Get Mystery Box with random crypto!

#WFP #Ethiopia የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክ | Esat tv

#WFP #Ethiopia

የግጭት ማቆም ውሳኔ ይፋ ከተደረገበት ከመጋቢት ወር ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል ከሚገባው እርዳታ #ከፍተኛ መጠን ያለው ቁሳቁስ በዚህ ሳምንት ወደ ክልሉ መግባቱን የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስታውቋል።

በዚህ ሣምንት ወደ ትግራይ የገባው 15 ሺህ ቶን ምግብ እና ሌሎች የነፍስ አድን አቅርቦቶች ሲሆን አሁንም ተጨማሪ እርዳታ ወደ ክልሉ እያመራ መሆኑን WFP ገልጿል።

ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ (በዓለም ምግብ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ቢሮ ኃላፊ) ፥ " ፍጥነቱ አሁን እየጨመረ ስለሆነ በዚህ ወር መጨረሻ በሁለት ሳምንታት ጊዜ ውስጥ 30 ሺህ ሜትሪክ ቶን ምግብ እና የምግብ ሸቀጦች ወደ ትግራይ ይደርሳል ብለን ተስፋ እናደርጋለን ። እቅዳችን በሰኔ ወር መጨረሻ 100 ሺህ ቶን ምግብ ለማድረስ ነው " ብለዋል።

በሌላ በኩል ፤ የረድኤት ድርጅቶች አፋርን ጨምሮ በአጎራባችን ክልሎች ቀውሶች እየተባባሱ በመሆናቸው እጅ እያጠራቸው ፤ የእርዳታ ክምችታቸውም እየተመናመነ መሆኑን ጠቁመዋል።

የዩክሬን ጦርነት እና ሌሎችም በዓለም ዙሪያ የታዩት ቀውሶች የለጋሾችን የረድዔት አቅም እየቀነሰው መሆኑ የታገለፀ ሲሆን WFP በሚቀጥለው 6 ወራት ውስጥ በኢትዮጵያ ለሚያስፈልገው የእርዳታ አቅርቦት የ522 ሚሊዮን ዶላር እጥረት እንደሚያጋጥመው ገልጿል።

ከዚህ ውስጥ 220 ሚሊዮን ዶላር ትግራይን ጨምሮ በሰሜን የኢትዮጵያ ክፍል ለሚሰራው የረድኤት ስራ የሚውል ነው።

ኤድሪያብ ቫን ደር ክናፕ ፤ " ያለን ክምችት በጣም በፍጥነት እያለቀ ነው። ስለዚህ ስጋታችን ይህን አውንታዊ ድባብ ፈጥረን እነኚህን መተላለፊያዎች ከፍተን መልሰን ማቆም ሊኖርብን ነው እናም ሁሉ ነገር ከሚያዚያ በፊት ወደነበረው ስፍራ ሊመለስ ነው " ብለዋል።