Get Mystery Box with random crypto!

ሰመ.ቁ. 219736 ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም የ ሁከት ተግባር ምንነት የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149( | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

ሰመ.ቁ. 219736 ጥቅምት 04/2015 ዓ.ም የ ሁከት ተግባር ምንነት
የፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149(1) የሁከት ተግባርን የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮችን ከመጥቀስ ባለፈ በራሱ “ሁከት” ለሚለው ቃል የሰጠው ግልፅ ትርጉም የለም፡፡ ከዚህ ድንጋጌ ይዘት መገንዘብ እንደሚቻለውም የሁከት ተግባር የሚያቋቁሙ ፍሬ ነገሮች ተብለው የተጠቀሱት ሁለት ድርጊቶች ናቸው፡፡ አንደኛው ባለይዞታው በሀብቱ ሰላማዊ በሆነ መንገድ በመጠቀም መብቱ ላይ የሚደረግ ጣልቃ ገብነት አልያም የሚፈጠር እንቅፋት (Interferance) ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በባለይዞታው እጅ የነበረን ንብረት/ይዞታ/ በሙሉ ወይም በከፊል በመውሰድ ባለይዞታውን በዚያው መጠን ይዞታ አልባ ማድረግን (Dispossession) የሚመለከት ነው፡፡

በሌላ በኩል የሁከት ተግባሩ በሁለት መንገድ ሊፈፀም የሚችል ስለመሆኑ በዚሁ ዙሪያ ከተደረጉ ጥናቶች ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡ አንደኛው ይዞታውን ከባለይዞታው እጅ በመውሰድ ወይም በይዞታው ሰላማዊ በሆነ መንገድ የመጠቀም መብት ላይ በተጨባጭ/በተግባር/ የሚፈፀም ጣልቃ ገብነት /Disturbance in fact/ ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ በባለይዞታው የይዞታ መብት ላይ በህግ ረገድ የሚፈጠር ሁከት/Disturbance in law/ የሚል ነው፡፡ ሁለተኛው የሁከት ዓይነት አብዛኛውን ጊዜ የሚፈፀመው አስተዳደር ክፍል ይዞታውን በተመለከተ በራሱ ተነሳሽነትም ሆነ በሌላ ወገን ጠያቂነት በተለያየ መንገድ የባለይዞታውን የይዞታ መብት በሚነካ መልኩ በሚወሰደው አስተዳዳራዊ እርምጃ ነው፡፡ ይህ አስተዳደራዊ እርምጃ እንደየሁኔታው ባለይዞታው ይዞታውን በተመለከተ አንድን ድርጊት እንዲፈፅም ወይም እንዳይፈፅም በማድረግ አልያም የባለሃብትነት መብቱን የሚያሳጣ ተግባር በመፈፀም ሊሆን ይችላል፡፡

በእነዚህ ሁኔታዎች በይዞታው ላይ ሁከት የተፈጠረበት ባለይዞታ የተወሰደበት ነገር እንዲመለስለት ወይም የተነሳው ሁከት እንዲወገድለት እና በድርጊቱ ስለደረሰው ጉዳት ኪሳራ እንዲሰጠው በህጉ በተቀመጠው የጊዜ ገደብ ውስጥ መጠየቅ የሚችል ስለመሆኑ እና ዳኞችም ይኸው ስለመፈፀሙ ሲያረጋገጡ የተፈጠረው ሁከት እንዲወገድ እና ተገቢ ሆኖ ሲገኝም ካሳ እንዲከፈል ሊወስኑ እንደሚችሉ ከፍ/ብ/ህ/ቁጥር 1149 ድንጋጌ ጠቅላላ ይዘት መገንዘብ ይቻላል፡፡
@habeshaadvocatesllp
t.me/ethiolawtips