Get Mystery Box with random crypto!

Assaye Derbie

የቴሌግራም ቻናል አርማ etegieassaye — Assaye Derbie A
የቴሌግራም ቻናል አርማ etegieassaye — Assaye Derbie
የሰርጥ አድራሻ: @etegieassaye
ምድቦች: ፖለቲካ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 20.38K

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-13 00:40:49 ከስምንት ወር በፊት ይሄንን ትንቢት መጻፌን የምታስታውሱ ስንቶቻችሁ ናችሁ?

ማርክ ማይ ወርድ!
አሳዬ ደርቤ
የአራት ኪሎው መንግሥት ወደ ፈላጭ ቆራጭነት ለመሸጋገርና በወልቃይት መሬት ላይ ለመደራደር ሲያስብ አብን እና ብአዴን የእቅዱ ተገዢ ሆነው ደስ አሰኙት፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ በሶሻል ሚዲያው መድረክ ሕዝባቸውን የሚያነቁ ጦማሪዎችና በጦር ሜዳ ላይ የሚዋደቁ ወጣቶች እንቅፋት ሆነው ታዩት፡፡
እርሱም አለ…
‹‹በወልቃይት ማንነት ዙሪያ ለመደራደርም ሆነ አማራን ለማስገበር የጌታቸው ረዳን ሐሳብ መተግበር ግድ ይላል፡፡ ይሄውም የአማራን ልሳኖችን እና ክንዶች የመስበር ዘመቻ 'ሕግ ማስከበር' ይባል፤››
ከዚህም ውሳኔ በኋላ ከላይ የተዘረዘሩትን ኃይሎች ጠርቶ ወረቀትና ገንዘብ ካቀበላቸው በኋላ "ሕግ አስከብሩ›› አላቸው።

እነርሱም ቦርጫቸውን እንደ ጠረጴዛ በመጠቀም የተሰጣቸውን ወረቀት ካስደገፉበት በኋላ ‹‹ጽንፈኛ›› በሚል ርዕስ ‹‹እንቢተኛ እና ሐቀኛ›› የአማራ ልጆችን ሥም መጻፍ ጀመሩ፡፡ እናም አሁን ላይ ፦
➔አንዳንድ የአብን አመራሮች በብአዴን የሚታፈኑ የአማራ ልጆችን እየጠቆሙ ነው፡፡
➔አንዳንድ ተከፋይ የአማራ ወመኔዎች ‹‹ወገኔ›› የሚሉትን ሕዝብ ለአፈና ዳርገው ‹‹ወያኔ›› የሚሉትን ጠላት እየጠበቁ ነው፡፡
➔አብዛኛው የአማራ ሙሕራን እና ፖለቲከኞች ‹‹ተደራጅ›› ብለው ሲቀሰቅሱት የኖሩት ፋኖ ሲሳደድ እያዩ ‹‹ሕግ እንዲከበር እንፈልጋለን፡፡ በወልቃይት ላይ ለመደራደር ያሰባችሁ ቀን ግን እንጣላለን›› እያሉ ነው፡፡

ይሄውም የመጀመሪያ ምዕራፍ ‹‹የሕግ ማስከበር›› ዘመቻ በስኬት መጠናቀቅ ከቻለ ሁለተኛው ምዕራፍ ‹‹ሰላም አስከባሪ›› የሚል ይሆናል፡፡ እናም ‹‹በአንዳንድ አካባቢዎች የሚነሱ የማንነት ጥያቄዎች መልስ እስኪያገኙ ድረስ በፌደራል መንግሥትና በኮማንድ ፖስት ሊተዳደሩ ይገባል›› መባል ይጀመራል፡፡

ያን ጊዜም ከላይ የተጠቀሱት ተላላኪ ኃይሎች ስምምነታቸውን ገልጸው ከወጡ በኋላ ለይምሰል ያህል ከሕዝብ ጎን ቆመው ቁጣቸውንና ተቃውሟቸውን እንዲገልጹ ይፈቀድላቸዋል፡፡
የሕዝብ ጠበቃና ጠባቂ የሆኑ ወጣቶች ወንጀለኛ እና ጽንፈኛ ተብለው እየተመረጡ ሲታፈኑ በዝምታው አማካኝነት ለዘብተኛ መሆኑን ሲገልጽ የከረመው የአማራ ሙሕርም በብልጽግና ውሳኔ የመናደድ መብቱ ይከበርለታል።

ከወልቃይት ምድርም ‹‹ማንነቴን የምትወስን አንተ ማን ነህ›› የሚል ትግል ይቀጣጠላል፡፡ ‹‹የወገን ያለህ›› የሚል ቃልም ይሰማል፡፡ ሆኖም ግን ያ ጊዜ እንደሚመጣ አውቀው በሸዋ፣ በወሎ፣ በጎጃምና በጎንደር ሲደራጁ የከረሙ ፋኖዎች ለአፋና እና ለብተና የተዳረጉ በመሆናቸው ፈጥኖ የሚደርስ ኃይል አይኖርም፡፡

ከዚያ በማስከተል በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የታፈኑ ሁሉ ያለምንም ፍርድ በነጻ ይለቀቃሉ፡፡ ከእነዚህ መሃከል አብዛኞቹ ትግላቸውን ሲቀጥሉ አንዳንዶቹም ዝምታን ተምረው ይወጣሉ፡፡

አሳሪዎቹ ደግሞ የሚታሠሩበት ቀን እስኪመጣ ድረስ የእነሱ ሕልውና በብልጽግና እድሜ ላይ የተመሠረተ መሆኑን ተረድተው የህውሓትና የመንግሥት ጋብቻ ሲፈጸም እልልታቸውን ያቀልጣሉ። ‹‹የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም›› በሚል አቋምም ዛሬ ላይ የንቁ ዜጎች ማሸማቀቂያ ካደረጉት ጠላት ጎን ተሰልፈው ሕዝባቸው ላይ ይዘምታሉ፡፡

ይህ ቀን እንዳይመጣ የሚሹ ወገኖች ግን አሁን ላይ እንቅልፍ በተጫጫነው ክልል ውስጥ ቆመው ቀን እና ሌሊት በመታገል ላይ ይገኛሉ። "አፈናው ይቁም" ይላሉ።
4.0K viewsAssaye Derbie, 21:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 19:42:44 "ነፍጠኛ" እየተባሉ በጥፊ ሲጠፈጠፉና ከንጹሐን ጋር ሲጨፈጨፉ የከረሙ የሃይማኖት አባቶች "የአማራ ልዩ ሃይል ቢጠፋም እኛ አባቶቻችሁ እያለን ማንም አይነካችሁ" በሚል ምልጃ ሕዝብን የማስተኛት ሥራ እየሠሩ ነው።

እናም ለእኒህ አባቶች የምንሰጠው መልስ..."ከእኛ በፊት ሲጨፈጭፉን የከረሙ አሸባሪዎችን ትጥቅ አስፈትታችሁ ከሥጋትና ከጥቃት ገላግሉን" የሚል መሆን አለበት።
8.1K viewsAssaye Derbie, 16:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 12:31:58 የመስከረም አበራ የስልክ ንግግር የሚባለውና በINSA በኩል ተለቀቀ የሚባለው የድምጽ ቅጂ የእርሷ ቢሆን እንኳን በሚዲያ ከምታወራው የተለየ ነገር የያዘ አይደለም። በዚያ ላይ ደግሞ ድምጽ ማቀናበር ከባድ አይደለም።

በተረፈ መንግሥት ተብዬው አካል የግለሰቦችን ስልክ ከመጥለፍ ባለፈ በየሪዞርቱና በየሆቴሉ የስለላ ካሜራ አስገጥሞ የዜጎችን ብቻ ሳይሆን የእራሱን ባለሥልጣናትም ጭምር ገመና እየሰበሰበ ብላክ ሜይል እንደሚያደርግ የታወቀ ነገር ነው።

ውርጋጥ መራሹ ሥርዓት ከትላልቅ ሆቴሎች መኝታ ቤት ሳይቀር ካሜራ አስገጥሞ የወሲብ ትዕይንት ሲከታተል የሚያድር አሳፋሪ ስብስብ መሆኑን ካወቅን ቆየን። (ለዚያም ነው "ያገራችን ጉዳይ ያገባናል" በሚል ንግግራቸው የሚታወቁ ፖለቲከኞች ሁሉ አንገት ደፍተው የቀሩት
2.1K viewsAssaye Derbie, 09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:59:51
ጧሒር መሐመድ....
ከሌሎች የአብን አመራሮች በተሻለ መልኩ ከሕዝብ ጎን ተሰልፎ የተገኘ!!
3.7K viewsAssaye Derbie, 07:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:34:28
4.0K viewsAssaye Derbie, 07:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 10:20:19
"ፌደራሊስት" ብሎ እራሱን ለሚጠራው ጨፍላቂ መንጋ

"አቶ ልደቱ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ ከእኛ የተለየች አንዲት ሐሳብ አነሳብን" ብለው በጸረ ሕዝብነት የፈረጁትና የሞት ፍርድ የፈረዱበት 'ፌደራሊስት' ተብዬዎች "ኤርሚያስ ከኢትዮ 360 የለቀቀው ለየት ያለ ሐሳብ ማስተናገድ ባለመቻላችሁ ነው" እያሉን ነው።

እኔ ግን እላለሁኝ...

ኤርሚያስ ይሄን ያህል ጊዜ መቆየት የቻለው በወልቃይትና ራያ ማንነት ዙሪያም ሆነ በሄዊ ዙሪያ የሚያራምደውን ሐሳብ ማስተናገድ በመቻላችን ነው።.

በተረፈ ኤርሚ በኡቡንቱም ሆነ በርዕዮት ሚዲያ በተቀጠረ ቅጽበት ስለ አዲስ አበባ ያለውን አቋም ካልቀየረ በማግስቱ "ሐጣ*ራው" ብላችሁ እንደምታፈናቅሉት ጥርጥር የለውም።
4.1K viewsAssaye Derbie, 07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 08:41:39
የኤርሚን ሥም ቀርቶ የሌላውንም ቢሆን ያለምክንያት የማንሳት ፍላጎት የለንም። እናም ባለፈው እንደተነበይነው ኤርሚ ከኢትዮ 360 ለቅቋል። በቀጣይ በሌላ ሚዲያ እንደሚመጣና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ¿ ክቡር ዘበኛ ሆኖ የኖረበት ካምፕ ላይ ሲዘምት እንደሚታይ አልጠራጠርም።

ምክንያቱም....
የኤርሚን ሥነልቦና ጠንቅቄ ከተረዳሁ በጣም ቆየሁኝ። በተረፈ ...
የብልጽግና እና የሄዊ ጋብቻ ከተፈጸመበት ጊዜ አንስቶ ኤርሚያስና ሽመልስ በተመሳሳይ ማሊያ መሮጥ ጀምረዋል።

መልካም ጊዜ ይሁንልህ!!
4.8K viewsAssaye Derbie, 05:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 19:33:45 "እንዴ ግስላ የተቆጣውን ሕዝብ አዘናግታችሁ ያሰብኩትን ዘመቻ የማታሳኩ ከሆነ ከወንበር አንስቼ ወደ መቃብር እንደማወርዳችሁ እወቁ" የሚል ዛቻ ካስተናገዱ የብአዴን አመራሮች "ሕዝቤ ሆይ በሶሻል ሚዲያ የሚወራውን አትስማ" ከማለት ባለፈ "ሕዝቤ ሆይ ጥያቄህን ሰምተናል" የሚል መልስ አይጠበቅም።
አሳዬ ደርቤ
6.7K viewsAssaye Derbie, 16:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:49:03
የባሕር ዳር ቁጣ እየበረታ መጥቷል። በኮምቦልቻ ከተማም እንቢተኝነቱ በርትቷል።
4.1K viewsAssaye Derbie, 09:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:37:25
ጄኔራል መስከረም አበራ "ወታደራዊ ሥልጠና ስትሰጥ ነበር" "የሚል ክስ ተመስርቶባታል።
4.4K viewsAssaye Derbie, 09:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ