Get Mystery Box with random crypto!

Assaye Derbie

የቴሌግራም ቻናል አርማ etegieassaye — Assaye Derbie A
የቴሌግራም ቻናል አርማ etegieassaye — Assaye Derbie
የሰርጥ አድራሻ: @etegieassaye
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.38K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2023-05-17 15:49:10 በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያሉንን መረጃዎች ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ ትከታተሉን ዘንድ ጋበዝን።

https://www.youtube.com/live/I2GRL8uuh6I?feature=share
6.2K viewsAssaye Derbie, 12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 20:10:59
ብልጽግና ሆይ፦ አፍነህ የወሰድከው ዜጋ የሚገኝበትን አድራሻ መናገር የደበረህ ብር ፈልገህ ከሆነ ፥ እንደ ሸኔ የምትፈልገውን የገንዘብ መጠን ንገረንና መዋጮ አሰባስበን እናምጣልህ።
7.2K viewsAssaye Derbie, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 19:52:25 አምባሳደር/ኡስታዝ ሐሰን ታጁ ማለፊያ ምክር
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆

የጥንት ሰዎች ትልልቅ የህይወት መርሆችን በእንስሳት፣በእጽዋት፣በግኡዛን አንደበት መናገር ያዉቁበታል፡፡ በዐረቦች ዘንድ በስፋት ሲነገር የኖረ አንድ አፈታሪክ አለ፡፡ አራተኛዉ ኸሊፋ ዐሊ እብን አቢጣሊብ በዘመናቸዉ የገጠማቸዉን ፈተና ለማሳየት ተጠቅመዉበታል፡፡

አፈታሪኩ እንደሚለዉ ሶስት በሬዎች በጫካ ዉስጥ አብረዉ ይኖሩ ነበር፡፡ የአንደኛዉ በሬ ቀለም ነጭ፣የሌላኛዉ ቀይና የሶስተኛዉ ጥቁር ናቸዉ፡፡ በአካባቢያቸዉ አንበሳ ቢኖርም ሶስቱ ተባብረዉ ራሳቸዉን ስለሚከላከሉ ሊያጠቃቸዉ አልቻለም፡፡ ነጣጥሎ የሚያጠቃበትን ብልሀት ዘየደ፡፡ እናም ቀዩንና ጥቁሩን ለብቻ አግኝቶ፡- ‹‹ነጩ ባልንጀራችሁ ቀለሙ ዓይን ሳቢ በመሆኑ ከሩቅ አደጋ ይጋብዛል፤ እናም እንድበላዉ ፍቀዱልኝ›› ሲል ጠየቃቸዉ፤ ጥቂት ካመነቱ በኋላ ‹እዉነቱን ነዉ፤ደግሞም እርሱ አለመኖሩ ጫካዉን ሁለታችን ብቻ እንድንጠቀምበት ስለሚያደርገን ጥሩ ነዉ›› በማለት እንዲያጠቃዉ ፈቀዱለት፡፡ ነጩ በሬ ባልንጀሮቹን ከጥቃት እንዲከላከሉለት ቢማጸናቸዉም አይተዉ እንዳላዩ፣ሰምተዉ እንዳልሰሙ በመሆን ችላ አሉት፡፡ አንበሳዉ ቅርጥፍ አድርጎ በላዉ፡፡ ጥቂት ሰነባብቶ ረሀብ ሲሰማዉ ተመልሶ መጣ፡፡ ሁለቱ በሬዎች በጋራ ከቆሙ እንደማይቻሉት ያዉቃልና ጥቁሩን በሬ ለብቻዉ አግኝቶ፡-‹‹ይህን ሰፊ ጫካ ያለተጋሪ ለብቻህ የምትጠቀምበትን ግሩም ሀሳብ አስቢያለሁ›› በማለት አግባባዉ፤ ጥቁሩ በሬ ይህን ‹‹ግሩም›› ሀሳብ አመነበትና በባልንጀራዉ ላይ ሞት ፈረደ፡፡ ቀዩ በሬ ተጠቃ፡፡ ባልንጀራዉ እንዲያግዘዉ ቢማጸንም የሚደርስለት አልሆነም፡፡ አያ አንበሶ ቅርጥፍ አደረገዉ፡፡ ጥቂት ሰነባብቶም ጥቁሩን በሬ፡- ‹‹አሁን ያንተ ተራ ነዉ›› ሲለዉ ‹‹እኔን የበላሀኝ ነጩን ባልንጀራዬን የበላሀዉ ቀን ነዉ›› ሲል በቁጭት መለሰለት፡፡ አያ አንበሶ ባባባሉ ተገርሞ፦‹‹ለምን ቀዩን በሬ ዘለልከዉ፤ብቻህን የቀረኸዉ እኮ እርሱን የበላሁት ቀን ነዉ›› ሲለዉ፡- ‹‹የለም፤አብሮ በአንድነት የሚያቆየንን አቋም የሸረሸርኩት ነጩን በሬ አሳልፌ ለመስጠት የተስማማሁ ቀን ነዉ›› በማለት መለሰለት ይባላል፡፡

በሀገራችን በየዕለቱ የሚሰማዉን አሰቃቂ ሁኔታ ይህ አፈታሪክ መስታወት ሆኖ ያሳየናል፡፡ በጋራ የሚያቆመን፣የሚያኖረን፣የሚከላከልልን ማህበራዊ ዕሴት አንድ ጊዜ እንዲጣስ ስለፈቀድን እያደር መሸርሸሩና ለሁላችንም አደጋ ማስከተሉ አልቀረም፡፡ ይህን በቲየሪ ሳይሆን በተግባር እያየነዉና እየኖርነዉ እንገኛለን፡፡ በረዥሙ ታሪካችን ታይቶ በማይታወቅ መጠንና ሁኔታ ሺዎች ንጹሀን ዜጎች በግፍ ሲገደሉና ሲፈናቀሉ፣ ንብረታቸዉ ሲዘረፍና ሲቃጠል፣ የሀይማኖት አባቶች ሲሳደዱ፣የማምለኪያ ቦታዎች በእሳት ሲጋዩና ሲፈርሱ ጉዳዩ ‹‹የነገሌ ወገን›› ብቻ ተደርጎ በቸልታ የታየ ጊዜ፣ ሲብስም ባልተገባ ስጋዊ ስሌት ከግፈኞች ጎን የመቆም አዝማሚያ የተስተዋለ ጊዜ ነዉ ዉሉ የተሳተዉ፡፡ አሁን ነገሮች ፈር ለቀዉ በሩቅ አካባቢዎች ሲፈጸሙ እንደትንግርት ስንሰማቸዉ የነበሩ ሰቆቃዎች ባልታሰበ ፍጥነት ወደመሀል አገር ደርሰዋል፡፡ በየዘመናቱ እንደተፈጸሙ በታሪክ መዛግብት ያነበብናቸዉ ግፎች ሁሉ አሁን በአንድ ዘመን በብዙ እጥፍ ተባዝተዉ እየተፈጸሙ እንደሆነ እየታዘብን ነው፡፡

እናማ ነገሮች ከዚህ በላይ ተበለሻሽተዉ፡- ‹‹የተበላሁት ነጩ በሬ የተበላ ቀን ነዉ›› የሚለዉን ያያበሬ ብሂል ከመድገማችን በፊት የ"ሰውነት ይቀድማል" መርህን አጠንክረን ይዘን፣ የብሄርና የሀይማኖት ስሌቶችን ወደጎን በመተዉ ሁላችንም በአንድ ልብ ከፍትህና ከሰብአዊነት ጎን መቆም ይገባናል፡፡

አላህ ከተገፊዎች ጋር ይሁን፡፡
7.1K viewsAssaye Derbie, 16:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-16 16:03:42 "ያሳፍራል "

ትንግርቱ ገ/ጻዲቅ (ረ/ፕ)

የምናወራው መንግስታዊ ሽብር ስለታወጀበት፣ ጦርነት ስለከፋበት ና የመኖር ህልውናው አደጋ ስለገጠመው አንድ ታላቅ ሕዝብ ነው።

በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን በማንነታቸው ምክንያት ብቻ ታፍነው በጨለማ በእስር ቤት ይማቅቃሉ፣ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ ተፈናቅሎብናል፣ በራሳችን ሀገረ-መንግስት ጦርነት ታውጆብን ህዝባችን በየለቱ እየታደነ ይኖራል።

ሲነጋም ሆነ ሲመሽ ይህን ህዝብ ከዚህ ሁሉ ጥፋት የመታደግ ሀላፊነት በኛ በትውልዱ ጫንቃ ላይ እንደተጣለም አምናለሁ።

ይሁ ሁሉ ቢሆንም...

በዚህ ሁሉ ምስቅልቅል ውስጥ ያለ ህዝብ እንዴት ስለ ብጣሽ ዞንና አንዲት ወረዳ መመስረት እየተብሰለሰለ እንዲያወራ ማድረግ እንደተቻለ ግን በፍጹም ሊገባኝ አልቻለም።

ያሳፍራል!

ድል ለአማራ !!

#AmharaStruggle
#Justice4Amhara
#AmharaGenocide
7.5K viewsAssaye Derbie, 13:03
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:47:50
አዲሱ የትሕኦነግ የሥራ ቋንቋ ይሄንን ይመስላል።
በአንድ ዘገባ ላይ በዚህ ልክ ለመሳሳት ትልቅ ደደብ መሆን ይጠይቃል።
8.3K viewsAssaye Derbie, 14:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 15:51:55 ከስር ያለውን ሊንክ በመጠቀም በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያሉንን መረጃዎችና ትንታኔዎች ትከታተሉ ዘንድ ጋበዝን።

https://www.youtube.com/live/TU-swAe49DE?feature=share
8.1K viewsAssaye Derbie, 12:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 09:25:30
''ለቤታችሁ ማፍረሻ 10ሺ ብር ካልከፈላቹህ የቤት እቃችሁ ለመንግስት ገቢ ይሆናል በሚል የድሀ ንብረት ጭነው እየወሰዱ ነው!''

@መሳይ መኮንን
8.2K viewsAssaye Derbie, 06:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-14 20:58:48
ወንድማችን ኤርሚያስ መኩሪያ "ሕግ አስከባሪዎች" የሚል ሥም በተሰጣቸው ሕገወጦች ታፍኖ ከተሰወረ ሦስት ቀናት አለፈው። ቤተሰቦቹም ኤርሚ የታሠረበትን ጣቢያ ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ገዥው ፓርቲ አረመኔያዊ ድርጊት ከሚፈጽምባቸው ጨለማ ቤቶች ውጭ ባሉ ፖሊስ ጣቢያዎች ውስጥ ፈልገው ሊያገኙት አልቻሉም።
8.4K viewsAssaye Derbie, 17:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 15:45:06 ከስር ባለው ሊንክ ገብታችሁ Live ትከታተሉን ዘንድ ጋበዝን!

https://www.youtube.com/live/HO0aAPMAJs8?feature=share
3.7K viewsAssaye Derbie, 12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 09:41:24
5.3K viewsAssaye Derbie, 06:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ