Get Mystery Box with random crypto!

አውራሽ/ሟች/ በህይወት እያለ ከይዞታ ቦታው ላይ ለሌላ ሠው ቤት እንዲሠራ ፈቅዶ ቢሰጠው ሟች በሚሞ | Lawyer_Henok Taye⚖️Ethio Law🥇ኢትዮ ሕግ

አውራሽ/ሟች/ በህይወት እያለ ከይዞታ ቦታው ላይ ለሌላ ሠው ቤት እንዲሠራ ፈቅዶ ቢሰጠው ሟች በሚሞትበት ጊዜ በሟች ፈቃድ ቤት የሠራው የቤቱ ባለቤት እንደሚሆንና ከሌላው ቦታ ጋር ሆኖ የውርስ ክፍል የሚሆን ስላለመሆኑ፣ የፍ/ህ/ቁ. 826/2/ እና 1179/1/። ሰ/መ/ቁ-96628 ቅፅ-17.
በመሆኑም ፈቅዶ የሰጠው ሟች የቦታውን መብት ለባለ ሀብቱ እያስተላለፈ /እያጠ/ ስለሆነ በፍ/ብ/ህ/ቁ/826/2/ መሰረት አውራሻቸው የሌለው መብት ለወራሾች ሊተላለፍ የሚችልበት የሕግ መሠረት የለም፡፡በፍትሐብሔር ሕግ ቁጥር 1179(1) መሠረት ባለመብት የሚሆነው አውራሽ ሳይቃወመው በራሱ ወጭ በሠራቸው ቤቶችና ቤቶቹ በተሰሩበት ወይም ባረፉበት ቦታ ላይ ብቻ ይሆናል ።ይህ ቦታም የውርስ ሀብት ክፍል በሆኑ ንብረቶቹ ውስጥ ሊካተት አይችልም ።
t.me/ethiolawtips
Share #Join