2022-05-11 13:23:24
ያልገባኝ ነገር…?
"…ትርፍ አምራች የሚባሉ ሃገራት፣ በኢንዱስትሪ የበለፀጉ የሚባሉቱ ሁሉ፣ ነዳጅና ስንዴ አቅራቢዎች ጭምር በየሪፖርታቸው ላይ ከ29 ዓመት በኋላ፣ ከ60 ዓመት በኋላ፣ ከ15 ዓመት በኋላ ወዘተ ታይቶ የማይታወቅ የኢኮኖሚ ድቀት ደረሰብን እያሉ በግልፅ ሲያለቃቅሱ እያየን ነው። በአንዳንድ የአውሮጳ ሃገራት እንዲያውም በነዳጅ እና በሸቀጣ ሸቀጥ አቅርቦት ላይ ጭማሪ በመታየቱ የተቃውሞ ሰልፎች ሁሉ መታየት ጀምረዋል።
"…ይህንና ይህን የመሳሰሉ ዓለም አቀፍ ዜናዎችን ሰምቼ አበቃና ወደ ምስኪን ሃገሬ ፊቴንም ጆሮዬንም አቅንቼ ስመለከት የማየውና የምሰማው ሁሉ ግራም ቀኝም ያጋባኛል። ታይቶ የማይታወቅ እድገት ይልልሃል አፈ ቅቤው የዥጋቤል ሰው ዐቢይ አሕመድ አሊ። በደቡብ ኦሮሚያ በቦረና ከብቶች አልቀው። የሰው ልጅ በበሬ ምትክ እያረሰ። ሶማሌ ክልልም እንደዚያው። በወለጋ ሚልዮኖች ተፈናቅለው። በቤኒሻንጉል በደቡብም እንደዚያው። ምሥራቅና ሰሜን ዐማራ ሙሉ ለሙሉ ወድሞ። አፋርም እንደዚያው። ትግራይ በሚልየን የሚቆጠር ህዝብ በምን ሁኔታ ውስጥ እንዳለ ከእግዚአብሔር በቀር ህወሓትም፣ ብልፅግናም በማያውቁበት ሁኔታ እድገታችን ተብሎ የሚወራውን ነገር ስሰማ ቁጥር ላይ በፊትም ደደብ ነበርኩ አሁንማ የባሰ ደደብ ነው ያደረገኝ።
"…ጦርነት በባህሪው ከባድ ወጪ የሚያስወጣ ነው። ሃገሪቷ እስከአሁን በማያባራ ጦርነት ውስጥ ናት። ከሸኔ ጋር እየተዛጠዙ ነው። መንግሥትም እየተዋጋሁ ነው እያለ ነው። ህወሓት ለሁለተኛ ዙር ውጊያ እያሟሟቀች ነው። ይሄም ወጪ አለው። አምራች ፋብሪካዎች በኃይል አቅርቦትም፣ በውጭ ምንዛሪ እጥረትም ምክንያት እየተዘጉ ነው። የምግብ፣ የሸቀጣሸቀጥ፣ የትራንስፖርት፣ የቤት ኪራይ ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል። ኑሮ እጅግ በጣም መወደዱ እየተነገረ ነው። አይመምህ እንጂ ከታመምክ ህክምናው የማይቀመስ፣ የማይቻልም መሆኑ ነው እየተነገረ ያለው። ከተሳሳትኩ እታረማለሁ።
"…እዚህ ላይ ነው ጥያቄዬን የማነሣው። እንዲህ ምስቅልቅሉ በወጣ ዓለም ላይ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ብቻውን በምን ተአምር ነው ተስፈንጥሮ አድጎ መንግሥት የሃገሪቱ እድገት በአስደናቂ ሁኔታ እየተመነደገ ነው የሚል ሪፖርት እንዲያወጣ ያስደረገው። ቆይ ሃገሪቱ የምትመራው በእነ ኢዩ ጩፋ እና በእነ ዳንሳ መንፈስ ነው እንዴ? እንዲያ ካልሆነ በቀር እንዴት ባለ ሁናቴ ውስጥ ቢኮን ነው እነ ጣሊያን፣ እነ ግሪክ ወገቤን በሚሉበት በዚህ ዘመን ከጣት የማይቆጠሩት ፋብሪካዎቿ የተዘጉባት ኢትዮጵያችን ተአምራዊ እድገት ላይ ነኝ እንድትል ያደረጋት? የገባችሁ አስረዱኝ።
"…ገበሬ አፈናቅላ፣ ምርት እና ክምር በእሳት አቃጥላ፣ የቀንድ ከብቶቿም በድርቅ ተፈጅተውባት፣ የለስላሳ ፋብሪካ እንኳ የውጭ ምንዛሪ አጥቶ ተዘግቶባት፣ ነዳጅ ጣራ…
https://t.me/esat_television_official
9.5K views10:23