Get Mystery Box with random crypto!

ከብድር ጋር በተገናኘ ብድር ከመክፈያ ጊዜዉ ሳይከፈል ከዘገዬ የሚታሰበዉ ወለድ እንጅ መቀጮ ሊታሰ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ከብድር ጋር በተገናኘ ብድር ከመክፈያ ጊዜዉ ሳይከፈል ከዘገዬ የሚታሰበዉ ወለድ እንጅ መቀጮ ሊታሰብ እንደማይገባ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 2489(2) መሰረት ተመላክቷል፡፡ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በሰ/መ/ቁ59882 በሰጠዉ እና ቅፅ 12 ላይ በታተመዉ ዉሳኔ መሰረት ለዘገዬ ብድር ወለድ እንጅ መቀጮ አይከፈልም የሚል ዉሳኔ ተሰጥቷል፡፡
በቅርብ በሰበር ሰሚ ችሎቱ በሰ/መ/ቁ217051 በተሰጠ ዉሳኔ የፍ/ብ/ሕ/ቁ 2489(2) እና በቅፅ12 ላይ በሰፈረዉ በሰ/መ/ቁ 59882 የተሰጠዉ ዉሳኔ ተፈፃሚነት የሚኖረዉ በግለሰቦች መካከል የሚደረግ ብድር እንጅ በድርጅቶች መካከል የሚደረግን ብድር እንደማይመለከት፤ ብድሩ የተደረገዉ ከድርጅቶች ጋር ከሆነ ከወለድ በተጨማሪ መቀጮ ሊከፈል እንደሚገባ ትርጉም ሰጥቶበታል፡፡