Get Mystery Box with random crypto!

Esat tv

የቴሌግራም ቻናል አርማ esat_television_official — Esat tv E
የቴሌግራም ቻናል አርማ esat_television_official — Esat tv
የሰርጥ አድራሻ: @esat_television_official
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 59
የሰርጥ መግለጫ

ኢሳት የኢትዮጵያ #አይን እና #ጆሮ
መሳይ መኮንን ✍️

Ratings & Reviews

2.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

1

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 3

2022-05-12 18:31:51
ትዊተር ላይ እየተዘዋወረ ባለው በዚህ ቪዲዮ ስር ከአንድ ዩክሬናዊ የተሰጠ አስተያየት


////'Police chase' ነው።ተፈላጊው ሞተረኛ ወደ ኪየቭ ከተማ ለመግባት እየከነፈ ነው።ሞተረኛው ሩሲያዊ እንደሆነ በፖሊሶቹ ተጠርጥሯል።በሌላኛው አቅጣጫ መንገድ ዘግተው ሞተረኛውን እንዲያቆሙት ከታዘዙት ፖሊሶች መካከል አንደኛው የራሱን ደህንነት ችላ ብሎ በመጋፈጡ የሆነው ሆነ ። በኋላ ላይ የሞተረኛው ማንነት ሲጣራ ግን ዩክሬናዊ ሆኖ ተገኘ .....ጠጥቶ የሰከረ ዩክሬናዊ! ////

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
5.9K viewsedited  15:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 18:08:17
የሆነስ ሆነና…

"…ሌላው ቢቀር ብርሃኑ ጁላና የአበባው ታደሰ ጦር ለፍርጠጣው ስልታዊ ማፈግፈግ ብሎ ከመቀሌ ወደ ሞለሌ በፈረጠጠ ጊዜ፣ እነ አገኘሁ ተሻገርና እነ አቶ አብርሃም የፓርቲ ገንዘብ በሚልዮን በሚልዮን ተከፋፍለው በፈረጠጡበት ጊዜ፣ እሱ ግን ህዝብ አስተባብሮ፣ ወጣቱን አደራጅቶ የተሾመባትን ከተማ የሚወዳትን ወልድያን ላለማስደፈር ብሎ በብርቱ የተዋደቀውን የወልድያ ከንቲማ ጀግና ክቡር አቶ መሀመድ ያሲንስ ተሸለመ ወይ? እኔ እስከአሁን ስላላየሁ ስላልሰማሁም ነው። ሸለሙት ግን?

ኢትዮጵያ ሃገሬ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ … እንደይሆን ብዬ ነው።

"…እየኮመታችሁ…!!

መሳይ መኮንን

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
6.0K viewsedited  15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 16:02:02
#መልካምዜና ጉግል የትርጉም መስጫ አገልግሎቱ (Google Translate) 24 አዳዲስ ቋንቋዎችን ማስጀመሩን ያስታወቀ ሲሆን በዚህ ውስጥ አፋን ኦሮሞ እና ትግርኛ ተካተዋል!

ከኢትዮጵያ ከአማርኛ በተጨማሪ ሌሎች ሁለት ቋንቋዎችን በ Google Translate አማካኝነት መተርጎም ይቻላል ማለት ነው። ከዚህ በኋላ "የተፃፈው ምን ይሆን?" ከማለት በቀጥታ ኮፒ አርጎ በማስገባት ትርጉሙን ማየት ይቻላል። አንዳንድ ግዜ የጉግል ትርጉሞች ችግር ያለባቸው ቢሆንም ብዙ ግዜ ግን እጅግ ጠቃሚ ናቸው።

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
6.8K viewsedited  13:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 15:49:58
መርጌታ ያብስራ የባህል መድህኒት አስማት እና ጥበብ ይፈልጋሉ:
የምንሰጣቸው የጥበብ አገልግሎቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል
1 ለመፍትሔ ስራይ
2 ለህማም
3 ጋኔን ለያዘው ሰው
4 ቡዳ ለበላው
5 ለቁራኛ
6 የዛር ውላጅ ለተዋረሰው
7 ነገረ ሚስጥራት(ሚስጥር የሚነግር)
8 ነገረ ራዕይ(ራዕይ የሚያሳይ)
9 ለዓቃቤ ርዕስ
10 ለመክስት
11 ለቀለም(ለትምህርት)
12 ሰላቢ የማያስጠጋ
13 ለመፍትሔ ሀብት
14 ለመስተፋቅር
15 ለሁሉ ሠናይ
16 ለገብያ
17 ለአምፅኦ ብእሲት(ፍቅረኛ ላጣ ወይም ላጣች የሚሰራ)
18 ለመድፍነ ፀር
19 ሌባ የማያስነካ
20 ለበረከት
21 ለከብት መስተሐድር(ከብት እንደረይጠፋ)
22 አፍዝዝ አደንግዝ
23 ለጠላት (ጠላት እንዳይጎዳ የሚያደርግ)
24 ለግርማ ሞገስ
25 መርበቡተ ሰለሞን
26 ለዓይነ ጥላ
27 ምስሐበ ንዋይ ወምስሐበ ሰብእ
28 ለሁሉ መስተፋቅር
29 ጸሎተ ዕለታት
30 ለታሰረ ሰው እነዲፈታ የሚያደር
31 ለእጅ ስራ (እንዲቀናህ)
32 ለትዳር የሚሆን የኮከብ ቆጠራ
33 ለድምፅ
34 ለብልት
አገልግሎት(ምናልባት ያለ ኮከባቸው
የተጋቡ ካሉ
አስማምቶ የሚያኖር መድሀኒት

ከምሰጣቸው በትንሹ ይህን ይመስላል

https://t.me/+1AYabX41TA83OTY0
ለጥያቄወ 0924245307 ይደውሉልን
6.8K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 14:47:34
ሰበር ሰበር ዜና

ሽብርተኛው ህወሓት በወልቃይት ጠገዴ በማይጋማ እና መደማመር አካባቢ የከፈተው ጦርነት እንዳለ ሆኖ ህወሓት ወደ ኤርትራ ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ጦርነት ከፍቷል::

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
7.1K viewsedited  11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 06:58:05 ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ተይዞ ስለቆየበት ሁኔታ በዝርዝር ተናገረ

#Ethiopia | ከአንድ ሳምንት በላይ ደብዛው ጠፍቶ የነበረው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ከመኖሪያ ቤቱ 'የተደራጀ የሕገ-ወጥ ቡድን' በሚመስል አካል ከተያዘ በኋላ ጦር ኃይሎች አካባቢ ባለ 'የድሮ ቤት' ውስጥ ሳያቆዩኝ አይቀርም አለ። ከአንድ ሳምንት ቆይታ በኋላ ትናንት ግንቦት 01/2014 ዓ.ም. ወደ መኖሪያ ቤቱ የተመለሰው ጋዜጠኛ ጎበዜ፤ ተይዞ ወደቆየበት 'የድሮ ቤት' እስኪደርስ ድረስ እንዲሁም ጥያቄ ሲቀርብለት ዓይኑ በጨርቅ ታስሮ እንደነበር ለቢቢሲ ተናግሯል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ተይዞ የቆየው ጦር ኃይሎች አካባቢ ባለ ቤት መሆኑን ያወቀው የያዙት ሰዎች ወደ ሥፍራው ለመሄድ አቅጣጫ ሲነጋገሩ ከሰማ በኋላ መሆኑን አስረድቷል።
ጋዜጠኛ ጎበዜ እንዴት ተያዘ?

"የያዙኝ የኢድ በዓል ዋዜማ ዕለት እሁድ ዕለት ረፋድ 4 ሰዓት አካባቢ ነበር" ይላል። 7 ወይም 8 የሚሆኑ ሲቪል የለበሱ እና የመንግሥት የፀጥታ ኃይሎች የማይመስሉ ግለሰቦች አያት አካባቢ ወደሚኖርበት ግቢ ዘለው መግባታቸውን ጎበዜ ያስረዳል።

"የፀጥታ ኃይል ናቸው ለማለት ይከብዳል። ድርጊታቸው የመንግሥት የፀጥታ ኃይል አይመስልም። ግቢ ውስጥ ገብተው ሲጯጯሁ ሰው አምልጧቸው የሚፈልጉ እንጂ እኔን ሊይዙ የመጡ አልመሰለኝም ነበር። 'አንተን ነው የምንፈልገው' አሉኝ" ይላል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ የግለሰቦቹን ማንነት ቢጠይቅም ወዲያው ምላሽ ለመስጠት ፍቃደኛ እንዳልነበሩ ይናገራል።

"መሳሪያ ይዘዋል። ማናችሁ ብዬ መታወቂያ ስጠይቃቸው መታወቂያ ለማሳየት ፍላጎት የላቸውም። ሲሳደቡ ነበር" ይላል።

በግለሰቦቹ አለባበስ እና ሁኔታ የመንግሥት ኃይሎች ስለመሆናቸው ጥርጣሬ አደረብኝ የሚለው ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ፤ ሊይዙት የመጡ ሰዎችን እንዲህ ሲል ይገልጻቸዋል።

"አለባበሳቸው የተለያየ ሲሆን ኮፍያ ባለው ሹራብ የተሸፈኑ አሉበት። ፀጉራቸው ያደገ። ሁኔታቸው እንደ 'ጋንግስተር' [አደገኛ ቦዘኔ] ነው። . . . የተደራጀ የሕገ-ወጥ ቡድን መጣ ብዬ ነው ያሰብኩት" ይላል።

ጨምሮም ሊይዙት ከመጡት ሰዎች መካከል አንዱ ቪዲዮ መቅረጽ መጀመሩን ጎበዜ ይናገራል። በተደጋጋሚ ማንነታቸውን ሲጠይቅ ከግለሰቦቹ መካከል አንዱ የፀጥታ ኃይል መሆናቸውን እንደነገረው እና መታወቂያ እንዳሳየው ያስታውሳል።

"ያሳየኝ መታወቂያ የመከላከያ ሠራዊት አባል እና የመረጃ ምናምን ይላል። ከዚያ ወደ ውጪ ይዘውኝ ወጡ" በማለት ጎበዜ ይናገራል።

ጎበዜ ግለሰቦቹ ይዘውት የሄዱበት መኪና የአገር መከላከያ ሠራዊት ሰሌዳ እንዳለው ይናገራል።

በግለሰቦቹ ተይዞ ከመኖሪያ ቤቱ ከወጣ በኋላ ዓይኑን በጨርቅ ሸፍነው ይዘውት እንደሄዱ ይናገራል። በመኪናው እየተጓዙ፤ "በጣም እየተጯጯሁ ይነጋገራሉ። ከንግግራቸው ጦር ኃይሎች አካባቢ እንደወሰዱኝ ማወቅ ችያለሁ" ይላል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ግለሰቦቹ ይዘውት ወደሚሄዱበት ቦታ 'ጀነራል' እያሉ ከሚጠሩት ግለሰብ ትዕዛዝ ይቀበሉ ነበር ይላል።

"አቅጣጫ እየነገራቸው ነበር ግን ያወቁት አይመስለኝም። መጨረሻ ላይ አንድ ግቢ ውስጥ ይዘውኝ ገቡ። ሰፊ ግቢ ነው። ግቢ ውስጥ ያሉት ቤቶች የድሮ ቤቶች ናቸው። ወለላቸው ጣውላ ነው። እዚያ ነው ይዘው ያቆዩኝ"።

ጎበዜ በቀጣይ ግን መርማሪ መጥቶ ጥያቄ እንዳቀረበለት ይናገራል።

"መርማሪው ሲመጣ ፊቴ ይሸፈናል" ያለው ጋዜጠኛ ጎበዜ፤ ጥያቄ ሲያቀርብለት ከነበረው ግለሰብ ሦስት ጉዳዮች በተደጋጋሚ ማንሳቱን ያስታውሳል።

"የመጀመሪያው አንተ ፋኖን ትደግፋለህ፤ የፋኖ አባል ነህ የሚል ነው። ሁለተኛ ደግሞ አንተ ኦሮሞ ጠል ነህ የሚል ነው። ሦስተኛው ደግሞ በተለያዩ ግጭቶች ውስጥ እጅህ አለበት የሚል ነው" በማለት ያስረዳል።

ጋዜጠኛ ሲሳይ ጥያቄ ሲያቀርቡለት የነበሩት ጉዳዮች በመገናኛ ብዙሃኃን ከሚናገራቸው እና በማኅብራዊ ሚዲያዎች የሚጽፋቸው ጉዳዮች እንደሆኑ ይናገራል።

ጎበዜ ተይዞ በነበረበት ወቅትም ስለያዙት ግለሰቦች ማንነት ጥያቄ ሲያቀርብ እንደነበረና "አንዳንዴ መከላከያ ነን ይላሉ። መከላከያ እና ደኅንነት ተቀናጅተው እንደያዙኝም ይናገራሉ።"

ጋዜጠኛ ጎበዜ ከመኖሪያ ቤቱ ተይዞ ሲወጣ የአገር መከላከያ ሠሌዳ ባለው መኪና መወሰዱ እና ግለሰቦቹ መንገድ ይጠቆሙ የነበሩት 'ጀነራል' እያሉ በሚጠሩት ግለሰብ በመሆኑ ተይዞ የነበረው በአገር መከላከያ እንደሆነ እንደሚያምን ይገልጻል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ታስሮ በነበረበት ወቅት ምንም አይነት አካላዊ ጥቃት እንዳልተፈጸመበት እና የምግብ ችግር እንዳልነበረበት ለቢቢሲ ተናግሯል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ትናንት ግንቦት 1/2014 ዓ.ም. ምሽት 3 ሰዓት አካባቢ ይዘውት የቆዩት ሰዎች ዓይኑን በጨርቅ አስረው መኖሪያ ቤቱ ጥለውት እንደሄዱ ተናግሯል።

ጎበዜ የያዙት ግለሰቦች ከመልቀቃቸው በፊት " 'እንደዚህ አይነት ሥራ አትስራ። አገራችንን የምንገነባው አንድ ላይ ነው። የትም ቦታ ብትሆን ከእኛ አታመልጥም።' የሚል ማስፈራሪያ ምክር ያለበት ንግግር ተናግረውኛል" ይላል።

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ተይዞ የቆየበት ሁኔታ እና የቀረበበት ማስፈራሪያ ከሚዲያ ሥራው እንደማያዛንፈው ተናግሯል።

"ሊከታተሉኝ ይችላሉ። ቤተሰብ ጓደኛ 'ተው ይቅርብህ' በሚሉ ምክንያቶች ጫናዎች ሊኖሩ ይችላሉ። ይህ ግን እኔን ወደ ኋላ አይመልሰኝም። በሚዲያ ሥራዬ እቀጥላለሁ።"

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ቀደም ሲል በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት) ከዚያም ደግሞ የኛ በሚባል ቴሌቪዥን ጣቢያ ላይ ሲሰራ ነበር።

ጋዜጠኛ ጎበዜ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራ ክልል ዘልቀው በገቡ ወቅት በፌስቡክ ገጹ በሚያጋራቸው መረጃዎች የብዙዎችን ትኩረት ስቦ ነበር።

በጉዳዩ ላይ የአገር መከላከያ ሠራዊት አስተያየትን ለማካተት ያደረግነው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።

BBC

https://t.me/esat_television_official
9.1K views03:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 06:57:52
8.1K views03:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 21:05:34 75 አመራርና ሰራተኞች ላይ እርምጃ ወሰደ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሥነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 75 አመራርና ሰራተኞች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በአገልግሎቱ የሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክተር አቶ ህብረወርቅ ይመኑ÷ተቋሙ ባለፉት 9 ወራት ከተለያዩ አካላት የቀረቡ 97 ጥቆማዎች እና 163 አቤቱታዎችን ተቀብሎ የማጣራ ስራ መስራቱን ተናግረዋል፡፡

በዚህም የሥነ-ምግባር ጥሰት በፈፀሙ 75 አመራርና ሰራተኞች ላይ የተለያዩ አስተዳደራዊ እርምጃዎች መውሰዱን እና ቀሪ 87 የሚሆኑት ጉዳያቸው በስነ ምግበር በመታየት ሂደት ላይ እንደሚገኙ ነው ያስረዱት፡፡

አስተዳደራዊ እርምጃው የተወሰደው በተቋሙ ህብረት ስምምነት እና በማኔጅመንት መተዳደሪያ ደንብ መሰረት መሆኑን የገለፁት ዳይሬክተሩ÷የገንዘብ ቅጣት፣ ከኃላፊነት ቦታ ማንሳት እንዲሁም እስከ ስራ ስንብት የሚደርስ እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል፡፡

አብዛኛው የተቋሙ ሰራተኛ ጥራት ያለውና አስተማማኝ አገልግሎት ለመስጠት የበኩሉን ጥረት እያደረገ ቢሆንም ጥቂቶች በህገ-ወጥ መንገድ አገልግሎቱን ለማግኘት ከሚፈልጉ አካላትና ደላሎች ጋር በመሆን ብልሹ አሰራር የሚፈጽሙ መኖራቸውን ተናግረዋል፡፡

በህገ-ወጥ መንገድ ቆጣሪ ማስገባት፣ ቆጣሪ ለማስገባት በሚደረገው ሂደት ጉቦ መጠየቅ፣ ደንበኛን በአግባቡ አለማስተናገድ፣ ያለበቂ ምክንያት ስራን ማዘግየትና ደንበኛን ማጉላላት፣ በአስቸኳይ ጥገና ስራ ደንበኞች ገንዘብ በማዋጣት እንዲከፍሉ ማስገደድ፣ ያለደረሰኝ የቆጣሪ ማስገቢያ ክፍያ መቀበል እና የመሳሰሉት በተደረገ ማጣራት ስራ የተገኙ የብልሹ አሰራር መገለጫዎች መሆናቸውን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል፡፡

ተቋሙ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ አስተዳደራዊ እና ህጋዊ እርምጃ ከመውሰድ ባለፈ ብልሹ አሰራርን ለመከላከል የተለያዩ ስራዎች እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

ተቋሙ የተለያዩ የቅሬታ ማስተናገጃ ስርዓት መዘርጋቱን የገለፁት አቶ ህብረወርቅ÷ ደንበኞች በተዘረጉ የቅሬታ ማቅረቢያ ስርዓቶች ቅሬታቸውን፣ ጥቆማቸውን እና ሃሳባቸውን ማቅረብ ይችላሉ ማለታቸውን ከአገልግሎቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

https://t.me/esat_television_official
9.6K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 21:05:24
8.5K views18:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-11 18:28:48
“በአንድነት ለጋራ ዓላማ መቆም ተግዳሮቶችን ለመሻገር እንዲሁም ለሀገር ዘላቂ ብልጽግናን ለመገንባት አቅም ይሆናል” - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

*********

በአንድነት ጋራ ዓላማ መም ተግዳሮቶች ለመሻገር እዲሁም ለሀገር ዘላቂ ብልጽግን ለመገንባት አቅም ይሆናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስታወቁ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በባህርዳር ከተማ በተካሄደው የአማራ ክልል የጸጥታ ኃይሎች የእውቅናና የምስጋና መርሀ ግብር ላይ ተገኝተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉት ንግግርም በአሁኑ ወቅት የሁሉም ክልሎች ልዩ ሀይሎች በተሻለ አቋምና ብቃት ላይ ይገኛሉ፤ የእነዚህ ሀይሎች የተሻለ ብቃትትና አቋም ላይ መሆን የኢትዮጵያን ሰላም አንድነትና ህልውና ዋስትና ናቸው ሲሉ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ጠላቶች ይህንን ሳይረዱ ኢትዮጵያዊያን በብሄር፣ በቋንቋ፣ በሀይማኖት በፖለቲካ ተከፋፍለዋል በሚል የተሳሳተ ስሌት ስህተት እንዳይፈጽሙ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ያሳሰቡት።

በዛሬው እለት የተሰጠው ሽልማት የህይወት እና የደም ዋጋ ለከፈሉ እንዲሁም በገንዘብና በእውቀት ለሀገራቸው አስተዋጽኦ ላበረከቱት መላ ኢትዮጵያዊያን የተሰጠም ነው ብለዋል።

https://t.me/esat_television_official
https://t.me/esat_television_official
9.7K views15:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ