አርማ ethiolawtips — Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ
የሰርጥ አድራሻ: @ethiolawtips
ምድቦች: ብድር, ግብሮች እና ህጎች
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 10.61K
የሰርጥ መግለጫ

ስለቤተሰብ ሕግ ፣ስለንግድ ሕግ፣ስለወንጀል ሕግ፣ስለውርስ ሕግ፣ስለውል ሕግ ፣የሰበር አስገዳጅ የሕግ ትርጉሞች የሚያገኙበት ቻናል ነው።
@lawyerhenoktaye 0953758395
🔔 👇
🛑 https://linktr.ee/lawyerhenok?

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

2

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 4

2023-02-13 15:09:27
ሰ/መ/ቁ 35962 (ያልታተመ)
ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል ፊት ያልተደረገ የቤት ሽያጭ ውል መሰረት በማድረግ ገዢ ቤቱን የሚመለከቱ ማንኛውም ሰነዶች እንዲያስረክበው በሻጭ ላይ ክስ አቅርቦ ጉዳዩን የሚያየው ፍርድ ቤት የቤት ሺያጭ ውሉ በፍ/ሕ/ቁ. 1723 መሰረት በዳኛ ወይም ውል ለማዋዋል ስልጣን በተሰጠው ሰው ፊት ባለመደረጉ የህግ ውጤት የለውም የሚል ድምዳሜ ላይ ከደረሰ ሻጭ ሰነዶችን ለማስረከብ እንደማይገደድ ከመወሰን አልፎ የሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ ውሳኔ ሊሰጥ አይገባም። ምክንያቱም የቤት ሽያጭ ውሉ እንዲፈርስ የቀረበ የዳኝነት ጥያቄ ባለመኖሩ ፍ/ቤቱ በዝርዝር ባልቀረበ ወይም በግልጽ ባልተጠየቀ ጉዳይ ላይ ውሣኔ መስጠቱ የፍ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ. 282/2/ የሚቃረን ነው።
habeshaadvocatellp
t.me/ethiolawtips
1.0K views12:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-08 13:56:38
ሰ/መ/ቁጥር 222681 ጥቅምት 04 ቀን 2015 ዓ/ም

የቤት ሽያጭ ውሉ በውል አዋዋይ ፊት ያልተደረገ ከሆነ በውሉ ላይ የሰፈሩት ማናቸውም የውል ቃሎች ፊርማን ጨምሮ ያለቅድመ ሁኔታ በሰነዱ ላይ በሰፈሩበት አግባብ የሚታመኑ ሳይሆኑ በሌላ አግባብነት ባለው ማንኛውም ማስረጃ ሊስተባበሉ የሚችሉ ናቸው፡፡
በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 2005/1 ስር በጽሑፍ ሰነድ ላይ የሚገኝ የስምምነት ቃል እንዲሁም በላዩ ላይ የተጻፈው ቀን በፈራሚዎቹ መካከል ሙሉ እምነት የሚጣልበት በቂ ማስረጃ ነው የሚለው በፍ/ብ/ሕግ ቁጥር 1678/ሐ፣1719/2 እና 1723/1 ስር በተደነገገው መሰረት በሕግ የታዘዘውን የአጻጻፍ ሥርዓት ተከትሎ ለተደረገ ውል እንጂ ለማንኛውም ውል አይደለም፡፡
@habeshaadvocatesLLp

t.me/ethiolawtips
2.1K views10:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-02 18:37:24
ሰ/መ/ቁጥር 215444
ጥቅምት 02 ቀን 2015 ዓ/ም
በውልና ማስረጃ ምዝገባ ጽ/ቤት ሳይመዘገብ በተወካይ አማካይነት የተደረገ የቤት ሽያጭ ውል ውሉ ስለመደረጉ በተወካዩ ታምኖ ሆኖም ወካዩ ውል መኖሩን ከካደ ህጋዊ ውጤት አይኖረውም።
ውሉ ፈርሶ ተዋዋዮች ወደነበሩበት መመለስ ይኖርባቸዋል።
t.me/ethiolawtips
4.4K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-01 17:52:41

3.9K views14:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-31 11:58:45 ፨ የሰ/መ/ቁ 191963 [ቅፅ 25]

አስቀድሞ ከዉርስ ንብረት የተቀበለ ወራሽ የዉርስ ክፍፍል ፋይል ሲከፈት የዉርስ ሀብቱን ለመዉረስ ካልጠየቀ አስቀድሞ የወሰደዉን ንብረት ወደ ዉርስ ሀብት መልሶ ለመዉረስ የሚገደድበት አግባብ የለም ።
t.me/ethiolawtips
4.4K views08:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-28 00:22:49 የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሕግ ትርጉም የሰጠባቸው ውሣኔዎች ዝርዝር ማውጫ ሰንጠረዥ ከቅጽ 1 እስከ 25
በ፦ ዋስይሁን ኃይለማርያም እና የኋላሸት ታምሩ
source Abyssinialaw.com
Join
t.me/ethiolawtips
6.0K viewsedited  21:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-25 14:43:52 ውል መሰረዝ፤ ማፍረስ እና በስምምነት ማቋረጥ
ውል መሰረዝ
ከተዋዋይ ወገኖች መካከል አንደኛው እንደ ውሉ ባለመፈጸሙና የውሉን ግዴታ በመጣሱ በተዋዋዩ ወይም በፍርድ ቤት ውሉን ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች ቀሪ ማድረግ
ውል የሚሰረዘው ከመሠረቱ ግድፈት ስላለው አይደለም፡፡ ይልቁንም የውል መሠረዝ ምክንያት ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታን ከመፈፀምና ካለመፈፀም ጋር ተያይዞ የሚከሠት ነው፡፡ የውል መሠረዝ ሥርዓትም የራሱ የሆነ አካሄድ አለው፡፡ ይኸውም ውሉን የመሠረዝ ፍላጐት ያለውን ወገን የውሉ ግዴታ ባለመፈፀሙ የተነሳ ከህግ ወይም ከውሉ ከራሱ ባገኘው መብት ተጠቅሞ ውሉን ሊሰርዝ ይችላል፡፡ ይህ መብት ተግባራዊ የሚሆንበት አጋጣሚም ግዴታው ባለመፈፀሙ የተነሳ የደረሰውን ጉዳት ከማረጋገጥ ጋር ተያይዞ የሚታይ እንጂ ጥያቄ አቅራቢው ሁል ጊዜ ተቀባይነት የሚያገኝበት አይደለም፡፡ በመሆኑም የውል ይሰረዝልኝና ተያያዥነት ያላቸው ጥያቄዎች በህጉ አግባብ የሚስተናገዱ ስለመሆኑ የፍ/ህ/ቁ. 1784 እና ተከታዮቹ ድንጋጌዎች ያስገነዝባሉ፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በተናጠል መሰረዝ
አንደኛው ተዋዋይ ወገን የፍታብሓር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን መሠረት በማድረግ ውልን በተናጠል ለመሠረዝ የሚችለው ከሚከተለት ሶስት ሁኔታዎች አንደኛው የተሟላ መሆኑን ለማስረዳት ሲችል ነው፡፡
• የመጀመሪያው ባለዕዳው በውሉ ላይ በተመለከተው መሠረት የውሉን ግዴታ የሚፈፅምበት ቁርጠኛ ጊዜ በውሉ ላይ በግልፅ ተመልክቶ እንደሆነና በውሉ ላይ የተገለፀው ቁርጥ የሆነ የውል መፈፀሚያ ጊዜ ያለፈ እንደሆነ ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ አንደኛው ተዋዋይ ወገን በተናጠል ውሉን ለመሰረዝ የሚችል መሆኑን የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1775(ለ) ድንጋጌዎች በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
• ሁለተኛው ምክንያት ባለዕዳው ውሉን ያልፈፀመበትን ምክንያትና ሌሎች የአካባቢ ሁኔታዎችን በማገናዘብ ዳኞች ባለዕዳው ውሉን የሚፈፅምበት የችሮታ ጊዜ ከሰጡት በኋላ ባለእዳው በዳኛ ውሣኔ በተሰጠው የችሮታ ጊዜ ውስጥ ግዴታውን ሳይፈጽም የቀረ እንደሆነ መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1770 ድንጋጌዎች ለመረዳት ይቻላል፡፡
• ሶስተኛው ባለገንዘቡ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 በተደነገገው መሠረት ሌላኛው ተዋዋይ (ባለዕዳው) በውል የገባውን ግዴታ የሚፈፅምበትን ጊዜ በመግለፅ ማስጠንቀቂያ የሰጠ ሲሆንና በማስጠንቀቂያው በተሰጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ ሳይፈፅም ሲቀር መሆኑን ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ለመረዳት ይቻላል፡፡ አንደኛው ተዋዋይ ወገን ሌላኛው ተዋዋይ ወገን በውሉ መሠረት እንዲፈፅም ለመጠየቅና ማስጠንቀቂያ ለመስጠት የሚችለው በመጀመሪያ እሱ የበኩሉን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም የተዘጋጀ ሲሆን እንደሆነ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1857 በግልፅ ይደነግጋል፡፡
ስለሆነም ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ መሠረታዊ ዓላማና ግብ እንደዚሁም የድንጋጌውን የተፈፃሚነት ወሰን ለመረዳት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌ ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 እና ከፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 ድንጋጌዎች ጋር በማጣመር መመርመር ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ አንፃር ስንመዝነው አንደኛው ተዋዋይ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771 ንዑስ አንቀጽ 1 ሌላኛው ተዋዋይ ውሉን እንዲፈፅምለት ለመጠየቅ፤ በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774 ድንጋጌዎች መሠረት የውል መፈፀሚያ ጊዜ ግልፅ ማስጠንቀቂያ በመስጠትና በፍትሐብሔር ቁጥር 1787 በተደነገገው መሠረት ውሉን በተናጠል ለመሠረዝ በመጀመሪያ በእሱ በኩል በውል የተጣለበትን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ በማስረጃ ለማረጋገጥ የቻለ መሆን እንዳለበት የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1771፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1774፣ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1757 እና የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌዎችን ይዘትና መሠረታዊ ግብ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሕግ አውጭው በውል ለገባው ግዴታ ተገዥ በመሆን በእሱ በኩል ያለውን ግዴታ ያልፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑን በበቂ ሁኔታ ለማረጋገጥ ያልቻለ አንድ ተዋዋይ ወገን ሌላኛውን ተዋዋይ ወገን ቀድሞ ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውሉን በተናጠል እንዲሰርዝ በማሰብ የፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1787 ድንጋጌን አውጇል ተብሎ አይገመትም፡፡ አንድ ተዋዋይ የውሉን መፈፀሚያ የጊዜ ገደብ በመግለጽ ለሌላኛው ወገን ማስጠንቀቂያ በመስጠት ውል በተናጠል ለመሰረዝ የሚችለው በመጀመሪያ እሱ በውሉ የገባውን ግዴታ የፈፀመ ወይም ለመፈፀም ዝግጁ መሆኑ ሲረጋገጥ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 57280 ቅጽ 13፣ ፍ/ህ/ቁ. 1770፣ 1771፣ 1774፣ 1757፣ 1787
ውል ማፍረስ
በህጉ የተቀመጡት የውል አመሰራረት መስፈርቶችን ያለሟላና ግድፈት ያለበት በመሆኑ የተነሳ የውሉ ወይም በውሉ የተቋቋሙትን ግዴታዎች መቅረት
ውል ማፍረስና ውል መሠረዝ በውል የተቋቋሙት ግዴታዎች ከሚቀሩባቸው መንገዶች ውስጥ የሚካተቱ ቢሆንም ምክንያታቸውና ውጤታቸው የተለያዩ ነው፡፡ የውል ማፍረስ ከውል አመሠራረት ጋር ተያይዞ የሚነሳ ሲሆን ሲሆነ
ውሉ ከአመሰራረቱ በህጉ የተመለከቱትን ሁኔታዎች ባለማሟላቱ ግድፈት ያለበት መሆኑን የሚያሳይ ነው፡፡ በሌላ በኩል የውል መሰረዝ ጉዳይ ከውል አመሰራረት ችግር የሚነሳ ሳይሆን ከተዋዋይ ወገኖች የውል ግዴታውን ካለመወጣት የሚመነጭ ነው፡፡
ሰ/መ/ቁ. 32299 ቅጽ 8
ውል በስምምነት ማቋረጥ /ቀሪ ማድረግ/
ተዋዋይ ወገኖች በውል አቋቁመውት የነበረውን ግዴታ በፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 1 መሠረት በስምምነት ቀሪ ሲያደርጉ የተለየ ፎርም መከተል እንዳለባቸው የሚደነግግ አስገዳጅ ድንጋጌ የለም፡፡ የውለታ በተዋዋዮች ስምምነት መቋረጥ (terminate) መደረግ ከውል መፍረስ ወይም ከውል መሠረዝ የተለየ ባህሪና ውጤት ያለው መሆኑን አግባብነት ያላቸውን የፍታብሔር ድንጋጌዎች ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡ እንደዚሁም ውል በስምምነት ቀሪ ማድረግ (termination of contract) ውልን ከማሻሻል (ውል ከመለወጥ) (variation of contract) እና ውል ከመተካት (Novation of contract) የተለየ ባህሪ፣ ይዘትና ውጤት ያለው መሆኑን፣ የፍታሐብሔር ሕግ ቁጥር 1819 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን፣ የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1722 እና የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1826 እና ተከታይ ድንጋጌዎችን ይዘት በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
የውሉ በተዋዋዮቹ ፈቃድና ስምምነት መቋረጥ (ቀሪ) መሆን የተዋዋይ ወገኖች የወደፊት የውል የመፈፀም ግዴታ የሚያስቀር መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 2 ይደነግጋል፡፡ እንደዚሁም የውሉ መቋረጥ /ቀሪ/ መሆን ያለፈውን ሁኔታ የማይነካ መሆኑን የፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1819 ንዑስ አንቀጽ 3 ይደነግጋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የውል ቀሪ መሆን (termination of contract) ተዋዋዮቹ በውል አቋቋመውት የነበረውን መብትና ግዴታ ቀሪ የማድረግ ውጤት የሚኖረው መሆኑን ከፍታብሔር ሕግ ቁጥር 1807 /ለ/ ድንጋጌ ይዘት መንፈስና ዓላማ በማገናዘብ ለመረዳት ይቻላል፡፡
ሰ/መ/ቁ. 63063 ቅጽ 14፣ ፍ/ህ/ቁ. 1682-84፣ 1722
በአብላጫ ድምፅ የተሰጠ
t.me/ethiolawtips
6.7K viewsedited  11:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-22 10:58:20
የሰበር መዝ/ቁ 212950
``````````ያልታተመ``````````
በወንጀል የማስረጃ ምዘና መርህ የተከሳሽ ሀላፊነት
~~~
በወንጀል የማስረጃ ምዘና መርህ መሰረት ከተከሳሽ የሚጠበቀው የማስረዳት ደረጃ እንደ ዐቃቢ ህግ ከምክንያታዊ ጥርጣሬ በፀዳ መልኩ ማስተባበል ወይም በቂ እና አሳማኝ በሆነ መልኩ ማስረዳት ሳይሆን በቀረቡት የዐቃቢ ህግ ማስረጃዎች ቃል እና በወንጀሉ መፈፀም ላይ "ጥርጣሬ መፍጠር" ብቻ ነው።
share
t.me/ethiolawtips
6.4K views07:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ