Get Mystery Box with random crypto!

Esat tv

የቴሌግራም ቻናል አርማ esat_television_official — Esat tv E
የቴሌግራም ቻናል አርማ esat_television_official — Esat tv
የሰርጥ አድራሻ: @esat_television_official
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 59
የሰርጥ መግለጫ

ኢሳት የኢትዮጵያ #አይን እና #ጆሮ
መሳይ መኮንን ✍️

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2022-05-21 21:52:06
#WFP #Ethiopia

የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።

ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ (በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ) ፥ " ፍጥነቱ አሁን እየጨመረ ስለሆነ በዚህ ወር መጨረሻ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 30 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና የምግብ ሸቀጦች ወደ ትግራይ ይደርሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። እቅዳችን በሰኔ ወር መጨረሻ 100 ሺህ ቶን ምግብ ለማድረስ ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የረድኤት ድርጅቶች አፋርን ጨምሮ በአጎራባችን ክልሎች ቀውሶች እየተባባሱ በመሆናቸው እጅ እያጠራቸው ፤ የእርዳታ ክምችታቸውም እየተመናመነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዩክሬን ጦርነት እና ሌሎችም በዓለም ዙሪያ የታዩት ቀውሶች የለጋሾችን የረድዔት አቅም እየቀነሰው መሆኑ የታገለፀ ሲሆን WFP በሚቀጥለው 6 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚያስፈልገው የእርዳታ አቅርቦት የ522 ሚሊዮን ዶላር እጥረት እንደሚያጋጥመው ገልጿል።

ከዚህ ውስጥ 220 ሚሊዮን ዶላር ትግራይን ጨምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ለሚሰራው የረድኤት ስራ የሚውል ነው።

ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ ፤ " ያለን ክምችት በጣም በፍጥነት እያለቀ ነው። ስለዚህ ስጋታችን ይህን አውንታዊ ድባብ ፈጥረን እነኚህን መተላለፊያዎች ከፍተን መልሰን ማቆም ሊኖርብን ነው እናም ሁሉ ነገር ከሚያዚያ በፊት ወደነበረው ስፍራ ሊመለስ ነው " ብለዋል።
3.3K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 18:40:29
በ12 አገራት ወደ 80 የሚጠጉ ሰዎች በዝንጀሮ ፈንጣጣ (ሞንኪፖክስ) መያዛቸው መረጋገጡን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ

የአገራቱን ስም ሳይገልጽ ሌሎች 50 ተጠርጣሪዎችም በምርመራ ላይ መሆናቸውንም የዓለም ጤና ድርጅት ገልጿል።መጀመሪያ በአውሮፓ መታየቱን ተከትሎ ቀደም ሲል በጣሊያን፣ በስዊድን፣ በስፔን፣ በፖርቱጋል፣ በአሜሪካ፣ በካናዳ እና በዩናይትድ ኪንግደም በሽታው መኖሩ ተረጋግጧል።
የዝንጀሮ ፈንጣጣ በብዛት በመካከለኛው እና በምዕራብ አፍሪካ አካባቢዎች በብዛት የሚከሰት ነው።

የእንግሊዝ ብሔራዊ የጤና አገልግሎት እንደገለጸው፣ ይህ ያልተለመደ የቫይረስ ኢንፌክሽን አብዛኛውን ጊዜ ቀላል ሲሆን ብዙዎች ላይም በጥቂት ሳምንታት ውስጥ የሚድን ነው።ቫይረሱ በሰዎች መካከል በቀላሉ የማይሰራጭ ሲሆን በሰፊው ሕዝብ ጤና ላይ የሚያስከትለው ስጋት በጣም ዝቅተኛ ነው ተብሏል።

ለዝንጀሮ ፈንጣጣ በሽታ የተለየ ክትባት የለም። ከመደበኛው ፈንጣጣ ጋር ተመሳሳይ በመሆናቸው የፈንጣጣ ክትባት 85 በመቶ የመከላከል አቅም ይሰጣል።የዓለም ጤና ድርጅት አርብ ዕለት በሰጠው መግለጫ "በቅርብ ጊዜ በ11 አገሮች የተመዘገበው ወረርሽኞች ተላላፊ ባልሆኑ አገሮች ውስጥ መከሰቱ ያተለመደ ነው" ብሏል።

"ተጎጂዎችን ለማግኘት፣ ለመደገፍና የበሽታ ክትትልን ለማስፋፋት ከተጎዱት አገራት እና ከሌሎች ጋር እየሠራሁ ነው" ብሏል።በተጨማሪም ድርጅቱ በበሽታው ምክንያት ማግለል እንዳይኖር አስጠንቅቋል።
6.0K views15:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-21 12:05:17
የመዲናዋ ህንፃዎች ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ተባለ

የአዲስ አበባ ህንፃዎች ሁሉ ግራጫ ቀለም ሊቀቡ ነው በሚል ከሰሞኑ በማህበራዊ ትስስር ገጾች የሚናፈሰው መረጃ ከዕውነት የራቀ ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኮሙኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ዮናስ ዘውዴ አስታወቁ።

የቢሮ ኃላፊው በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደገለጹት፤ አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብና ለነዋሪዎቿ ምቹ ለማድረግ የህንፃ ስታንዳርድና የውጭ ማስታወቂያ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ ነው፡፡ ሆኖም ግን ይህን መነሻ አድርጎ በማህበራዊ ትስስር ገጾች አዲስ ከተማ ግራጫ ቀለም ልትቀባ ነው በሚል በስፋት ሲዘዋወር የታየው መረጃ የተሳሳተ ነው ብለዋል፡፡

እስካሁን ድረስ የከተማዋ ህንጻዎች ቀለም ምን አይነት ይሁን የሚለው ጉዳይ ለውይይት ቀረበ እንጂ የከተማ አስተዳደሩ በጉዳዩ ላይ ምንም አይነት ውሳኔ እንዳላሳለፈ አመልክተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይም ከዚህ ቀደም ‹‹ከተማችን ቡራቡሬ ሆና ባለቤት አልባ መስላለች›› ማለታቸውን ያስታወሱት የቢሮ ኃላፊው፤ ይህን ችግር ማንኛውም የመዲናዋ ነዋሪም ሊታዘብ ይችላል። የከተማ አስተዳደሩም ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቷል ብለዋል።

ችግሩን ለመፍታት የውጭ ማስታወቂያውና የከተ ማዋ ቀለም ሁኔታ የሚመራበት ስታንዳርድ ዝግጅት ተደረገ እንጂ ውሳኔ ላይ አለመድረሱን ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
8.3K views09:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 17:31:26 ልዩ እና ሰበር ዜናዎች ብቃት ባላቸው ጋዜጠኞች ኢንተለጀንሶች ተከፍቶ መረጃዎችን እያነፈነፈ ለህዝብ የሚያቀርብ ሀገራዊ የቴሌግራም ቻናል እንጠቁሞ

https://t.me/+PY4FFQ1WAEVmN2Mx
ሊንኩን ተጭነው አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
6.2K views14:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-20 17:29:14
በ2015 ዓ.ም የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲ መጨናነቅ ምክኒያት ባሉበት የትምህርት ደረጃ እንዲቀጥሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናገሩ!

ሙሉ መረጃ ይመልከቱ
6.4K views14:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 16:40:25
በአባቷ የቀብር ስነስርዓት ላይ ለጓደኛዉ የታገቢኛለሽ ወይ? ጥያቄ ያቀረበዉ ግለሰብ አነጋጋሪ ሆኗል !!

የጉድ ሀገር እንዲሉ በአባቷ ቀብር ላይ ለጓደኛዉ ቀለበት ያሰረዉ ደቡብአፍሪካዊ ከሀገሩ እንዲሁም ከሌሎች የዓለማችን ክፍል ነዋሪዎች ዘንድ ከባድ ትችትን እያስተናገደ ይገኛል፡፡

በአባቷ የቀብር ስነስርዓት ላይ ተንበርክኮ ታገቢኛለሽ ብሎ ሲጠይቃት የሚያሳየዉን አስደንጋጭ ቪድዮ የቀብር ስነስርዓቱ ላይ የተገኘች አንዲት ሴት ቀርጻ ወዲያዉ በቲክቶክ የማህበራዊ መገናኛ ላይ ከለቀቀች በኋላ፤ እጅግ በርካታ ሰዎች እንደተቀባበሉት እና ብዙ ተጠቃሚዎችም ትችቶችን እንደሰነዘሩበት ኦዲቲ ሴንትራል ነዉ የዘገበዉ፡፡

ቪድዮዉ ላይ የሚታየዉ የአባቷ አስከሬን ሳጥን ፊት ቁጭ ብላ በማልቀስ ላይ የምትገኘዉ ጓደኛዉን ተንበርክኮ የታገቢኛለሽ ጥያቄ ሲያቀርብ ነዉ። ማይክራፎን በመጠቀምም ንግግር ያደርግ እና የሌሎች ሹክሹክታ እና ተቃዉሞ አንዳች ሳያግደዉ ቀለበት አዉጥቶ በጣቷ ላይ ሲያጠልቅ ያሳያል፡፡

ጓደኛዉ በፍጹም ድንጋጤ ዉስጥ ሆና የምትታይ ሲሆን ምንም ዓይነት ምላሽ ባለመስጠቷም የጋብቻ ጥያቄዉን ትቀበል አትቀበል ምንም ግልጽ የሆነ ነገር የለም፡፡ በቦታዉ እየሆነ ያለዉን ነገር በስርዓቱ ለማጣጣም በትክክለኛዉ የስሜት ሁኔታ ላይ እንዳልነበረችም በግልጽ ይታይ ነበር፡፡

Via oddity central

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
6.6K views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-16 13:58:52
መርጌታ ያብስራ የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደር
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል

https://t.me/+1AYabX41TA83OTY0
ለጥያቄወ 0924245307 ይደውሉልን
7.2K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 21:18:22 ልዩ እና ሰበር ዜናዎች ብቃት ባላቸው ጋዜጠኞች ኢንተለጀንሶች ተከፍቶ መረጃዎችን እያነፈነፈ ለህዝብ የሚያቀርብ ሀገራዊ የቴሌግራም ቻናል እንጠቁሞ

https://t.me/+PY4FFQ1WAEVmN2Mx
ሊንኩን ተጭነው አሁኑኑ ይቀላቀሉ!
2.6K views18:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 17:39:17 የኢ.ኤም.ኤስ የእለተ እሁድ አጫጭር መረጃዎች

1. በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር የኢትዮጵያ ሰብዓው መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳሰቧል።
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን “በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ኃይሎች መካከል” ዳግም እየተካረረ የመጣው የጦርነት ስጋት እንዳሳሰበው ባወጣው መግለጫ ገልጿል። ተቋሙ በመግለጫው እንዳስታወቀው በኢትዮጵያ ዳግም ጦርነት እንዳይጀመር ሁሉም የበኩሉን እንዲወጣ አሳስቧል።
ከ19 ወራት በፊት በሰሜን ኢትዮጵያ በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት በርካቶች ለተለያዩ አስከፊ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እንደተጋለጡ ያወሳው ኢሰመኮ አሁንም ዳግም ወደ ጦርነት ለመግባት እያደገ የመጣው መካረር ሊቆም እንደሚገባ ገልጿል።

2. ሕንድ በግዛቷ የሚመረት ስንዴ ወደ ውጭ ሀገራት እንዳይወጣ እገዳ መጣሏን የሀገሪቱ ዜና ወኪል ዘግቧል።ሆኖም አዲሱ የስንዴ የውጭ ሀገራት እግድ ከዚህ በፊት በሂደት ላይ የነበሩ የስንዴ ግብይቶችን እንደማይመለከት አስታውቃለች። የአውሮፓ ሀገራት በበኩላቸው የሕንድን ውሳኔ የኮነኑ ሲሆን ውሳኔው በዓለም የስንዴ ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረዋል ሲሉ አክለዋል። ሕንድ በስንዴ ሽያጭ ላይ እገዳ መጣሏ በተለይም በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ምክንያት የስንዴ አቅርቦት የተቋረጠባቸው የአፍሪካ እና እስያ ሀገራት ሕንድን እንደ አማራጭ ለመጠቀም አስበው ነበር። በሕንድ አንድ ቶን ስንዴ በ25 ሺህ ሩፒ ወይም በ320 ዶላር የሚሸጥ ሲሆን፤ ወደ ውጪ ሀገራት አዲስ የሚደረጉ የስንዴ ግብይቶችን በሀገር ውስጥ የምግብ እጥረት እንዳይከሰት በሚል የስንዴ ምርት ከሀገር እንዳይወጣ እገዳ ጥላለች።

3. የፊንላንድ መንግስት አሜሪካ መራሹን የኔቶ ጥምር ጦር መቀላቀል እንደሚፈልግ በይፋ አስታውቋል። የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳውሊ ኒኒስቶ ከካቢኔያቸው ጋር ባደረጉት ስብሰባ ላይ ፊንላንድ የኔቶ አባል ለመሆን በምታቀርበው የአባልነት ጥያቄ ላይ ስምምነት ላይ ተደርሷል ብለዋል። ይህ የካቤኒው ስምምነት ለመጽደቅ የፓርላማ ይሁንታ ማግኘት ይኖርበታል ተብሏል።

4. ጎረቤት ሀገር ሶማሊያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ስታካሂድ ውላለች፡፡ ከማለዳ ጀምሮ የድምፅ አሰጣጥ ሂደቱ እየተካሄደ ይገኛል። ይህ የዛሬው ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ ለ6ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ረጅም ጊዜ ሲጠበቅ ነበር። ቀጥተኛ ባልሆነው በዚህ ምርጫ ላይ 30 በላይ እጩዎች እየተወዳደሩ ይገኛሉ።

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
7.2K viewsedited  14:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-15 12:39:02 እስካሁን ያልጠሩ ዩኒቨርስቲዎች ችግራቸው ምንድነው ?

1, ዲላ ዩንቨርስቲ (በቅርቡ ይጠራል )

2, ወሎ ዩኒቨርስቲ ( በጦርነቱ ምክንያት መጥራት አልቻለም፣ ሁሉ ነገር አልተስተካከለም ተመራቂ ተማሪዎችን ገና አላስመረቀም)

3, ወልዲያ ዩኒቨርስቲ ( በጦርነቱ ምክንያት መጥራት አልቻለም፣ ሁሉ ነገር አልተስተካከለም )

4, ደባርቅ ዩኒቨርስቲ (አከባቢ ላይ ያለው የፀጥታ ሁኔታ) & በቅርቡ

5, ደምቢዶሎ ዩኒቨርስቲ (አከባቢ ላይ ያለው የፀጥታ ሁኔታ)

6, ጋምቤላ "(አከባቢ ላይ ያለው የፀጥታ ሁኔታ)

7, ቀብረ ዳር ዩኒቨርስቲ (ማወቅ አልቻልንም)

8, ጅንካ ዩኒቨርስቲ (ታገሱ)

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
2.7K viewsedited  09:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ