Get Mystery Box with random crypto!

ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማከናወን ወንጀል ሰ/መ/ቁ 211028 ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማከናወን ወንጀል ሰ/መ/ቁ 211028
ያለ ደረሰኝ (ቫት) ግብይት ማከናወን ወንጀል ጋር በተያያዘ የድርጅት ሥራ አስኪያጅ የድርጅቱን አስተዳደር በሚመለከት በውክልና ለሌላ ሰው ያስተላለፈ መሆኑ እና ተወካዩም በተቀበለው ውክልና መሠረት ሥራውን የሚያከናውን መሆኑ በተረጋገጠ ጊዜ ተጠያቂ የሚሆነው ውክልናውን ተቀብሎ ስራውን በውክልና የሚያስተዳድረው ሰው እንጂ ስራ አስኪያጁ ወይም የድርጅቱ ባለቤት ሊሆን አይገባም።

አዋጅ ቁጥር 285/94 በአዋጅ ቁጥር 609/2001 እንደተሻሻለው በአንቀጽ 56/1/፤ አንቀጽ 22/1/ እና አንቀጽ 50/ለ/1 መሠረት የአንድ የንግድ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ በወንጀል ተጠያቂ የሚሆነው እሱ የሚመራው ድርጅት የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ሆኖ ያለተጨማሪ እሴት ታክስ ደረሰኝ ግብይት ማከናወኑ ሲረጋገጥ እንደሆነ፤ የድርጅቱ ሃላፊነት ከተረጋገጠ የሥራ አስኪያጁ ሃላፊነት የሕግ ግምት የሚወሰድበት ስለመሆኑ እንገነዘባለን።
4 ለ 1 አብለጫ ድምጽ የተሰጠ
የፌዴራል ታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁ 983/08 አንቀጽ 131(1)(ለ)፤ 131(1)(ለ)፤ 128
@habeshaadvocatesllp
t.me/ethiolawtips